Women in uniform

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

Description
Subscribers

We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 week, 1 day ago

The first Telecom operator in Ethiopia https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 2 weeks, 2 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 week, 2 days ago

1 day, 13 hours ago
ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
3 days, 13 hours ago

#_ታላቅ_የንግሥ_በዓል_ጥሪ_በወይን_አምባ_ማርያም!

#_ሰኞ_ግንቦት_21_ቀን!

ሼር በማድረግ ለእመቤታችን ልጆች አዳርሱ!

የወለላይቱ እመቤት ልጆች ሰኞ ግንቦት 21 ቀን በወይን አምባ ማርያም የእመቤታችን በደብረ ምጥማቅ የመገለጧ ዓመታዊ በዓል እንደተለመደው በደማቅ ሁኔታ ይከበራል። በዚህ ቀን የእመቤታችን እና የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ታቦታት ወጥተው ሕዝቡን ይባርካሉ።

የእመቤታችን እና የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ታቦታት ወደ መንበረ ክብራቸው ከገቡ በኋላ ሰፊ የእመቤታችን ዝክር አለ። ስለዚህ መጥታችሁ ከበዓሉ ረድኤትን፣ ከጥምቀቱ ፈውስን፣ ከዝክሩ በረከትን ተቀበሉ።

#_የትራንስፖርት_መምጫው

ከየትኛውም አቅጣጫ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ሠፈራ ብላችሁ በባጃጃ ተሳፍራችሁ፣ ድልድዩን እንደተሻገራችሁ አስፓልቱ ጫፍ ላይ ቤተ ክርስትያኗ ትገኛለች።

👉 ከመገናኛ ቀጥታ ወይን አምባ ማርያም የሚል ታክሲ አለ ተሳፍራችሁ ቤተ ክርስቲያኗ በር ላይ ያወርዳቹኃል።

👉 ከመገናኛ በቀጥታ ጎሮ ብለው ተሳፍረው፣ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ከዚያ ባጃጅ ተሳፍረው፣ ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ላይ ስትወርዱ ትገኛለች፡፡

👉 ከሲ አምሲ፣ ከአያት፣ ከሰሚት የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ወርደው ትገኛለች፡፡

👉 ከቃሊቲ፣ ከቱሉ፣ ዲምቱ፣ ከኮዬ ፈጩ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው ከዚያ በባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ወርደው ጫፍ ላይ ትገኛለች፡፡

ግንቦት /17/15 ዓ.ም
አዲስ አበባ

1 week, 1 day ago

https://youtu.be/BLKYRhPz1Cw

YouTube

ደም እየፈሰሰኝ ማህጸንሽ ይውጣ ተብዬ እመቤታችን ከማህጸኔ ዕጢ አወጣችልኝ!

1 week, 2 days ago

https://youtu.be/eVxwPbr_Gg4

YouTube

ለ 200 መቶ ዓመታት የተገበረ ቦረንትቻ! እኔ በኃይለ ሥላሴ ዘመን ነው የተቀበልኩት! ቤተሰቡን ገደለ አመሰቃቀለ!

1 week, 3 days ago

https://youtu.be/S7663dXjnFw

YouTube

ግንቦት 9 የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ዓመታዊ የዝክር በረከት!

2 weeks, 4 days ago

https://youtu.be/YP2ZO9keD-0

YouTube

የግንቦት አንድ የልደታ ማርያም የዝክር በረከት!

3 weeks ago

https://youtu.be/yPCdlgtBqs8

YouTube

በበዓለ ሃምሳ የአምልኮት ስግደት መስገድ ይቻላል ወይ? ሥጋዊ እና የክፉ መናፍስት ውጊያ ያለበት ሰው በበዓለ ሃምሳ እንዴት ነው መስገድ ያለበት? ወዘተ ...

3 weeks, 4 days ago

#_ታላቅ_የንግስ_በዓል_ጥሪ_በወይን_አምባ_ማርያም!

#_ሚያዝያ_30_ሰኞ_ዕለት

የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ በዓለ እረፍት እና የወይን አምባ ማርያም ቅዳሴ ቤት!

ሼር በማድረግ ላልሰሙት አሰሙ አዳርሱ!

የወለላይቱ እመቤት ልጆች ተአምረኛው፣ ፈዋሹ፣ ጌታን ያጠመቀው መጥምቀ መለኮት የተባለው የቅዱስ ዮሐንስ ታቦቱ በወይን አምባ ማርያም አለ። ብዙዎች በተአምረኛ ጸበሉና እምነቱ እየዳኑ ነው።

ሚያዝያ 15 ቀን መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የከበረችው አንገቱ 15 ዓመት ዓለምን ዞራ ወንጌልን አስተምራ በክብር ያረፈችበት ዕለት ነው። እንዲሁም የተአምረኛዋ የወይን አምባ ማርያም ቅዳሴ ቤቷ ነው። የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ የከበረችው አንገቱ ያረፈችበትን ዕለት ለበዓሉ እንዲመች ሚያዝያ 30 ሰኞ በዕለተ ቀኑ ይከበራል።

ሚያዝያ 30 ሰኞ የመጥምቀ መለኮት እና የእመቤታችን ታቦቶች ወጥተው ሕዝቡን ይባርካሉ። ስለዚህ መጥታችሁ ከበዓሉ ረድኤት፣ ከጥምቀቱ ድህነት፣ ከዝክሩ በረከት ተካፈሉ!

#_የትራንስፖርት_መምጫው

ከየትኛውም አቅጣጫ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ሠፈራ ብላችሁ በባጃጃ ተሳፍራችሁ፣ ድልድዩን እንደተሻገራችሁ አስፓልቱ ጫፍ ላይ ቤተ ክርስትያኗ ትገኛለች።

ከመገናኛ በቀጥታ ጎሮ ብለው ተሳፍረው፣ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ከዚያ ባጃጅ ተሳፍረው፣ ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ላይ ስትወርዱ ትገኛለች፡፡

ከመገናኛ ቀጥታ ወይን አምባ ማርያም ብላችሁ መሳፈር ትችላላችሁ።

ከሲ አምሲ፣ ከአያት፣ ከሰሚት የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ወርደው ትገኛለች፡፡

ከቃሊቲ፣ ከቱሉ፣ ዲምቱ፣ ከኮዬ ፈጩ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው ከዚያ በባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ወርደው ጫፍ ላይ ትገኛለች፡፡

ማያዝያ 25-8-15 ዓ.ም

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

አዲስ አበባ

3 weeks, 5 days ago

#ክፉኛ_የዝሙት_አጋንንትና_የዝሙት_ፈተና_በአረጋዊ_መንፈሳዊ_

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም!

ሼር በማድረግ ለወዳጆ አዳርሱ!

ተወዳጆች ሆይ በመጻሕፍተ መነኰሳት በአረጋዊ መንፈሳዊ ላይ ስለ ዝሙት አጋንንት ክፉኛ ፈተና ተጽፏል። ለአንባቢ እንዲመች ይዘቱን ሳይለቅ አቀራረቡን ብቻ ጥቂት በመቀየር፣ ትንሽ በመጨመር አቅርቤዋለሁ።

ከአጋንንት ሁሉ ይልቅ የዚህ የሰይጣን ዝሙት ፈተናው ቡዙ ነው። የዝሙት አጋንንት ሕዋሳታችንን የሚያዝልበት ጊዜ አለ። ልቦናችንን የሚለውጥበት ጊዜ አለ። ሕሊናችንን የሚሰውርበት ጊዜ አለ። ሰውነታችንን ማዘዝ የማንችልበት ጊዜ አለ። ከጸጋ ስጦታ ለይቶ ኅሊናችንን ይለውጣል። ተኝተን ሳለን በዝሙት የሚዋጋን ጊዜ አለ።

የዝሙት አጋንንትን አመጣጡን እንወቅበት። በምን እናውቃለን? ካልን የዝሙት እሳቱ በፊታችን ላይ እንደ እሳት ብልጭ ይልብናል። የዝሙት አጋንንት ሲመጣ ድንግጥ ድንግጥ እንላለን። የዝሙት አጋንንት ሲፈትነን ጸሎታችን፣ ስግደታችን ይከብደናል። እንዳንጸልይ እንዳንሰግድ ከባድ አድርጎ ያሳየናል።

የዝሙት አጋንንት ሲፈትነን ጸሎታችንን የአምልኮት ስግደታችንን ትተን ወይም አቋርጠን እንተኛለን። ቆመን ተኝተን ሕዋሳታችንን እንዳብሳለን። እግራችንን እናፋትላለን። ነገር ግን ታግሰን ብንጸልይ የእግዚአብሔር መልአክ ይረዳናል። ብንጸልይ ብንሰግድ ብንተጋ ፈተናው ይቀልልናል ይርቅልናል።

እነዚህ የዝሙት አጋንንት የፈተና ምልክቶች እያሉብን ያለ ጸሎትና ያለ ስግደት መተኛት የለብንም። ያለ ጸሎት ያለ ስግደት ብንተኛ ጠባቂ መልአክ ይርቀናል የዝሙት አጋንንት ቀርቦ ይፈትነናል።

የዝሙት አጋንንት በዓይን ይገባል። በዓይን ሲገባ ወደ ሰውነታችን ገብቶ በመቆጣጠር ሕዋሳችንን በእጅ እንድናሽ ያደርገናል። /ይህ አባባል ግለ ወሲብ እንድንፈጽም ያደርገናል ለማለት ነው/ የዝሙት አጋንንት እንዲህ ሲፈትነን በክርስቶስ ኃይል እናማትብበት።

ወደ ተግባረ ዝሙት እንዳይከተን በርትተን መጸለይ መስገድ አለብን። ይህን ካለደረግን የዝሙት አጋንንት ወደ አባለ ዘር ገብቶ ያለ ርህራሄ በዝሙት ፈተና ያስጨንቀናል በዝሙት ይጥለናል።

የዝሙት አጋንንት ሰዎችን እንደ ጊንጥ ይነድፋሉ። ቆመንም ቢሆን፣ ተቀምጠንም ቢሆን፣ ሥራም በያዝንበት ጊዜም ቢሆን የዝሙት ስሜት ቢያነሳሳብን በሕሊናችን እንጸልይ እንገስጸው።

ከወትሮ ይልቅ አብዝተን ስንበላ ስንጠጣ የዝሙት ፆር ይጸናብናል። አብዝቶ መብላት መጠጣት እና እላፊ መተኛት የዝሙት አጋንንትን ያቀርበዋል። አብዝተን ስንበላ ስንጠጣ ያኔ የዝሙት አጋንንት ሊዋጋን እንደቀረበ እንወቅ። ሰውነታችንን ለዝሙት ካነሳሳ ያኔ የዝሙት አጋንንት እንደሰለጠነብን እንወቅ።

ወዳጆቼ ብዙዎቻችንን ከንስሐ መንገድ ያራቀን፣ ክብራችንን ቅድስናችንን ያስጣለን፣ ከዓለማዊ እስከ መንፈሳዊ፣ ከምዕመን እስከ አባቶች እናቶች፣ በአምልኮት ሕይወት ከጸኑት፣ በቅዱስ ቁርባን እስከ ተወሰኑት ወዘተ የዝሙት አጋንንት እየፈተነን በቀላሉ እየጣለን ነው። በዚህም ቅድስና ከሕይወታችን ርቋል።

ከዝሙት አጋንንት የሸሸ እግዚአብሔርን ይከተላል። ከዝሙት አጋንንት የሸሸ ጸጋና በረከቱን ይዞ ይኖራል። ከዝሙት አጋንንት የሸሸ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በማዕረግ ያገባል። ከዝሙት አጋንንት የሸሸ ንጽሕናውን ቅድስናውን ይጠብቃል። ከዝሙት አጋንንት የሸሸ ከርኩሰት ይሸሻል። ከዝሙት አጋንንት ሸሽቶ፣ ወደ እግዚአብሔር ተጠግቶ የሚኖር ሰማያዊ ሽልማት ያገኛል። ከዝሙት አጋንንት እና ከዝሙት እንሽሽ። ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ "ከዝሙት ሽሹ" ያለን። /1ኛ ቆሮ 6፥ 18/

እጅግ በጣም የገረመኝ አረጋዊ መንፈሳዊ "የሰይጣናት ተንኮላቸውን እናገር ዘንድ ከምን ተችሎኝ ላልፈጽመው" በማለት ገና ያላወቅናቸው ነገር ግን በወጥመዱ የተያዝንባቸው፣ በሴራው የወደቅንባቸው ተንኮሎቹ እንዳሉ ይነግረናል።

እኛ ግን ስለ ጥንተ ጠላታችን ከገነት ስላስወጣን፣ ከእግዚአብሔር ስለለየን፣ ከዘላለማዊ መንግሥቱ እንድንባረር ስላደረገን ሰይጣን ተንኮሉ ሴራው ውጊያው ሲነገረን ስለ ሰይጣን የተሰበክን መስሎን እንጃጃላለን። ስለ ጠላታችሁ ንቁ እወቁ ሲባሉ ሰይጣን ለምን ተነካ የሚሉ አሉ።

ቅዱስ ጴጥሮስ ግን "ባላጋራችሁ ዲያቢሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና" በማለት ውጊያው ቀላል እንዳልሆነና የማንጸልይ፣ የማንሰግድ፣ ቅዱስ ቁርባን የማንቀበል ከሆነ እንደ አንበሳ፣ በሕይወታችን እያገሳ ስንት ነገራችንን እየነሳ ይኖራል። /1ኛ ጴጥ 5፥8/

ወዳጆቼ ዲያቢሎስ "ፈልጎ እንደሚያገሳ" መባሉን ልብ በሉ። እኛ ባንፈልገውም እሱ ፈልጎ ይዋጋናል። የመንፈሳዊ የጦር ዕቃዎችን ማለትም ጸሎት፣ ስግደት ወዘተ የማያነሳ ሰው ላይ እንደ አንበሳ መሆኑን አንርሳ።

ሚያዝያ 24-8-15 ዓ.ም

አዲስ አበባ

1 month ago

በነገራችን ላይ ብዙዎች በዝሙት የሚፈተኑት መጠጥ በመጠጣት የሚጠመዱት በኃጢአትም የሚወድቁት በዚህ በበዓለ ሃምሳ ነው፡፡ በዚህ በበዓለ ሃምሳ ጾም የለ አርብ ረቡዕ የለ እንደልብ ይበላል ይጠጣል፡፡

እንደ ልብ ያገኘነውን ስንበላ ስንጠጣ ደማችን ይሞላል ሥጋችን በምቾት ይደላደላል፡፡ ደማችን ሞላ ሥጋችን ተመቸው ማለት ሥጋችን ሉጋም የሌለው ፈረስ ይሆናል፡፡

በተለይ ጾም ስግደት ለሥጋችን ሉጋም ነው፡፡ ሥጋን በኃጢአት እንዳይወድቅ አስሮ ይይዛል፡፡ ጾም ተፈታ ማለት የሥጋ ሉጋምም አብሮ ስለሚፈታ በቀላሉ በኃጢአት እንወድቃለን፡፡

አምስተኛ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ለሚፈትኑን ክፉ መናፍስት በር እንከፍታለን፡፡ በዓብይ ጾም በርትተን ተግተን ነገር ግን በበዓለ ሃምሳ በኃጢአት ብንወድቅ ጠላቶቻችን በድካማችን በኃጢአታችን ምክንያት ተደራጅተው ወደ ሕይወታችን ይገባሉ ክፉኛም ይፈትናሉ፡፡

ለምሳሌ አንድ ጎበዝ ምዕመን በጾም በጸሎት በስግደት እራሱን ከዝሙት ጠብቆ ነገር ግን በበዓለ ሃምሳ ዝሙት ቢፈጽም ሁለት ነገር ይገጥመዋል፡፡ አንደኛው በኃጢአት መውደቅ ሲሆን ሁለተኛው ዝሙት በመሥራቱ የዝሙት አጋንንት ይገባበታል፡፡ ከዛማ የዝሙት አጋንንት ይቆጣጠረዋል በተደጋጋሚ እራሱን መቆጣጠር እስኪያቅተው ድረስ በዝሙት ይወድቃል፡፡

በበዓለ ሃምሳ አንድ ሰው በኃጢአት ቢወድቅ ንስሐ መግባት ካልቻለ ወይም ንስሐ ገብቶ ቀኖና መቀበል ላልቻለ ሰው ምን መፍትሔ አለው ለሚለው ሦስተኛው መፍትሔ ምጽዋት ነው፡፡

የእግዚአብሔር ልጆች እኛ ከበደላችን የዳንነው በጌታችን በአካሉ ምጽዋትነት ነው፡፡ ይህም ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ነው፡፡ ይህ ለእኛ ለሰው ልጆች ከጌታ በነፃ የተመጸወትነው ነው፡፡
ምጽዋት ሥርየተ ኃጢአትን ታሰጣለች ሞትንም ታርቃለች፡፡
ስለዚህ
በዚህ በበዓለ ሃምሳ ስለሠራነው ኃጢአት ለነደያን በመመጽወት እግዚአብሔር ስርየት እንዲሰጠን መለመን ነው፡፡ ካህናትም ንስሐቸውን ተቀብለን ቀኖናቸውን ወደ ምጽዋት መቀየር ነው፡፡

አቅማቸውን ባገናዘበ መልኩ በምጽዋታቸው ለነደያን ለተጎዱ ገደማት ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት እና በገዳም ተወስነው ለሀገራችን ለሚጸልዩት እናት አባቶች በጎ ነገር እንዲያደርጉ ማዘዝ ነው፡፡

ለተጎዱ ቤተ ክርስቲያን ከሆነ መቀደሻ ለብሰ ተክህኖ መጎናጸፊያ ዕጣን ዘቢብ ጧፍ መጻሕፍት ወዘተ ገዝተው እንዲሰጡ ማድረግ ነው፡፡ ምዕመናንም እኛ እንግዛላችሁ እኛ እንስጥላችሁ በማለት ምጽዋቱን አምጡ ከሚሉ አባቶች ተጠበቁ፡፡

እነሱ ይዘዝዋችሁ እናንተ ደስ ላላችሁ ተጎዳ ላላችሁ ቤተ ክርስቲያን ንዋየ ቅድሳቱን ገዝታችሁ ስጡ፡፡ በተረፈ የነፍስ ነፃነት እንዲሰማን ከበዓለ ሃምሳ በኃላ ንስሐ መግባት እንችላለን፡፡

የእግዚአብሔር ልጆች ንስሐ ጸጸት ለቅሶ ቁጭት ጾም ስግደት ስላለው በበዓለ ሃምሳ ደግሞ ለቅሶ ሐዘን ጾም ስግደት ስለሌለ በአጭሩ ንስሐ ገብተን ግን ቀኖና መቀበል ስለማንችል በበዓለ ሃምሳ ሰይጣን የበቀል ጦሩን የኃጢአት ዘግሩን ይዞ እንዳይነሳ አንስቶም በኃጢአት እንዳይጥለን ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡

በበዓለ ሃምሳ መብልን በተመለከተ የአባቶቻችን ልምዳቸው ምን ይመስላል? እኛስ ከእነሱ ምን እንማር? የሚለው ስናይ
በበዓለ ሃምሳ እንደ ልባችሁ እንዳሻችሁ ብሉ ጠጡ ሳይሆን ጸማችሁን አትዋሉ፣ በአግባቡ በመጠኑ ብሉ ነው የተባልነው፡፡

በገዳም በጾም በጸሎት በስግደት የሰነበቱ አባቶች በዓለ ሃምሳ ሲመጣ ብዙ ትሩፋት ቢቀርባቸውም ጾምን በተመለከተ ግን እንደ ጸጋቸው የራሳቸውን ዘዴ ይጠቀማሉ፡፡

አንዳንድ አባቶች በልቶ ጠጥቶ ከሚመጣ ሥጋዊ ኃጢአትና ፈተና እራሳቸውን ለመጠበቅ እና ከሰይጣን ለመራቅ ሃምሳውንም ቀን ጥሬ በመብላት የሚሰነብቱ አሉ፡፡

በቀን አንዴ ወይም ጠዋት ተመግበው ከሃያ አራት ሰዓት በኃላ የሚመገቡ አሉ፡፡ የራሳቸውን ፈንታ ለነደያን ሰጥተው ነደያንን አጥግበው እነሱ ከነደያን የተረፈውን የሚመገቡ አሉ፡፡

ጠዋት ተመግበው ምሳን ትተው እራትን ብቻ የሚመገቡ አሉ፡፡ ሰንበትን ላለመሻር ብቻ ረፋድ ላይ በልተው በዛው የሚያድሩ አሉ፡፡ በጥቂቱ ብቻ መጥነው በመብላት የሚሰነብቱ አሉ፡፡

ወዳጆቼ እነዚህ ሁሉ በዓለ ሃምሳን እንዳቅማቸውና እንደ ጸጋቸው በመመገብ በዓለ ሃምሳን ከጾም ባልተናነሰ ሁኔታ የሚያሳልፉ አሉ፡፡
እኛ በዓለም የምንኖር በመሆኖችን አመጋገባችን እንደ እነሱ ባይሆንም ሥጋችንን በውፍረት እያደላ ደማችንን እየሞላ በዝሙት ተላላ ከሚያደርገን አመጋገብ ተጠንቅቀን በመጠኑ ብንመገብ ክፋት የለውም፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ወንድሞች ሆይ መጠራታችሁና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና›› በማለት በዓብይ ጾም የነበረንን ትጋት በበዓለ ሃምሳ ብንደግመው ከኃጢአት ውድቀት እና ከክፉ መናፍስት ጥቃት እንጠበቃለን፡፡ በእግዚአሔር ዘንድ ያለንን መጠራት እና መመረጥ እናጸናለን፡፡ /በ2ኛ ጴጥ 1÷10/

አይ በዓለ ሃምሳ የተድላ የደስታ ጊዜ ነው በማለት እላፊ በመብላት ሥጋዊ ምቾትን ብቻ በመሻት በተሳሳተ ትምህርት እንደፈለግን ብንሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ያለንን መጠራት እና መመረጣችንን እናጣለን ቅዱስ ጴጥሮስም እንዳለን እንሰናከላለን፡፡

በተረፈ ይህን ትምህርት ሰምታችሁ ንስሐ መግባት የምትፈልጉ በዘረዘርኩላችሁ መንገድ ንስሐ ግቡ የአመጋገብ ሥርዓታችሁን አስተካክሉ፡፡

We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 week, 1 day ago

The first Telecom operator in Ethiopia https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 2 weeks, 2 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 week, 2 days ago