Abel Ashebir Noah Real Estate

Description
Hi There!

This is Abel. I am a Sales Consultant at Noah Real Estate. You'll find different updates on this channel.
We recommend to visit

Community chat: https://t.me/hamster_kombat_chat_2

Twitter: x.com/hamster_kombat

YouTube: https://www.youtube.com/@HamsterKombat_Official

Bot: https://t.me/hamster_kombat_bot
Game: https://t.me/hamster_kombat_bot/

Last updated 4 months, 2 weeks ago

Your easy, fun crypto trading app for buying and trading any crypto on the market.

📱 App: @Blum
🆘 Help: @BlumSupport
ℹ️ Chat: @BlumCrypto_Chat

Last updated 4 months, 1 week ago

Turn your endless taps into a financial tool.
Join @tapswap_bot


Collaboration - @taping_Guru

Last updated 2 weeks, 6 days ago

1 year, 2 months ago

ኖህ ሪል እስቴት ያስገነባቸውን አዳዲስ መኖሪያ ቤቶች አስረከበ

"የአስተዳደሩ ድጋፍ ይቀጥላል" ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ኖህ ሪል እስቴት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ያስገነባቸውን 754 የመኖሪያ ቤቶች ምርቃት ስነ-ስርአትና 10ኛ ዓመቱን የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት ባለስልጣናት እና እንግዶች በተገኙበት በዛሬው እለት አክብሯል።

ኖህ ሪል እስቴት ባለፉት አስርት ዓመታት 8 ሺ በላይ ለሆኑ ቤተሰቦች በከፍተኛ ጥራት የተገነቡ ቤቶችን በታማኝነት፣ በሰዓቱ እና በቃሉ መሰረት ያስረከበ ሲሆን ይህ ጉዞ ኩባንያውን በኢትዮጵያ የቤቶች ልማት ዘርፍ ቁልፍ ተዋናይ ሆኖ እንዲቀጥል እንዳስቻለው ተገልጿል። ለአገራዊ የልማት ግቦች ስኬትም ትልቅ አስተዋዕዖ እያደረገ እንደሚገኝም ተነግሯል።

የኖህ ሪል ኢስቴት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ንፁህ አውግቸዉ “በዛሬው ዕለት በኖህ ግሪን ፓርክ ሳይት አዲስ የተገነባውን የመኖሪያ መንደር በይፋ ሲያስመርቅ ባለፉት አስርት ዓመታት የስኬት ጉዞአችን የምናከብርበት፣ እንዲሁም ወደፊት በአብሮነት ለተሻለ ሥራ ቃልኪዳናችንን የምናድስበት ነው” ብለዋል።

“ኖህ ሪል እስቴት የመኖሪያ አፓርትመንቶችን በጊዜው እና በጥራት ገንብቶ በማጠናቀቅ በደንበኞቹ ዘንድ አመኔታን ያተረፈ ተቋም ነው ሲሉም አክለዋል።

ኩባንያው በ2020 ዓ.ም ፣ 30 ሺ ቤቶችን ገንብቶ ለማስረከብ ትልቅ ራዕይ የሰነቀ ሲሆን ፣ የመኖሪያ ቦታዎችን ወደ ሚሊዮኖች ካሬ ሜትር ለማስፋፋት ማቀዱም ተነግሯል።

በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ለማልማት ከታቀደው 3 ሚልየን ካሬ ሜትር በላይ የሚሆነው ለመኖሪያ ቤት መገንቢያ ሲሆን 1 ሚልየን ካሬ ሜትር ያህል ደግሞ የንግድ ማእከላት ለመገንባት ይውላል ተብሏል ።

በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ላይ እየተካሄዱ ያሉ ፕሮጀከቶች የኖህ ሪል ስቴት ለላቀ ትጋት ቀጣይነት ማሳያ እንደሆኑ ተነግሯል።

በምረቃ ስነስርአቱ ላይ እንደተገለፀው የኖህ ታላቅ ስኬት ዋነኛ ማሳያው 31 ፕሮጀክቶች በጥራት እና በተቀመጠለት ጊዜ ማጠናቀቅ መቻሉ ነው። አሁን ላይ በርካታ በመካሄድ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ያሉት ኩባንያው ከፕሮጀክቶች መካከል በጉርድ ሾላ፣ በሰሚት፣ በቦሌ ፣ በፍላሚንጎ፣ በቀበና እና በእንቁላል ፋብሪካ ያሉ ግንባታዎች በመፋጠን ላይ ይገኛሉ።

በመርሐግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስአበባ ከተማ አዳነች አቤቤ የከተማችን ነዋሪዎች አንገብጋቢ ጥያቄ የሆነው የመኖሪያ ቤት አቅርቦት በመንግስት ብቻ የሚመለስ ሳይሆን ከግሉ ዘርፍ ጋር በትብብር መስራትን እና የግሉን ዘርፍ ማበረታታትን ይጠይቃል ብለዋል።

አያይዘውም ባለፉት 5 የለውጥ ዓመታት የተገነቡ 5 ሺ ቤቶችን ጨምሮ እስከአሁን ከ8 ሺ 600 በላይ ቤቶችን ገንብቶ ለነዋሪዎች ያስተላለፈ ሲሆን፣ ግንባታቸው በመጠናቅቅ ላይ ያሉ ቤቶች በጥራት መገንባታቸውን እና የበርካታ ነዋሪዎችን የቤት ችግር የሚቀርፉ መሆናቸውን በጉብኝታችን ወቅት መመልከታቸውን ጠቅሰዋል።

በመኖሪያ ቤት ላይ ለተሰማሩ ኩባንያዎች የከተማ አስተዳደራችን ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥልም ከንቲባዋ አረጋግጠዋል።
(በድሬቲዩብ ሪፖርተር)

We recommend to visit

Community chat: https://t.me/hamster_kombat_chat_2

Twitter: x.com/hamster_kombat

YouTube: https://www.youtube.com/@HamsterKombat_Official

Bot: https://t.me/hamster_kombat_bot
Game: https://t.me/hamster_kombat_bot/

Last updated 4 months, 2 weeks ago

Your easy, fun crypto trading app for buying and trading any crypto on the market.

📱 App: @Blum
🆘 Help: @BlumSupport
ℹ️ Chat: @BlumCrypto_Chat

Last updated 4 months, 1 week ago

Turn your endless taps into a financial tool.
Join @tapswap_bot


Collaboration - @taping_Guru

Last updated 2 weeks, 6 days ago