የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion 📩 @Share_Home
Last updated 2 months ago
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 5 months, 3 weeks ago
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 7 months, 2 weeks ago
…ᘛሀብታም ማን ነው..... ❓❔❓❔
ድሃ ማለት ማን እንደሆነ ታወቃላችሁ⁉️**
•
የአላህ መልክተኛ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ከዕለታት አንድ ቀን ከባለደረቦቻቸው ቁጭ ብለው ሳለ፦
“ድሐ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ?” በማለት ይጠይቃሉ።
•
ሰሐቦችም ፦ “እኛ ጋር ድሀ ማለት ምንም ንብረትና ገንዘብ የሌለው ነው” በማለት ይመልሳሉ።
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ግን፦ “ከኡመቴ ደሀ ማለት የትንሳኤ ቀን በብዙ ሰላቶች፤ ዘካዎችና፤ ፆሞች የሚመጣ ሰው ነው፣ ነገር ግን ይህ ሰው አንድ ወንድሙን ሰድቧል፣ ሌላው ላይ ዋሽቷል፣ የአንዱን ገንዘብ ያለአግባብ ወስዷል፣ የሌላውን ደም አፍስሷል፣ አንዱን መትቷል፣ በሌላው ላይም ድንበር አልፏል፣
ያኔም የቂያም ቀን (የምርመራ ቀን) የራሱን ጥሩ ሥራዎች ለበደላቸው በካሳ መልክ አሳልፎ ይሰጣል፣ ጥሩሥራው ለመካሻ አልበቃ ይለውና የበደላቸውን ሰዎች ኃጢያት ይሸከማል፣ ከዚያም ወደ ጀሀነም ይወረወራል” በማለት መለሱላቸው።
ቢንቱ አብደሪያ??
????????@Yemuslimoch_Akida ጆይን ይበሉ?**
፨፨፨፨፨፨፨፨#ጁለይቢብ**፨፨፨፨፨፨፨፨፨
«ሰባት ጥሎ ወድቆዋል እሱም ከኔ ነው እኔም ከርሱ ነኝ » #ነብዩ ሙሀመድ ﷺ
ስሙ ያልተለመደና ያልተሟላ ነው ። ጁለይቢብ «አጭር ፣ ትንሽ » ማለት ሲሆን የሚያመለክተውም ድንክዬ የነበረ መሆኑን ነው። ጁለይቢብ መልከ ጥፉ ሰውም ነበር ።
ሕብረተሰቡ ያገለለው ጁለይቢብ የዘር ሀረጉም አይታወቅም ነበር ። ስለ አባቱ እና እናቱ እንዲሁም ጎሳው በታሪክ የደረሰ የለም።
ቤተሰብ እና ጎሳን በማምለክ ላይ የተመሰረተው የጃሂልያ ህብረተሰብ ውስጥ ጉዋደኛ ደጋፊ እና ተከላካይ እንደሌለው ተረድቶዋል ። የሚታወቀው የአንሷር አረብ መሆኑ ብቻ ነው ። ምናልባት ከመዲና ውጪ ከሚኖሩ አረቦች የመጣ ይሁን ? ወይስ ከከተማው አንሷሮች ? አላህ ያውቃል ።
በሰብአዊነቱ ተከብሮ በርኅራሄ አይን ይታይ ይሁን? እንዴት? በማን? የችግሩ ተካፋይ የደስታው ተቋዳሽ ሰው ሊያገኝ ይችላልን ?
በነብዩ ሙሀመድﷺ አማካኝነት የሚመራውና ትእዛዝ ከሰማይ የሚወርድለት አዲሱ ህብረተሰብ በውስጥ እና በውጪ ጠላቶች ተዋክቦ የሞት ሽረት ትግል ላይ በነበረበት ወቅት ጁለይቢብን አስታውሶ አቅፎና ደግፎ ይይዘው ይሁን ? የርህራሄ ህያው ተምሳሌት የሆኑት ነብይﷺ የመዲና ውስብስብ ችግሮች ምንም ያህል ቢገዝፉ ጁለይቢብን ከልባቸው ሊያስረሷቸው አልቻሉም።
ምልእክተኛውﷺ ወደ አንድ አንሷር ( የመዲና ሰው ) ቤት ሄደው «ልጅህን ለትዳር ፈልጌአታለሁ» አሉት « ማሻአላህ አንቱ የአላህ መልእክተኛ ልብን በፍሰሀ የሚሞላ አስደሳች ነገር ነው የጠየቁኝ» አለ በደስታ ፊቱ ፈክቶ ። «ለእኔ ግን እምዳይመስልህ» አሉት ነብዩ ﷺ «የአላህ መልእክተኛ ሆይ ታዲያ ለማን ነው ? » ብሎ በቀዘቀዘ ድምፅ ጠየቃቸው ። «ለጁለይቢብ» በማለት መለሱለት ።
በድንጋጤ የፈዘዘው አንሷር ሚስቴን ላማክር በማለት በፍጥነት ከነብዩ ራቀ ። ሚስቱ ጋር እንደደረሰ « የአላህ መልእክተኛ ልጅሽን ለትዳር ጠየቁ» ሲላት እሷም በደስታ « ማሻአላህ በጣም ደስ የሚል ዜና ነገርከኝ» « ለርሳቸው መሰለሽን ? ለጁለይቢብ ነው እኮ» ሲል አቁዋረጥት ። «ለጁለይቢብ (በፍፁመ) በህያው አላህ ይሁንብኝ ለሱ አንድራትም» አለች በንዴት ፊቱዋ ጠቁሮ ።
አባትየው አቋማቸውን ለመልክተኛው ለመናገር ሲነሳ ልጅ ጭምጭምታ ሰምታ «ለማን ልዳር ነበር» በማለት ጠየቀቻቸው ።
ነብዩﷺ ለጁለይቢብ (ረ.ዐ) እንደጠየቋቸውና አነሱ ግን ፍቃደኛ ያለመሆናቸውን እናትየው በነገረቻት ጊዜ ልጅቱዋ በጣም አዘነች ተረበሸች ።
«የአላህን መልእክተኛ ﷺ ጥያቄ ውድቅ ታደርጋላችሁን? እንዳታከስሩኝ ወደ እሳቸው ላኪኝ »
በማለት የኢስላም መልእክት የገባት እና ኢማን የተላበሰችዋ ልጅ ጠየቀች ።
የነብዩ «» ትእዛዝ ከማክበር እና ከመፈፀም በላይ ለአንድ ሙስሊም ምን ደስታ ይኖረዋል ? ጁለይቢብ ይህችን የቁርአን አንቀፅ ሰማ ፦
【(وَمَا كَانَ لِمُؤۡمِنࣲ وَلَا مُؤۡمِنَةٍ إِذَا قَضَى ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥۤ أَمۡرًا أَن یَكُونَ لَهُمُ ٱلۡخِیَرَةُ مِنۡ أَمۡرِهِمۡۗ وَمَن یَعۡصِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ فَقَدۡ ضَلَّ ضَلَـٰلࣰا مُّبِینࣰا)】
【አላህና መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ ለምእምናንና ለምእምናት ከነገራቸው ለእነርሱ ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም! የአላህንና የመልክተኛውንም ትእዛዝ የጣሰ ሰው ግልጽ የሆነን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ፡፡】
አንቀፁ ለመነሻነት የወረደው የዘይነብ ቢንት ጀህሽ እና ዘይድ ኢብኑ አል ሀሪስን እንዲሁም ተመሳሳይ ችግር የገጠማቸውን ሰሀቦች በማስመልከት ነበር ። ቀድሞ ባሪያ የነበረውን ዘይድን እንድታገባ ነብዩ ያቀረቡለትን ሀሳብ አልተዋጠላትም ። በመሆኑም ጋብቻው እንብዛም አልቆየም ተፋቱ። በመጨረሻም ዘይነብ ነብዩን ሙሀመድን «»አገባች።
ለጁለይቢብ የታጨችው ልጅ የቁርአኑን አንቀፅ ለወላጆቿ በማንበብ «የአላህ መልእክተኛ ይበጅሻል ያሉኝን ነገር ሁሉ በደስታ እቀበለዋለው። በተግባርም እተረጉመዋለው » ብላ ነበር። ረሱል መልሱዋን በሰሙ ጊዜ « ጌተዬ ሆይ ጥሩውን ለእሷ አድርግላት ህይወቷንም የችግርና የመከራ አታድርገው » በማለት አላህን ለመኑላት ።
እንደሷ ለትዳር ተስማሚና ብቁ ከአንሷር ሴቶች መካከል አልነበረም ይባል ነበር ። በነብዩ እየተረዱ ጁለይቢብ በሞት እስኪለያት ድረስ በደስታ አብረው ኖረዋል። በአንድ ወቅት ጁለይቢብ ከነብዩ ጋር ለጂሀድ ዘምቶ ከሙሽሪኮች ጋር ጦር ገጠሙ ። ጦርነቱን በድል ከተወጡት ቡሀላ ነብዩ ሙሀመድﷺ « ከኛ የጠፋ ሰው አለ ? » በማለት ሰሀቦችን ጠየቁ ። ሁሉም ዘመዱን ጉዋደኛውን እገሌ እገሌ እያለ ይቆጥር ጀመር እየዞሩ ቢጠይቁ ሁሉም ወዳጁን ብቻ ይጠራል ።
በመጨረሻ ረሱልﷺ «እኔ ግን ጁለይቢብን አጣው በጦር ሜዳው ፈልጉልኝ» በማለት አዘዙ። ከሰባት ከሀዲያን ጎን ወድቆ አገኙት ። ነብዩ ወደ ጁለይቢብ ሄደው ከአስክሬኑ ፊት ቆመው «ሰባት ገድሎ ተገደለ እሱም ከኔ ነው እኔም ከርሱ ነኝ » አሉ ። ይህችን ወርቃማ ቃል ሁለት ሶስት ጊዜ ደጋገሟት ። በእጃቸው አቅፈው አነሱት ። መቃብሩ ተቆፈረለት ። ሸሂድ ነውና ሰውነቱን ሳይታጠብ ቀበሩት።
፠፠፠፠፠፠፠ ረዲየላሁ ዐንሁ ፠፠፠፠፠፠፠፠
ቢንቱ አብደሪያ??**@limugenet@limugenet
_ተዉሂድ_የሁሉም_መሰረት ክፍል_ 1⃣? بسم الله الرحمٰن الرحيم الحمد لله رب العالمين والصلاة والسلام على رسول الله አሏህ ሱብሐነሁ ወተዓላ እኛን የሰው ልጆችን ያለምንም ዓላማና ግብ አልፈጠረንም። ይህን አስመልክቶ አሏሁ ተባረከ ወተዓላ በተከበረዉ ቁርኣኑ እንዲህ ይላል፦ { أَفَحَسِبْتُمْ أَنَّمَا خَلَقْنَاكُمْ عَبَثًا وَأَنَّكُمْ…
ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ አሉ።
ቁጭ አድርገው ይሰድቧቸዋል አይደል ?
ኢብራሂም ቱፋ ና ሱልጣን አማን ቁጭ ብለው ነው ማልቀስ ያለባቸው። የክፋት ዶክትሬት ነው የሰጧቸው ቢገባቸው።ይሄ እኮ የቁም ሞት ነው።
ሱልጣን አማን አዲስ አበባ ላይ ለነጠቀው መስጂድ ላሳሰረው ወጣት መሻይኽ ለተቃወመው መውሊድና ዚክር ተሸለመ አሉ።
ኢብራሂም ያው ላፈረሰው መስጂድ ላሰዋው ወጣት ስለተከለው ዘረኝነት በከረፉ ክርፋታሞች ክርፋት በታጠኑ ሰዎች ተሸለሙ አሉ???ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ።
ይሄ እኮ ከባድ ዱላ ነው አንዴ የከተማው ከንቲባ ለፀጥታ አካላት ትእዛዝ ሰጡ አሉ የኢትዮጵያ ህዝብ መቀጥቀጥ አለበት ሰአት እላፊ ያገኛቹሁትን ምቱ በሉልዋቸው ብሎ አዘዘ አሉ ከዛ የስራ አፈፃፃሙን ሊያይ ሲወጣ ፖሊሶቹ እንዳልነበር አደረጉት አሉ ከዛ እንደምንም ብሎ መታወቅያውን አውጥቶ ሲያሳያቸው እንዴ አለቃ እርሶ ኖት እንዴ እኛ እኮ የኢትዮጵያ ህዝብ መስለውን ነው አሉዋቸው ይባላል።???
እንዚህም ሰዎች ከዚህ በላይ ትንሽ ግልጥ ልጥ ሲሉ መንጋውም እንዴ እናንተናችሁ እንዴ እኛ እኮ ህዘበ ሙስሊም መስለውን ይላቸዋል። በመሰረቱ እጅጉን ብዙ መንጋ ነቅትዋል።
ተሸለማችሁ አይምሰላችሁ ፖሊሶቹ በከንቲባው እንደ ቀለዱት ሸላሚ ተብዬዎቹ እናንተ ላይ እየቀለዱባችሁ ነው እየቀለዱባችሁ ነው።
አሚር ሁሴን//ያ ሀቢቢ//
?*?*??**@Yemuslimoch_Akida@Yemuslimoch_Akida
?????? ጁምዓ ሙባርክ _ቀብር_ዚያራ_በአህለል_ሱናዎች_ዘንድ_የተፈቀ_ስለመሆኑ_ክፍል_ 2⃣ ﺑِﺴْﻢ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦِ ﺍﻟﺮَّﺣِﻴﻢ ﺍﻟْﺤَﻤْﺪُ ﻟﻠﻪِ ﺭَﺏِّ ﺍﻟْﻌَﺎﻟَﻤِﻴﻦ .. ﻟَﻪُ ﺍﻟﻨِّﻌْﻤَﺔُ ﻭَﻟَﻪُ ﺍﻟﻔَﻀْﻞُ ﻭَﻟَﻪُ ﺍﻟﺜَّﻨَﺎﺀُ ﺍﻟْﺤَﺴَﻦ ﻭَﺍﻟﺼَّﻼﺓُ ﻭَﺍﻟﺴَّﻼﻡُ ﻋَﻠﻰ ﺳَﻴِّﺪِﻧَﺎ ﻣُﺤَﻤَّﺪ?ُ ، ምስጋና፣ ጸጋ…
የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion 📩 @Share_Home
Last updated 2 months ago
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 5 months, 3 weeks ago
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 7 months, 2 weeks ago