★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 4 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month ago
✥✥✥ሦስት ሌሊት እና መዓልት✥✥✥
? ጥያቄ:- ጌታችን ሦስት ቀንና ሌሊት በከርሠ መቃብር (በመቃብር ሆድ/ውስጥ/) ቆየ ስንል ኣቆጣጠሩ እንዴት ነው?
መልስ በኮሜንት?
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ
በዐቢይ ኃይል ወስልጣን
በታላቅ ኃይልና ሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
ዲያብሎስን አሰረው
አግኣዞ ለአዳም
አዳምን ነጻ አወጣው
ሰላም
ሰላም
እምይዕዜሰ
ከዛሬ ጀምሮ
ኮነ
ሆነ
? ፍስሃ ወሰላም
ደስታና ሰላም ?
"እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና፤ እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤"
ማቴ፳፰፥፭-፮
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች?
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
# ዕለተ ትንሣኤሁ ለክርስቶስ ዘቅዳሴ
#በዕለቱ_ቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበ_መልዕክታት_ወንጌልና_ምስባክ፡፡
ዲ/ን ቆሮ15÷20-41
ን/ዲ 1ጴጥ 1÷1-13
ን/ካ ግብ፡ሐዋ 2÷22-37
፡#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ 117÷24
ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር ።
ንትፈሣሕ ወንትሐሠይ ባቲ።
ኦ እግዚኦ አድኅንሶ።
#ትርጒም፦
እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት።ሐሴትን እናድርግ በእርሷም ደስ ይበለን።አቤቱ እባክህ አሁን አድን።
ዮሐ፥20 ÷1- 19
ቅዳሴ፦ ዘዲዮስቆሮስ
ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች #share እናድርግ
~ @DNZEMA ~
~ @DNZEMA ~
~ @DNZEMA ~
3ኛ-ኮርስ ክርስቲያናዊ ሕይወት እና ሥነ-ምግባር
#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን
◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆
፩.፮.፩, #ትእዛዝ-➊-ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አታምልክ
✅ይህ ትእዛዝ እግዚአብሔር እርሱነቱን የገለጠበትና አምልኮት የሚገባው እውነተኛ አምላክ እርሱ መሆኑን የሚያስገነዝብ ሲሆን ከዚህ ጋር እርሱን ተክቶ በርሱ ቦታ ሊመለክ የሚገባው ምንም አይነት ነገር ሊኖር እንደማይገባ የሚናገር ነው።
✅እስራኤላውያን ከግብፅ የጥንቆላ ኑሮን፣ የጣዖት አምልኮትንና የተለያዩ በአድ አምልኮትን አይተው ስለነበረ ለእስራኤላውያን ከፈጣሪያቸው እንዳይለዩ ባሕረ ኤርትራን ከተሻገሩ በኋላ በሙሴ አማካኝነት ይህን ህግ ነግሮአቸዋል።
✅ሲነግራቸውም "እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ፣ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አታምልክ፣ የማናቸውንም ነገር ምሳሌ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ። አትስገድላቸውም አታምልካቸውም" (ዘጸ 20፥2-6) በማለት አብራርቶ ነግሮአቸዋል።
✅ከዚህ ውጭ ግን ሰው በውስጡ ገንዘቡን፣ እውቀቱን፣ መልኩን ወዘተ ሊያመልክ/ሊመካበት ይችላል እሄ ማይገባ ነው ነገር ግን ገንዘብና አውቀት ለማግኘት ኑሮን ለማሸነፍ የሚያደርገው ሩጫ አምልኮ ባዕድ ማለት አይደለም።
✅የሁሉ ነገር ምንጭና መገኛ እግዚአብሔር መሆኑን በማመን ሁሌም ይህን ሣይዘነጋ መሥራት የሚገባውን እየሠራ ነገር ግን "ያለኝ ሁሉ ከአንተ የተገኘ ነው፤ እንዲኖረኝ ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ ስላለኝም ብቻ ያላንተ እርዳታ ማድረግ የምችለው ነገር የለኝም፣ ባለኝ ነገር እሠራ ዘንድ ስለረዳኸኝ አመሰግንሃለሁ። ነገንም በምትወደውና በምትፈቅደው መልክ እኖር ዘንድ ያለኝን ባርክልኝ" ብሎ ከእግዚአብሔር ፊት መንበርከክ ያሰፈልጋል።
✅በአምልኮተ እግዚአብሔር የሚኖር ሰው ከጥረቱ፤ ከድካሙ በላይ የሁሉ ነገር ምንጭ አምላክ መሆኑን ያውቃልና።
◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆
#ቀጣይ_ትምህርታችን-->ትእዛዝ 2️⃣ የእግዚአብሔር የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ?*#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን*!!?****
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች?
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
3ኛ-ኮርስ ክርስቲያናዊ ሕይወት እና ሥነ-ምግባር #በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን???? ፩.፫, #በነገረ_ድኅነት_የምግባር_አስፈላጊነት ✅የክርስትና ሕይወት ትልቁ አላማ መዳን ነው። ✅በክርስትና ትምህርት መዳን ማለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ በሚመጣበት ጊዜ የክብር ትንሣኤ ከሚነሱት፣ ደስ ከሚላቸውና ከሚዘምሩት "እናንተ የአባቴ ቡርካን ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችሁን…
ኧኸ ክበር ተመስገን ጌታችን
#አዝ
የነገስታቱ ሁሉ ንጉስ
የካህናቱ ቤተመቅደስ
በርባን ተፈቶ ተሰቀለ
እውነት በሀሰት ተከለለ
#አዝ
ለደከመው ሰው ማረፊያ ነው
ጌታ ቅርብ ነው ለለመነው
የሚያሰማራ በለምለሙ
ፈውስ ነው ጌታ ለአለሙ
#አዝ
የሚቀኙልህ ሊቃውንቱ
በኪዳኑና በሰአታቱ
ክበር እያሉ ሲያወድሱ
ቀንና ለሊት በመቅደሱ
#አዝ
ሞቴን በሞቱ የገደለ
ስለበደሌ ተሰቀለ
ምናለ ለኔ ያልሆነልኝ
እርቃኑን ሆኖ አለበሰኝ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች?
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
Your name gives me
Your name gives me
The strength to climb up mountain
I have passed through the snare
With your intercession
Holy virgin Mary
I’ve broken free through
your mediation
Above all creation
he has filled you with grace
His son born from your womb
Your flesh He has embraced
The vessel for the world
to be saved Yes it’s true
holiest of holies virgin
Mary it’s you
I will pass through the storm
With my support Mary
My weakness will vanish
Under the shade you bring
Without you we could not
Have received medicine
The heavenly manna through
You we were given
The father of David praise to the creator
Blessings have filled my home
Through the interceder
Those who draw near to you
In body and spirit
The heavenly reward from Him they’ll inherit
So that my soul be filled
And I may not hunger
From your abundant well
Nourish me my mother
By entering your home
Finally, I’m at peace
My clothes have been made new
From the stain I’m released
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች?
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
በዚህ ሊንክ ግቡ ጀምሯል
?
https://t.me/dnzema?livestream
አንዳንድ ነጥቦች በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ መከልከል ዙሪያ፦
1. ለዚህ አሳዛኝ ድርጊት የተቀነባበረ ሽፋን በቅርብ ሲሰጥ እንደምንሰማ የታወቀ ነው። በመንግሥት አካላት ተደርሶ የሚቀርበው ድራማና ዶክመንተሪ አያልቅምና ያልሠሩትን ወንጀል ሲያሸክሟቸውና ሲያጥላሉዋቸው እንሰማ ይሆናል። ስለዚህም ከሚዲያ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ልሳን የሆኑ ሚዲያዎችን ብቻ እንከታተል።
2. መንግሥት ይህን መሰል አንገት ሰባሪና ድፍረት የተሞላበት ድርጊት ሲፈፅምም ብፁዕነታቸው ያሉበትን ኃላፊነት ከግምት አላስገባም። ክብራቸውን የሚወክሉትን ቤተ ክርስቲያንና ሕዝባቸውን አላከበረም። በዚህ ጸያፍ ድርጊቱ እርሳቸውን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኝን እንዳሳዘነ መታወቅ አለበት።
3. ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ፓትርያርኩን ሸክም ጎንበስ ብለው የሚሸከሙ አባት ናቸው። የዛሬው የመንግስት ድርጊት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ከሜዳው በማግለል የቅዱስ ሲኖዶስን ማዕከላዊነት የመናድ ሙከራ ነው።
4. ብፁዕነታቸው በእምነታቸው የማይደራደሩ ታላቅ አባት ሲሆኑ እርሳቸውን ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ የማድረግ ርምጃ የቤተ ክርስቲያንን በር የበግ ለምድ ለለበሱ ተኩላዎችና ለእንደ ልቡዎች ክፍት የማድረግ ዕቅድ አካል ነው። ከዚያም ውጪ ሌሎች ውጪ የሚኖሩ አበው ብፁዓን አባቶችንም አፍ የማስያዣ አካሄድ ነው።
5. በሌላ በኩል በውጪ ያሉ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ቁጣቸውን ማሳደር አለባቸው። ምክንያቱም መንግሥትም ሆነ ሕገ ወጥ አካላት በተለያዩ ሚዲያዎች በኩል ይህን ነገር እያራገቡ ጫና ፈጥረው ሌላ ሲኖዶስ እናቋቁም የሚል ሀሳብ እንዲፈጠር መሥራታቸው አይቀርምና በዚህ በኩል ረጋ ብሎ መጠንቀቅ ተገቢ ነው። ተተኪ ጸሐፊ ይመረጥ የሚል ሤራ እንዳይሸርብም ነቅቶ መጠበቅና መሥመር ማስያዝ እንደሚገባው ሳይረሳ!!
6. ይህ ድርጊት ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል የታሰበ እቅድ ነው። ስለዚህም እንደ ምእመን በበለጠ የቤተ ክርስቲያን አንድነት ላይ ማተኮርና ቤተ ክርስቲያናችንን በንቃት መጠበቅ አለብን።
7. ይሄ ጉዳይ መሥመር እንዲይዝ የሚያደርጉ አባቶችን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ ማገዝና ትዕዛዛቸውንም እንደ ልጅ መፈጸምም ይገባናል።
ልዑል እግዚአብሔር ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን
#ኢንፈርህሞተ
#ሞትንአንፈራውም
ብርሃኑ ተ/ያሬድ
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 4 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month ago