Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net

Description
“እውነት ለሁሉ” በዓለም ዙርያ በሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ክርስቲያኖች የተመሠረተ ድረ-ገፅ ሲሆን እስልምናንና ክርስትናን የተመለከቱ መጣጥፎችን፣ መጻሕፍትን፣ ዜናዎችንና የመሳሰሉትን ያስነብባል፡፡ የኦዲዮና የቪድዮ መረጃዎችንም ያቀርባል፡፡ የበለጠ ለማወቅ http://www.ewnetlehulu.org ይጎብኙ።
Advertising
We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month, 2 weeks ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 4 days, 23 hours ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 5 months, 1 week ago

2 weeks ago
2 weeks, 3 days ago

ልጅ ኢብን አባስ ሲፈስረው "..በአላህ ሃይማኖት (እስልምና) እና በግልፅ ማስረጃዎች የተመራ.." (rightly #guided by means of allah's #religion and clear proof) በማለት ነው የፈሰረው። በዚህ አንቀጽ ላይ #የተመሩ ተብሎ የተተረጎመው የአረብኛ ቃል فَهَدَىٰ /ፋሃዳ/ ሲሆን በሱራ 93:7 ላይ #መራህ ተብሎ የተተረጎመው ቃል ነው። ስለዚህ ይህ فَهَدَىٰ /ፋሃዳ/ የሚለው ቃል በእስልምና ውስጥ መሆንን፥ በተውሒድ ማመንን የሚያመለክት ቃል መሆኑን ከዚህ በቀላሉ ማረጋገጥ እንችላለን።

ሌላ ምሳሌ፦

"ፀሐይንም በወጣች ጊዜ ከዋሻቸው ወደ ቀኝ ጎን ስታዘነብል ታያታለህ፡፡ በገባችም ጊዜ እነርሱ ከእርሱ በሰፊው ስፍራ ውስጥ ኾነው ሳሉ ወደ ግራ በኩል ትተዋቸዋለች፡፡ ይህ ከአላህ ተዓምራቶች ነው፡፡ አላህ #የሚያቀናው ሰው ቅኑ እርሱ ብቻ ነው፡፡ የሚያጠመውም ሰው ለርሱ አቅኝን ረዳት አታገኝለትም፡፡" ሱራ 18:17

በዚሁ አንቀጽም እንዲሁ አላህ ሰዎችን የሚያቀናው እርሱ መሆኑን ሲናገር እንመለከታለን። በዚህ ምዕራፍ ላይ አላህ ከስሩጉ ዮሴፍ (Joseph of Serugh) ልቦለዳዊ ስራ የተኮረጀውን የዋሻው ውስጥ ተኚዎች (cave sleepers) ታሪክ ይናገራል። ሙሉ ምዕራፉ እንዴት የተወሰኑ ሙስሊሞች ወደ ዋሻ እንደገቡና ለሶስት መቶ አመት እንደቆዩ የሚናገር ሲሆን በዚህኛው አንቀጽ ላይ (ቁ.17) ታሪኩን ከተናገረ በኋላ አላህ የሚያቀናው ሰው ቅኑ እርሱ ብቻ እንደሆነ ይናገራል። ኢብን አባስ በዚህ አንቀጽ ላይ "..የሚያቀናው.." የሚለውን ቃል ሲተረጉመው "..አላህ ወደ ሃይማኖቱ (እስልምና) የሚያቀናው.." ( #guides him to his #religion) በማለት ነበር የተረጎመው። በዚህ አንቀጽ ላይ #የሚያቀናው ተብሎ የተተረጎመው የአረብኛ ቃል فَهَدَىٰ /ፋሃዳ/ የሚለው ሲሆን በሱራ 93:7 ላይ #መራህ ተብሎ የተተረጎመው ቃል ነው። ስለዚህ ይህ فَهَدَىٰ /ፋሃዳ/ የሚለው ቃል አላህ በገለጸው አሃዳዊው መንገድ ውስጥ መሆንን፥ በተውሒድ ማመንን የሚያመለክት ቃል መሆኑን ከዚህ መረዳት እንችላለን።

ሌላ ምሳሌ፦

"ቀጥተኛውንም መንገድ #መራናቸው" ሱራ 37:118

በዚህ አንቀጽ ላይ አላህ የተባለው ገጸ-ባህርይ ለሙሳና ለሀሩን ያደረገውን ነገር ሲናገር እንመለከታለን። በእነርሱ ላይ ጸጋን እንደለገሰ፥ እነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም ከታላቅ ጭንቅ እንዳዳነ፥ እንደረዳቸው፥ አሸናፊዎች እንደነበሩ፥ በጣም የተብራራውንም መጽሐፍ እንደሰጣቸውና ቀጥተኛውንም መንገድ እንደመራቸው ይናገራል። የመሐመድ የአጎት ልጅ የሆነው ኢብን አባስ በዚህ አንቀጽ ላይ የሚገኘውን "..መራናቸው.." የሚለውን ቃል ሲተረጉመው  "..በእውነተኛውና በቀጥተኛው ሃይማኖት (እስልምና) ላይ አጸናናቸው.." (we #confirmed them on the true, straight #religion (islam) በማለት ነበር የተረጎመው። በዚህ ቦታ ላይ #መራናቸው ተብሎ የተተረጎመው የአረብኛ ቃል وَهَدَيْنَاهُمَا /ዋሃዳይናሁማ/ የሚል ሲሆን ሱራ 93:7 ላይ #መራህ ተብሎ ከተተረጎመው فَهَدَىٰ /ፋሃዳ የአረብኛ ቃል ጋር አንድ ስረወ-ቃል (root word) የሆነ ቃል ነው። ስለዚህ ይህ ቃል በእስልምና ውስጥ መሆንን፥ በ በተውሒድ ማመንን የሚያመለክት ቃል መሆኑን ከዚህ በቀላሉ ማረጋገጥ እንችላለን።

✍️ ስለዚህ በሱራ 93:7 ላይ የሳትኽም ሆነህ ሳለህ መራህ ማለት፥ ጣዖት አምላኪ ሆነህ ሳለ ወደ ቀጥተኛው መንገድ መራህ ማለት ነው። ስተህ፥ በጥመት ውስጥ ሳለህ ወደ ተውሒድ መንገድና እምነት ተመራህ ማለት እንደሆነ ጥርጥር የለውም። ይህ መሐመድ በቀድሞው ዘመኑ ጣዖት አምላኪ እንደነበር በግልጽ ያሳያል

👉 ይህንን የቁርአን አንቀጽ የተረጎሙ የቁርአን ተርጓሚያን፥ በእርግጥም መሐመድ ስቶ እንደነበርና፥ በኋላ ላይ ወረደለት የተባለለትን ትዕዛዝ (ተውሒድን) ይቃረን የነበረ ጣዖት አምላኪ እንደነበር መዘገባቸው በእርግጥም ይህ ሀሳዊ ነብይ ጣዖት አምላኪ የነበረ ለመሆኑ ተጨማሪ ማስረጃ ነው፦

"And did He not find you #erring, from the [ #revealed ] Law which you [ #now ] #follow, and guided you?, that is, and then #guided you #to #it."

[Tafsir Al Jalalayn 93:7]

ሁለቱ ጀላላዎች ይህን የቁርአን አንቀጽ ባብራሩበት ተፍሲራቸው ላይ፥ "..የሳትኽም ሆነህ አገኘህ.." የሚለውን አንቀጽ ሲያብራሩት፥ አሁን ላይ ከተገለጠልህ ሕግ ስተህ እና ጠምመህ በነበርህበት ዘመን አገኘህ ወደ እርሱም (አሁን ወደምትከተለው ሕግ) መራህ ማለት እንደሆነ ገልጸዋል። መሐመድ ነብይ ነኝ ብሎ ከተነሳ በኋላ የተገለጠለት ሕግ የተውሒድ እምነት ነው (ሱራ 112:1-4) ስለዚህ ስቶ በነበረበት ሰዓት ተቃርኖ እና ጠምሞ የነበረው በኋላ ላይ ተገለጠልኝ ካለው ከተውሒድ እምነት ነበር ማለት። እንደ እስልምና አስተምህሮ ደግሞ የተውሒድ ተቃራኒ ሽሪክ (አጋሪ ወይም ጣዖት አምላኪ መሆን) ነው። ስለዚህ መሐመድ ከተውሒድ ውጪ የነበረ አጋሪና ጣዖት አምላኪ ነበር ማለት ነው።

"Gabriel then said: (Did he not find thee) o #muhammad (wandering) #among #people in #error (and direct thee) and guided you by means of prophethood? The prophet (pbuh) said; yes, o Gabriel"

[Tafsir Ibn Abbas 93:7]

ከሁለቱ ጀላላዎች በተጨማሪ የሀሰተኛው ነብይ የመሐመድ የአጎት ልጅ፥ ኻብራል ኡማ (የኡማው/የሙስሊሙ ማህበረሰብ ብርዕ) ሳላፍ (ከመሐመድ የመጀመሪያ ተከታዮች አንዱ) የሆነው የቁርአን ተንታኝ (ሙፈሲር) ሱራ 93:7 ላይ "..የሳትኽም ሆነ አገኘህ.." ማለት ከሳቱ (አጋሪ ወይም ጣዖት አምላኪ ከሆኑ) ሰዎች መካከል ሆነህ ሳለህ ማለት ነው በማለት መሐመድ ከጣዖታዊያኑ አንዱ የነበረ መሆኑን አንቀጹ እንደሚናገር ግልፅ አድርጓል። በኢብን አባስ ተፍሲር መሰረት መሐመድ ከሳቱ ሰዎች መካከል የነበረ ቢሆንም፥ በኋላ ላይ አላህ ወደ ተውሒድ እንደመራው ገልጿል። ስለዚህ መሐመድ ጣዖት አምላኪ ነበር ማለት ነው። እሱ ከሳቱ ሰዎች ጋር አብሮ ይኖር ነበር እንጂ ስቶ አልነበረም ብሎ መከራከር አይቻልም። ምክንያቱም ሱራ 93:7 ".. #የሳትኽም ሆነህ ሳለ.." በማለት የሳተው ወይም ጣዖት አምላኪ የነበረው መሐመድ መሆኑን ግልጽ ያደርጋል። ራሱ ሳይስት፥ በሳቱ ሰዎች መካከል ስላለ ብቻ ስተህ ነበር አይባልምና። ይህ የሙስሊሞች ነብይ ጣዖት አምላኪ እንደነበር ያለ ምንም ብዥታ ያረጋግጣል።

✍️ በቀጣዩ ክፍል ይህ ሀሰተኛ ነብይ ነብይ ነኝ ብሎ ከመነሳቱ በፊት ጣዖት አምላኪ እንደነበር የሚያሳዩ ተጨማሪ ማስረጃዎችን እንመለከታለን

▶️ ይቀጥላል

2 weeks, 3 days ago

♦️ ጣዖት አምላኪው መሐመድ (ክፍል 1)

ሙስሊሞች ሀሰተኛው ነብያቸው መሐመድን እንደ አርአያና እንደ መልካም መከተል ያዩታል። በተጨማሪም ነብይ ከመሆኑ በፊትም አላህን ያመልክ ነበር በማለት ይናገራሉ። ነገር ግን ቁርአንን እና እስላማዊ ምንጮችን ስንመረምር፥ መሐመድ "ነብይ" ከመሆኑ በፊት ፍጹም ጣዖት አምላኪ እንደነበር  እንረዳለን። መጽሐፍ ቅዱስ ጣዖት አምልኮን የሚቃወም ሲሆን፥ ይህን ተግባር የሚፈጽሙ ሁሉ የዘላለም ሞት እንደሚጠብቃቸው ይናገራል (ራዕ 21:8) ቀጥለን በማስረጃ እንደምንመለከተው፥ ሀሰተኛው ነብይ መሐመድ ይህን ሃጢያት ይፈጽም እንደነበር እንረዳለን

መረጃዎቹ እነሆ፦

" #የሳትክም ኾነህ አገኘህ መራህም፡፡ " ሱራ 93:7

በዚህ ሱራ ላይ አላህ ለመሐመድ ያደረገለትን ነገር ሲዘረዝር እንመለከታለን። አላህ ካደረገለት ነገሮች አንዱ፥ መሐመድን ከሳተበት መምራቱ ነው። በዚህ ስፍራ "ሳትኽ" ተብሎ የተተረጎመው የአረብኛው ቃል َالًّا /ዳለን/ የሚል ሲሆን "ወደ ጥመት የሄደ፥ በአላህ ግልጽ የተደረገውን አህዳዊውን፥ ቀጥተኛውን መንገድ በመተው ወደ ጥመት የሄደ" ማለት ነው

[ A word for word meaning of the quran vol 3, page 1964 and 1999 ]

በቁርአን ውስጥ ይህ ቃል ከአላህ ውጪ ሌሎች ጣዖታትን የሚያመልኩ ሰዎችን ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለ ቃል ነው። ለናሙና ያህል ጥቂቶቹን እንመልከት፦

"ኢብራሒምም ለአባቱ ለአዘር « #ጣዖታትን አማልክት አድርገህ ትይዛለህን እኔ፤ አንተንም ሕዝቦችህንም በግልጽ #መሳሳት ውስጥ ኾናችሁ አያችኋለሁ» ባለ ጊዜ (አስታውስ)" ሱራ 6:74

በዚህ አንቀጽ ላይ አላህ ኢብራሂም ለአባቱ ለአዘር የእርሱንና የሕዝቦቹን ጣዖት አምላኪነት አስመልክቶ የተናገረውን ነገር ለመሐመድ ሲያስታውሰው እናያለን። ኢብራሂም አባቱና ሕዝቦቹ ጣዖት አምልኮ ውስጥ መሆናቸው ትክክል አለመሆኑን ሲነግረው "..ግልጽ #መሳሳት ውስጥ አያችኋለሁ .." በማለት ነበር የነገረው። የመሐመድ የአጎት ልጅ የሆነውና፥ "ኻብራል ኡማ/የኡማው (የሙስሊሙ ማህበረሰብ) ብዕር ተብሎ የሚታወቀው ኢብን አባስ ይህን አንቀጽ ሲተረጉመው "..መሳሳት.." የሚለውን ቃል "..በግልጽ አለማመንና ጣዖታትን ከማምለክ የተነሳ የተፈጸመ ስህተት.." (in manifest #disbelief and wrong in so #worshiping #idols) በማለት ነው የተረጎመው። በዚህ አንቀጽ ላይ #መሳሳት ተብሎ የተተረጎመው የአረብኛ ቃል፥ ضَالًّا /ዳለን/ የሚለው ቃል ሲሆን በሱራ 93:7 ላይ #የሳትኽም ተብሎ የተተረጎመው ራሱ የአረብኛ ቃል ነው። ይህ በግልጽ ضَالًّا /ዳለን/ የሚለው የአረብኛ ቃል ጣዖት አምላኪነትን፥ ከተውሒድ ውጪ መሆንን ለማመልከት ጥቅም ላይ የሚውል ቃል መሆኑን በማያሻማ አኳሃን ያስረዳል።

ሌላ ምሳሌ፦

"(ሙሳ) አለ፡- ሃሩን ሆይ! #ተሳስተው ባየሃቸው ጊዜ ምን ከለከልህ?" ሱራ 20:92

በዚህ አንቀጽ ላይ አላህ የእስራኤል ልጆች ስተው የወርቁን ጥጃ በማምለክ ጣዖት አምልኮን ስለፈጸሙበት ክስተት ይናገራል። ከቁ.88 ጀምሮ እንዴት የወርቁ ጥጃ እንደተሰራና አምላካችሁ፥ የሙሳም አምላክ ነው እንደተባሉ፥ እነርሱም አምላክ አድርገው እንዲያዙትና እንዳመለኩት ይህ እና ሌሎች የቁርአን አንቀጾች ይናገራሉ (ሱራ 7:148-152 ሱራ 2:51-54 ሱራ 4:153) ከዚያም ሄዶ የነበረው ሙሳ (20:91) ሲመለስ ሃሩንን ተሳስተው ባየሃቸው ጊዜ ምን ከለከለህ በማለት የእስራኤል ልጆች ሲፈጽሙት የነበረውን ጣዖት አምልኮ ጠቁሞ ያወግዘዋል። የመሐመድ የአጎት ልጅ የሆነው ኢብን አባስ በዚህ አንቀጽ ላይ "..ተሳስተው.." የሚለውን ቃል ሲፈስረው "..ከትክክለኛው መንገድ ስተው.." (gone #astray from the #right way) በማለት ነው የፈሰረው። በዚህ አንቀጽ ላይ #ተሳስተው ተብሎ የተተረጎመው የአረብኛ ቃል ضَالًّا /ዳለን/ የሚለው ቃል ሲሆን በሱራ 93:7 ላይ #የሳትኽም ተብሎ የተተረጎመው ራሱ የአረብኛ ቃል ነው። ይህ በግልጽ ضَالًّا /ዳለን/ የሚለው የአረብኛ ቃል ጣዖት አምላኪነትን፥ ከተውሒድ ውጪ መሆንን ለማሳየት ጥቅም ላይ የሚውል ቃል መሆኑን ከዚህ እንረዳለን።

ሌላ ምሳሌ፦

"አላህ በርሱ #የማጋራትን (ወንጀል) አይምርም፡፡ ከዚህም ወዲያ ያለውን ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም #የሚያጋራ ሰው (ከእውነት) የራቀን #መሳሳት በእርግጥ #ተሳሳተ፡፡" ሱራ 4:116

በዚህ አንቀጽ ላይ አላህ የማጋራትን ወንጀል እንደማይምር ሲናገር እንመለከታለን። ከዚህ ወንጀል ወጪ ሌላ ወንጀልን እንደሚምር "..ከዚህም ወዲያ ያለውን ለሚሻው ሰው ይምራል.." በማለት ቢገልጽም በእርሱ ላይ የሚያጋራን ሰው እንደማይምረው ይናገራል። ከዚያም ይቀጥልና "..በአላህም የሚያጋሪ ሰው ከእውነት የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ.." በማለት በአላህ ላይ ማጋራት መሳሳት መሆኑን ይናገራል። ማጋራት ማለት ከአላህ በተጨማሪ ሌሎች አማልክትን ደምሮ ማምለክ ሲሆን፥ በእስልምና አስተምህሮ ከጣዖት አምልኮ ውስጥ የሚመደብ ተግባር ነው። አላህ በዚህ አንቀጽ መሳሳት የሚለው ይህንን ተግባር ነው። በዚህ አንቀጽ ላይ #መሳሳት ተብሎ የተተረጎመው የአረብኛ ቃል፥ ضَالًّا /ዳለን/ የሚለው ቃል ሲሆን በሱራ 93:7 ላይ #የሳትኽም ተብሎ የተተረጎመው ራሱ የአረብኛ ቃል ነው። ልክ እንደ ቅድሙ አንቀጽ ይህኛውንም አንቀጽ የሀሰተኛው ነብይ የመሐመድ የአጎት ልጅ ኢብን አባስ ሲተረጉመው፥ "..መሳሳት.." የሚለውን ቃል "..ከምሪት የሳተ.." (hath #wondered far #astray from #guidance) በማለት ነው የተረጎመው። ስለዚህ እንደ እስልምና አስተምህሮ ከጣዖት አምልኮ አይነቶች አንዱና ዋነኛ የሆነው ማጋራት (ሽርክ) ስህተት ወይም መሳሳት ነው ማለት ነው። ይህ ضَالًّا /ዳለን/ የሚለው የአረብኛ ቃል ተውሒድ ከሚታመንበት ከእስልምና ሃይማኖት ውጪ መሆንን ለመጠቆም ጥቅም ላይ የሚውል ቃል መሆኑን ያረጋግጣል

ስለዚህ በሱራ 93:7 ላይ ለመሐመድ ይህ ضَالًّا /ዳለን/ የሚለው ቃል ስቶ እንደነበር ለመግለጽ ጥቅም ላይ መዋሉ፥ ጣዖት አምላኪ እንደነበር ማረጋገጫ ነው።

▶️ በሱራ 93:7 ላይ ተመስርተን መሐመድ ጣዖት አምላኪ እንደነበር በይበልጥ የምናረጋግጠው፥ ስቶ በነበረበት ሰዓት አላህ "መራህ" በመባሉ ነው

"መራህ" የሚለው የአረብኛ ቃል َهَدَىٰ /ፋሃዳ/ የሚል ሲሆን፥ ከጣዖት አምልኮ፥ ከጥመት ወደ "ቀጥተኛው" መንገድ ወደ ተውሒድ መመራት ማለት ነው።

ለዚህም ከቁርአን ጥቂት ናሙናዎችን እንመልከት፦

"የአላህን መስጊዶች የሚሠራው በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ፣ ሶላትንም በደንቡ የሰገደ፣ ግዴታ ምጽዋትንም የሰጠ ከአላህም ሌላ (ማንንም) ያልፈራ ሰው ብቻ ነው፡፡ እነዚያም #ከተመሩት ጭምር መኾናቸው ተረጋገጠ፡፡" ሱራ 9:18

በዚህ አንቀጽ ላይ አላህ ከሃዲዎች የአላህን መስኪዶች መስራት እንደሌለባቸው ከተናገረ በኋላ እነ ማን የእርሱን መስኪድ መስራት እንዳለባቸው ይናገራል። በዚህ አንቀጽ መሰረት የአላህን መስኪዶች የሚሰራው በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ፥ ሶላትንም በደንቡ የሰገደ፥ የግዴታን ምጽዋት የሰጠ፥ ከአላህ ሌላ ማንንም ያልፈራ ሰው ብቻ መሆኑን ይገልጻል። ከዚያም እነዚህ አይነቶቹ ሰዎች ከተመሩት ጭምር መኾናቸው እንደተረጋገጠ ይናገራል። በዚህ አንቀጽ ላይ "..ከተመሩት.." ተብሎ የተተረጎመውን ቃል የሀሰተኛው ነብይ የመሐመድ የአጎት

2 months, 1 week ago

♦️ ኪሩቤል በሰማይ ለጌታ ለኢየሱስ ይሰግዳሉ!

ከራዕይ 5:8 የምንረዳው እውነት ይህ ነው። በሰማይ ኪሩቤል ለጌታ ለኢየሱስ ይሰግዳሉ። መጽሐፉን ከአባቱ ከእግዚአብሔር አብ ከወሰደ በኋላ በመታረዱና የሰውን ልጅ በመዋጀቱ ምክንያት ኪሩቤል ለበጉ ሰግደውለታል። ይህ እጅግ አስገራሚና አስደናቂ ነገር ነው። ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት የሚነግረን ነገር አለ።

ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረው፥ ሰማያዊያን ፍጥረታት ወይም መላእክት የሚሰግዱት ለእግዚአብሔር ነው፦

"ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ፤ #መላእክቱ ሁሉ፥ #ስገዱለት።"
(መዝሙረ ዳዊት 97:7)

"አንተ ብቻ እግዚአብሔር ነህ፤ ሰማዩንና የሰማያት ሰማይን ሠራዊታቸውንም ሁሉ፥ ምድሩንና በእርስዋ ላይ ያሉትን ሁሉ፥ ባሕሮቹንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ ፈጥረሃል፥ ሁሉንም ሕያው አድርገኸዋል፤ #የሰማዩም_ሠራዊት ለአንተ #ይሰግዳሉ።"
(መጽሐፈ ነህምያ 9:6)

➣ ይህም ሀቅ በዚያው በራዕይ መጽሐፍ የተረጋገጠ ሀቅ ነው። መላእክት የሚሰግዱት ለእግዚአብሔር ነው፦

" #መላእክቱም ሁሉ በዙፋኑና በሽማግሌዎቹ በአራቱም እንስሶቹ ዙሪያ ቆመው ነበር፤ በዙፋኑም ፊት በግምባራቸው #ተደፉ#ለእግዚአብሔርም #እየሰገዱ።"
(የዮሐንስ ራእይ 7:11)

በተለይም ደግሞ በራዕይ 5:8 ላይ በበጉ ፊት የወደቁት አራቱ እንስሳት (ኪሩቤል) ለማን እንደሚሰግዱ በዚያው በራዕይ መጽሐፍ ተረጋግጧል። ኪሩቤል የሚሰግዱት ለእግዚአብሔር ነው፦

"ሀያ አራቱም ሽማግሌዎችና #አራቱ_እንስሶች በፊታቸው #ተደፍተው በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው #ለእግዚአብሔር። አሜን፥ ሃሌ ሉያ እያሉ #ሰገዱለት።"
(የዮሐንስ ራእይ 19:4)

✍️ የመጽሐፍ ቅዱሱ ትምህርት ግልፅ ነው። መላእክት በተለይም ኪሩቤል የሚሰግዱት ለእግዚአብሔር ነው። በራዕ 5:8 ላይ ግን ለበጉ ሰግደውለታል። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?

ኪሩቤል ለታረደው በግ ሊሰግዱ የቻሉት በጉ ጌታችን ኢየሱስ የተሰገወው እግዚአብሔር በመሆኑ ነው። ሐዋርያው ዮሐንስ በወንጌሉ ላይ ቃል እግዚአብሔር እንደነበር (ዮሐ 1:1) በኋላም ስጋ እንደሆነ (ዮሐ 1:14) በመንፈስ ቅዱስ ጥንሳሴ ነግሮናል። ይህንኑ ትምህርት በመልእክቱ ላይም ደግሞታል። እርሱም ልጁ ጌታ ኢየሱስ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ (1ዮሐ 5:20) ደግሞም በስጋ እንደመጣ (1ዮሐ 4:2) ተናግሯል። ይህንኑ የታመነ ትምህርት ደግሞ በራዕዩ በድጋሚ እየገለፀ ነው። ጌታ ኢየሱስ አልፋና ኦሜጋ ፊተኛውና ኋለኛው እንደሆነ (ራዕ 1:17-18 ራዕ 22:13-16) ነገር ግን ምን አልፋና ኦሜጋ ቢሆንም ሕጻን ሆኖ እንደተወለደ (ራዕ 12:5) በራዕዩ ተመልክቷል። ስለዚህ ይህ ክርስቶስ ሰው ሆኖ የተወለደው/የተሰገወው አምላክ በመሆኑ የታረደ፥ ደሙን ያፈሰሰ ቢሆንም በሰማይ ከኪሩቤል ስግደትን የሚቀበል አምላክ ነው።

ለዚህ ነው ሐዋርያው ጳውሎስ መላእክት ሁሉ ለእግዚአብሔር ልጅ እንደሚሰግዱ በመንፈስ ቅዱስ ጥንሳሴ የጻፈው፦

"ደግሞም #በኵርን ወደ ዓለም ሲያገባ። የእግዚአብሔር #መላእክት ሁሉም ለእርሱ #ይስገዱ ይላል።"
(ወደ ዕብራውያን 1:6)

ልክ በራዕ 5:8 እንዳየነው በዕብ 1:6 ላይም መላእክት ለእግዚአብሔር ልጅ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሰግዳሉ። ምክንያቱም ሰማይና ምድርን የሰራው (ዕብ 1:10) አባቱ አለማትን የፈጠረበት (ዕብ 1:2) ፍጥረት ሲለወጥ የማይለወጠው (ዕብ 1:11-12) የክብሩ ነጸብራቅና የባህርይው ትክክለኛ ምሳሌ፥ ሁሉን በሃያል ቃሉ ደግፎ የያዘው (ዕብ 1:3) በግርማው ቀኝ የተቀመጠ (ዕብ 1:3 ዕብ 1:13) ከመላእክት እጅግ የሚበልጥ (ዕብ 1:4) ኃጢአታችንን ያነጻ (ዕብ 1:3) ዘላለማዊ ዙፋን ያለው አምላክ (ዕብ 1:8) እና ጌታ (ዕብ 1:10) በመሆኑ ነው። ለዚያ ነው ልክ እንደ ራዕ 5:8 በዕብ 1:6 ላይም መላእክት ሁሉ ለእርሱ የሰገዱት። ይህ ግልፅ የሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ነው።

እናም ከራዕ 5:8 ካስገረሙኝና ላካፍላችሁ ከወደድኩት እውነታዎች ዋነኛው ይህኛው ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ በኪሩቤል የሚሰገድለት አምላክ ነው። ክብር ለስሙ ይሁን! እኛም ከኪሩቤልና ከመላእክቱ ጋር ሆነን ይህን ንጉስና እናመልከዋለን። አምልኮ፥ ውዳሴ፥ ሃይል፥ ክብር፥ ምስጋና፥ በረከት፥ ስግደት፥ ሞገስ፥ ንግስና፥ ልዕልና፥ ጌትነት፥ ግዛት፥ መፈራት፥ ብርታትና እልቅና ለታረደው በግ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ልጅ ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን!

✏️ ከክርስትና ውጪ ላሉ ወገኖቻችን (በተለይ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ልጅ የጌታ ኢየሱስን አምላክነት አያስተምርም ለሚሉ ወገኖች) ጥያቄ፦

1) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኪሩቤል በሰማይ የሚሰግዱት ለማን ነው?

2) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኪሩቤል የሰገዱለት ፍጡር አለ?

3) ክርስቶስ ኢየሱስ በስጋ የመጣው መለኮት ካልሆነ ኪሩቤል በሰማይ እንዴት ሊሰግዱለት ቻሉ?

✍️ በማሰረጃ እንድትመልሱልኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ

▶️ ይቀጥላል

2 months, 1 week ago

የሆነ ጊዜ ላይ የራዕይን መጽሐፍ እያነበብኩ ነበር። በሰአቱ እውቁ ዐቃቤ እምነት ሳም ሻሙን ያን መጽሐፍ እያስተማረ ስለነበር መጽሐፉን በጥንቃቄ ከመጀመሪያው ጀምሮ ማንበብ ጀመርኩ። እጅግ በጣም የሚያስገርም መጽሐፍ ነው። በእውነቱ የእግዚአብሔር ቃል ሁሌም አዲስና ተዝቆ የማያልቅ ሀብት ነው። ስለ ቃሉ የቃሉን ባለቤት አመሰግናለሁ

እናም በዚሁ የዮሐንስ ራዕይ ንባቤ ላይ አንድ ክፍል ትኩረቴን ሳበው። ከዚህ በፊት አንድምታውን አስተውዬው አላውቅም ነበር። በኋላ ላይ ግን ክፍሉን ሳጠናው ትርጉሙ እጅግ በጣም አስገራሚና አስደናቂ እንደሆነ ተረዳሁ። እናም ላካፍላችሁ ወደድኩ።

ክፍሉ እነሆ፦

"መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ #አራቱ_እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች #በበጉ ፊት #ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።"
(የዮሐንስ ራእይ 5:8)

በዚህ ክፍል ላይ የእግዚአብሔር በግ የሆነው ጌታ ኢየሱስ ሰባቱ ማህተሞች ያሉበትን መጽሐፍ ከአባቱ ከእግዚአብሔር አብ በወሰደ ጊዜ በሰማይ የሆነውን ነገር እናነባለን። እንደሚታወቀው የራዕይ መጽሐፍ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝጊያ ስለሆነ፥ በውስጡ የሚያካትታቸው ስዓላዊ ትዕይንቶች (imageries) በሙሉ በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ የተብራሩና የተገለጹ ናቸው። ጌታ ኢየሱስም በበግ የተመሰለው ለዚሁ ነው። የአለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ መሆኑ በሌላው መጽሐፍ ተገልጿልና (ዮሐ 1:29) ስለዚህ በዚህም ክፍል ላይ የተባሉትን ነገሮች መረዳት ያለብን ከሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር በማሰናሰል ነው።

በራዕይ 5:8 ላይ በጉ መጽሐፉን በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በፊቱ እንደወደቁ እናነባለን። ከዚያም እያንዳንዳቸው በገናን እና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ እንደያዙ ተገልጾ እንመለከታለን። ሐዋርያው ዮሐንስ ያያቸው እነዚህ ነገሮች በሙሉ አስገራሚና አስደናቂ ትርጉም አላቸው። በዚህ ክፍል ላይ የተነገሩት ነገሮች በሙሉ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት የሚናገሩት ነገር አለ። አንድ በአንድ ለመመልከት እንሞክር

✍️ አራቱ እንስሳት ማናቸው?

ሐዋሪያው ዮሐንስ በራዕዩ እንደተመለከተው በራዕይ 5:8 ላይ በጉ መጽሐፉን ከወሰደ በኋላ ከሀያ አራቱ ሽማግሌዎች ጋር ሆነው በፊቱ የወደቁት አራቱ እንስሳት ናቸው። እነዚህ አራቱ እንስሳት ማናቸው?

ሐዋሪያው ዮሐንስ በራዕይ መጽሐፉ ለመጀመሪያ ጊዜ እነዚህን አራት እንስሳት የተመለከታቸው በምዕራፍ አራት ላይ ነው። ሐዋሪያው የሚያየው ይህ ራዕይ በሰማይ ውስጥ የሚሆን ክስተት ሲሆን (ራዕ 4:2) እነዚህን እንስሳት ሲያያቸው በእግዚአብሔር ዙፋን መካከልና ዙሪያ ነበሩ፥ በፊትና በኋላም ዓይኖች ሞልተዋቸው ነበር (ራዕ 4:6 ራዕ 4:8) መልካቸውም የፊተኛው የአንበሳን፥ ሁለተኛው የጥጃን፥ ሶስተኛው እንደ ሰው ያለ፥ አራተኛው ደግሞ የንስርን ይመስል ነበር (ራዕ 4:7) ከዚያም ባለፈ አራቱም እንስሶች ስድስት ክንፎች ነበሯቸው (ራዕ 4:8)

▶️ ሐዋርያው ዮሐንስ በዚህ ራዕዩ ያያቸው እንስሳት ነቢዩ ሕዝቅኤል በራዕዩ ያያቸው ኪሩቤል ናቸው። የሕዝቅኤል መጽሐፍን ስናጠና ነቢዩ ሕዝቅኤል በራዕይ አይቷቸው የገለጻቸው ኪሩቤል ሐዋርያው ዮሐንስ በራዕዩ ያያቸው እንስሳት መሆናቸውን እንረዳለን።

ነቢዩ ሕዝቅኤል ልክ እንደ ሐዋርያው ዮሐንስ የእግዚአብሔርን ራዕይ ባየ ጊዜ (ሕዝ 1:1 ዮሐ 1:1) የአራት እንስሳትን አምሳያ ይመለከታል (ሕዝ 1:5) እነዚህም እንስሳት ከእግዚአብሔር ዙፋን በታች ያሉ (ሕዝ 1:26) አራት ፊቶች ያሏቸው እንስሳት ሲሆኑ አንደኛው እንደ ሰው ፊት፥ በስተቀኛቸው እንደ አንበሳ ፊት፥ በስተግራቸው እንደ ላም ፊት፥ ደግሞም የንስር ፊት ነበራቸው (ሕዝ 1:10) ከዚህ በተጨማሪም አራት አራት ክንፎች የነበራቸው ሲሆን (ሕዝ 1:6) በዙሪያቸው ዓይኖችን ተሞልተው ነበር (ሕዝ 10:12) ከዚህ ሁሉ የምንረዳው ነገር፥ ነቢዩ ሕዝቅኤል በራዕዩ ያያቸው እንስሳት ሐዋርያው ዮሐንስ ያያቸው ራሳቸው እንስሳት መሆናቸውን ነው። ምክንያቱም በዮሐንስ ራዕይ ላይ የተገለጹበት አገላለጽ በሕዝቅኤል መጽሐፍ ውስጥ ከተገለጹበት አገላለጽ ጋር አንድ አይነት ነውና።

ይህንንም እውነት የዮሐንስ ራዕይንና የሕዝቅኤል መጽሐፍን በጥልቀት ስናጠና በይበልጥ እንረዳዋለን። ነቢዩ ሕዝቅኤል ስለ እነዚህ እንስሳት በራዕዩ ካያቸው ነገሮች አንዱ፥ ለእያንዳንዳቸው በክንፋቸው በታች እጅ ያላቸው መሆኑ ነው (ሕዝ 1:8) እነዚህ እንስሳት ከክንፋቸው በታች እጅ እንዳላቸው በሕዝቅኤል መጽሐፍ ውስጥ እንጂ በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ አልተነገረም። ነገር ግን በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ አራቱ እንስሳት እጅ ያላቸው እንደሆነ ተመላክቷል። በራዕ 15:7 እንደምናነበው ከአራቱ እንስሳት አንዱ የእግዚአብሔርን የቁጣ ጽዋ ቁጣውን ለሚያስተላልፉት ሰባት መላእክት ይሰጣቸዋል። ሐዋርያው ዮሐንስ እንስሳው ጽዋን ለመላእክቱ ሲሰጣቸው ሊያይ የቻለው ያ እንስሳ ነቢዩ ሕዝቅኤል እንዳየው እጅ ስላለው ነው። ይህ በእርግጥም ሐዋሪያው ያያቸው እንስሳት ነቢዩ ያያቸው ራሳቸው እንስሳት ለመሆናቸው ግልጽ ማረጋገጫ ነው

እነዚሁ እንስሳት ኪሩቤል መሆናቸው በዮሐንስ ራዕይ ላይ ባይገለጽም፥ በሕዝቅኤል መጽሐፍ ላይ ተገልጿል፦

"እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ #በኪሩቤል ራስ ላይ ባለው ጠፈር #በላያቸው እንደ ሰንፔር ድንጋይ ያለ እንደ #ዙፋን የሚመስል መልክ ተገለጠ።"
(ትንቢተ ሕዝቅኤል 10:1)

በሕዝ 10:1 እንደምናነበው እንደ ሰንፔር የሚመስለው ዙፋን ያለው በኪሩቤል ራስ ባለው ጠፈር እላይ ነው። ስለዚህ ከኪሩቤል ላይ ጠፈር አለ፥ ከጠፈሩ ላይ ደግሞ ዙፋኑ አለ። ይህ ምስል ነቢዩ በምዕራፍ አንድ ላይ ያየው ምስል ነው። በምዕራፍ አንድ ላይ እንደምናነበው፥ ከአራቱ እንስሳት ራስ በላይ ጠፈር አለ (ሕዝ 1:22-23) ከጠፈሩ በላይ ደግሞ እንደ ሰንፔር ያለው ዙፋን አለ (ሕዝ 1:26) ስለዚህ በሕዝ 10:1 ላይ ኪሩቤል የተባሉት፥ በሕዝ 1 ላይ ነቢዩ ያያቸው አራት እንስሳት ናቸው ማለት ነው። ስለዚህ እነዚያ አራቱ እንስሳት ኪሩቤል ለመሆናቸው ይህ ማረጋገጫ ነው።

እነዚያ አራት እንስሳት ኪሩቤል ለመሆናቸው ከሕዝቅኤል መጽሐፍ ተጨማሪ ማስረጃዎችን እንመለከታለን። በሕዝቅኤል 10:20-22 ላይ እንደምናነበው፥ ነቢዩ ሕዝቅኤል በኮበር ወንዝ ማዶ (ሕዝ 1:1 ሕዝ 1:3) ያየው እንስሳ ኪሩቤል እንደሆኑ ያስተውላል። ምዕራፍ አንድ ላይ እንዳየው እያንዳንዳቸው አራት አራት ፊትና አራት አራት ክንፍ ነበሯቸው (ሕዝ 1:6/ሕዝ 10:21) ፊቶቻቸውን በኮቦር ወንዝ ማዶ ያያቸውን ፊቶች ይመስሉ ነበር፥ እርሱና መልካቸውም እንዲሁ ነበር (ሕዝ 10:22) ይህ ሕዝቅኤል ያያቸው አራቱ እንስሳት ኪሩቤል ለመሆናቸው ግልፅ ማሳያ ነው። ከዚያም በተጨማሪ በሕዝ 10 ላይ ስለ አካሄዳቸው የተገለጸው ነገር ምዕራፍ 1 ላይ ካለው አገላለጽ ጋር አንድ ነው። በሁለቱም ቦታ ሲሄዱ ሳይገላመጡ እንደሆነ ተነግሯል (ሕዝ 1:9/ሕዝ 10:11) ይህ ሁሉ ሕዝቅኤል ያያቸው አራቱ እንስሳት ኪሩቤል መሆናቸውን በሚገባ ያሳያል።

ከላይ በማስረጃ እንደተመለከትነው ግን እነዚህ ነቢዩ ሕዝቅኤል ያያቸው አራቱ እንስሳት (ኪሩቤል) ሐዋርያው ዮሐንስ ያያቸው እንስሳት ናቸው። ሐዋሪያው ዮሐንስ በራዕዩ ሲያያቸው የነበሩት አራቱ እንስሳት እነዚህ ኪሩቤል ናቸው። ስለዚህ በራዕይ 5:8 ላይም በበጉ ፊት የወደቁት እነዚሁ ኪሩቤል ናቸው ማለት ነው።

3 months ago

የክርስቶስ ትንሣኤ ታሪካዊነት የቀጥታ ትምህርት ይከታተሉ።

5 months, 2 weeks ago

ባሳለፍነው ህዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአፍሪካ፣ከካሪቢያንና ከፓሲፊክ የተውጣጡ ሀገራት ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት የሚቆይ የንግድና ኢኮኖሚ ትብብር ስምምነትን ከአውሮፓ ህብረት ጋራ #ሳሞዋ በምትባል ሀገር በፈረሙ ወቅት አገራችን #ኢትዮጵያም ይህንኑ ስምምነት ተቀማጭነታቸው ብራሰልስ በሆኑ አምባሳደር አማካኝነት #በፊርማ_አጽድቃለች፡፡ ይህ #አደገኛ_ይዘቶች ያሏቸውን አንቀጾች የያዘው ስምምነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ከሚቀጥለው #ጥር ወር ጀምሮ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡

ይህ የትብብር ስምምነት በውሥጡ የያዛቸውን አስራ ሁለት ዋና ዋና አደገኛ ይዘቶችን ጠቅልለው የሚይዙ የተወሰኑ ሀሳቦች ለመጥቀስ ያህል ፡-

ሀ) የሀገር ሉዓላዊነትን የሚጥሱ አንቀጾች በግልጽ መቀመጣቸው፣

ለ) ግብረሰዶማዊነት፣ የጾታ መቀየርና፣ውርጃና ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርትን የመሳሰሉ እኩይ አጀንዳዎች በሰብዓዊ መብት ሽፋንና በሌሎች አሳሳች ሀረጎች ተሰውረው የገቡበት መሆኑ፣

ሐ) ግብረሰዶማዊነት በርካታ ቀውሶች ማለትም በአካል፣ በሥነልቦናና በማህበራዊ ህይወት ላይ የሚያስከትልና ለሀገር ደህንነትም አደጋ መሆኑ፣

መ) የወላጆችን መብት የሚጥስና የኢትዮጵያዊ ቤተሰብ እሴቶችን የሚንድ መሆኑ፣

ሠ) የሀገራችንን ሀይማኖት፣ባህልና እሴቶች የሚንዱ ጸያፍ ልምምዶችን እንድንቀበል በሰብዓዊ መብት ሽፋንና በእርዳታ ስም የምንገደድበትና ለዘመናዊ ባርነት ወይንም ቅኝ አገዛዝ ታልፈን የምንሰጥበት መሆኑ፣

በአጠቃላይ ይህ አዲስ የአጋርነት ስምምነት ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡና ትውልድንና ብሎም ሀገርን እጅግ የሚጎዱ በርካታ አንቀጾች የተካተቱበት መሆኑ ለሀገራችን ህዝብ ዕድገትን ሳይሆን ውድቀትንና ከፍተኛ የሞራል ዝቅጠትን የሚያስከትል መሆኑን በሚገባ ተረድተናል፡፡

በተጨማሪም ከተጠበቀው ውጭ ሀገራችን ይህንን ስምምነት በመፈረሟ የተጋረጠብንን እጅግ አሳሳቢ አደጋ ለመቀልበስ አስፈላጊ የሆኑ ሰላማዊና ህጋዊ መንገዶችን ሁሉ በመጠቀም መንግስት ትኩረትን እንዲሰጠው ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡

በመሆኑም ይህ የመንግስት ውሳኔ እንደገና ተጠንቶ ውሳኔው እንዲቀለበስ ማለትም ስምምነቱ አስፈላጊው ሁሉ ማስተካከያ እስኪደረግበት ድረስ ወይንም እጅግ አደገኛ የሆኑት አንቀጾች ተነቅሰው ወጥተው የማንቀበላቸው መሆናችንን በይፋ ማሳወቅ (Submission of an Interpretive Declaration) እስከምንችል ድረስ የምንወዳት ሐገራችን ኢትዮጵያ #ፊርማዋን_በመሰረዝ_ከስምምነቱ ራሷን እንድታገልል በሐገራችን ከፍተኛው የሥልጣን አካል ለሆነው ለተከበረው #የህዝብ_ተወካዮች_ምክር_ቤትና ለሐገሪቱ መሪ #ለክቡር_ጠቅላይ_ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በታላቅ አክብሮት እጅግ አስቸኳይ ጥሪን እናደርጋለን፡፡

የፊርማ ማሰባሰብ ሂደቱን ለመደገፍ ከታች ያለውን ማስፈንጠርያ ይጠቀሙ።

👉 https://keap.page/gq193/.html

6 months ago

♦️ ስለዚህ በዘፍጥረት 32 ታሪክ ላይ ያዕቆብ ወደ እርሱ የጸለየውን ጸሎት ሰምቶ ከወንድሙ ከኤሳው ያዳነው ማነው?

በዘፍጥረት 32 ላይ የያዕቆብን ጸሎት ሰምቶ ከወንድሙ ከኤሳው እጅ ያዳነው ማን ነው ለሚለው ጥያቄ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚከተለው መልሱን ይሰጠናል፦

"24፤ ያዕቆብ ግን ለብቻው ቀረ፤ አንድ #ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታገለው ነበር። 25፤ እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ የጭኑን ሹልዳ ነካው፤ ያዕቆብም የጭኑ ሹልዳ ሲታገለው ደነዘዘ። 26፤ እንዲህም አለው። ሊነጋ አቀላልቶአልና ልቀቀኝ። እርሱም። #ካልባረክኸኝ አልለቅቅህም አለው። 27፤ እንዲህም አለው። ስምህ ማን ነው? እርሱም። ያዕቆብ ነኝ አለው። 28፤ አለውም። ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔር ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና። 29፤ ያዕቆብም። ስምህን ንገረኝ ብሎ ጠየቀው። እርሱም። ስሜን ለምን ትጠይቃለህ? አለው። በዚያም ስፍራ #ባረከው። 30፤ ያዕቆብም። #እግዚአብሔርን ፊት ለፊት #አየሁ#ሰውነቴም #ድና ቀረች ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል ብሎ ጠራው።"
(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 32:24-30)

➣ ያዕቆብ በዘፍ 32 ላይ የምናነበውን ጸሎት ካቀረበ በኋላ የሆነውን ነገር በዚህ ስፍራ ላይ እናነባለን። ለወንድሙ ለኤሳው እጅ መንሻን ካዘጋጀ በኋላ ቤተሰቡንና ከብቱን በረድፍ በረድፍ አሰልፎ የያቦቅ ወንዝን ያሻግራቸዋል (ዘፍ 32:13-23) እርሱ ግን ወንዙን ሳይሻገር ለብቻው ወደ ኋላ ይቀራል። ያኔም አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታገለው ነበር። እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ የጭኑን ሹልዳ ነካው፥ ያዕቆብም ደነዘዘ። ሊነጋ ሲያቅላላ ልቀቀኝ ሲለው፥ ያዕቆብ ካልባረከኝ አልለቅህም አለው። ካልባረከኝ አልለቅህም ማለት በዚህ አውድ ከወንድሜ ከኤሳው ካላዳንከኝ አልለቅህም ማለት ነው። በሰአቱ ለያዕቆብም ጭንቅ የሆነበት ጉዳይ እርሱ ነበርና። ካልባረከኝ አልለቅህም ማለት ከወንድሜ ከኤሳው ካላዳንከኝ አልለቅህም ማለት ነው። በዚህ አውድ በረከት ከጠላቱ ከኤሳው መዳኑ ነውና

ከዚያም የታገለው ሰው ስሙን ወደ እስራኤል ከቀየረው በኋላ፥ በዚያ ስፍራ እንደባረከው በዘፍ 32:29 እናነባለን። ይህ ማለት ደህንነቱ ተረጋገጠ ማለት ነው። ያ የታገለው ሰው ያዕቆብን በመባረክ ከወንድሙ ከኤሳው አዳነው። ከላይ እንዳልነው ያዕቆብ ካልባረከኝ አልለቅህም ሲለው ከወንድሜ ከኤሳው ካላዳንከኝ አልለቅህም ማለቱ ነው። ስለዚህ የታገለው ሰው ያዕቆብን ሲባርከው አዳነው ማለት ነው። እርሱን መባረኩ ከወንድሙ ከኤሳው ማዳኑ ነው። ያዕቆብ በዘፍ 32:11 ላይ በጸሎት የለመነውን ነገር እርሱን በመባረክ ፈጸመለት። ስለዚህ በዘፍ 32:11 ላይ ያዕቆብ ከወንድሜ ከኤሳው አድነኝ ብሎ የጸለየውን ጸሎት ሰምቶ እርሱን በመባረክ ከኤሳው በማዳን የመለሰለት፥ ይህ ለብቻው ሳለ አግኝቶት የታገለው ሰው ነው።

✏️ ታዲያ ይህ ያዕቆብን የታገለው ሰው ማነው?

መጽሐፍ ቅዱስ በዘፍ 32 ላይ ያዕቆብን የታገለው ማን ነው ለሚለው ጥያቄ መልሱን በዚህ መልኩ ይሰጠናል፦

"4፤ በማኅፀን ውስጥ ወንድሙን በተረከዙ ያዘው፥ በጕልማስነቱም ጊዜ ከአምላክ ጋር ታገለ፤ 5፤ #ከመልአኩም ጋር #ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ በዚያም ከእኛ ጋር ተነጋገረ። 6፤ እርሱም የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው፤ የመታሰቢያው ስም እግዚአብሔር ነው።"
(ትንቢተ ሆሴዕ ምዕራፍ 12:4-6)

መጽሐፍ ቅዱስ በትንቢተ ሆሴዕ 12 ላይ በግልጽ እንደሚነግረን፥ ያዕቆብ በዘፍ 32 ላይ የታገለው ከመልአኩ ጋር ነበር! ከአምላክ ጋር ታገለ፥ ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ በማለት ያዕቆብ በያቦቅ ወንዝ ማዶ የታገለው መልአኩ መሆኑን በግልጽ ይናገራል። ስለዚህ በዘፍ 32 ላይ ያለውን የያዕቆብን ጸሎት ሰምቶ፥ በትክክል ሊያድነው የመጣው አምላክ መልአኩ ነበር ማለት ነው። በዘፍ 32ም በሆሴ 12ም መልአኩ እግዚአብሔር ተብሎ የተጠራ ሲሆን፥ ያዕቆብ አድነኝ ብሎ የጸለየውን ጸሎት ሰምቶ ሊመልስለት መምጣቱ በእርግጥም ያዕቆብ ወደ እርሱ ሲጸልይ የነበረው አምላክ መልአኩ መሆኑን ያረጋግጣል።

ለዚያ ነው በዘፍ 32:30 ላይ "..ሰውነቴ ድና ቀረች.." ያለው። እግዚአብሔርን ስላየና፥ ስለባረከው ዳነ። ከላይ በዘፍ 32:11 ላይ አድነኝ ብሎ ነገር የጸለየው። አሁን ግን የተገለጠለትን እግዚአብሔር (መልአኩን) ካየ በኋላ ሰውነቴ ድና ቀረች አለ። ከወንድሜ ከኤሳው ድኛለሁ ማለቱ ነው። ያ እግዚአብሔር ታይቶት ስለባረከው፥ ደህንነቱ ተረጋገጠ ወይም ዳነ። በቁ.30 ላይ "ድና" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "נָצַל/ናትጻል" ሲሆን በቁ.11 ላይ "አድነኝ" ተብሎ የተተረጎመው ቃል ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት በቁ.11 ላይ የጸለየበት ጉዳይ በቁ.30 ላይ ተፈጻሚነት እንዳገኘ ለማሳየት ነው። ይህ የያዕቆብን ጸሎት ሰምቶ፥ ከወንድሙ ከኤሳው ያዳነው እግዚአብሔር መልአኩ መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል። መጥቶ የታገለው፥ የተገለጠለት፥ ደግሞም የባረከው አምላክ እርሱ ነውና። ይህ መልአኩ ጸሎት የሚሰማው አምላክ መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ያረጋግጣል።

▶️ ይቀጥላል

6 months ago

ይህን እውነት ግልፅ ከሆነ በኋላ ግን፥ አንድ ሊጠየቅ የሚገባው ጥያቄ አለ። እርሱም፦

♦️ በዘፍጥረት 28 ላይ ለያዕቆብ ተገልጦለት የነበረው አምላክ ማነው?

ከላይ በብዙ ማስረጃዎች ለማየት እንደሞከርነው፥ ያዕቆብ በዘፍ 32 ላይ እየጸለየ የነበረው በዘፍ 28 ላይ ተገልጦለት ወደነበረው አምላክ ነው። ታዲያ ይህ በዘፍ 28 በቤቴል ለያዕቆብ ተገልጦለት የነበረው አምላክ ማነው ብለን ስንጠይቅ፥ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚከተለው መልሱን ይሰጠናል፦

"10፤ እንዲህም ሆነ፤ በጎቹ በጎመጁ ጊዜ ዓይኔን አንሥቼ #በሕልም አየሁ፤ እነሆም፥ በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ሽመልመሌ መሳዮችና ዝንጕርጕሮች ነቁጣ ያለባቸውም ነበሩ። 11፤ የእግዚአብሔርም #መልአክ በሕልም። ያዕቆብ ሆይ አለኝ፤ እኔም። እነሆኝ አልሁት። 12፤ እንዲህም አለኝ። ዓይንህን አቅንተህ እይ፤ በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ሽመልመሌ መሳዮችና ዝንጕርጕሮች ነቁጣ ያለባቸውም ናቸው፤ ላባ በአንተ ላይ የሚያደርገውን ሁሉ አይቼአለሁና። 13፤ #ሐውልት_የቀባህበት_በዚያም_ለእኔ_ስእለት_የተሳልህበት_የቤቴል_አምላክ_እኔ_ነኝ፤ አሁንም ተነሥተህ ከዚህ አገር ውጣ፥ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመለስ።"
(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 31:10-13)

▶️ በዚህ ስፍራ ላይ የእግዚአብሔር መልአክ ለያዕቆብ በሕልም ተገልጦ የተናገረውን ነገር እንመለከታለን። የላባ ልጆች ያዕቆብ የአባታችን የሆነውን ሁሉ ወሰደ ይህን ሁሉ ክብር ከአባታችን ከብት አገኘ ብለው ያሉትን ሰሞቶ፥ የላባን ፊት ካየ በኋላው ከላባ ጋር እንደ ድሮ መሆን ያቆማሉ። በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ወደ አባቱ ምድር እንዲመለስና በዚያም ከእርሱ ጋር እንደሚሆን ይናገረዋል። ይህን የሰማው ያዕቆብም ራሔልና ልያን አስጠርቶ እንዴት አባታቸውን በቅንነት እንዳገለገለው፥ ነገር ግን እሱ አስር ጊዜ ደሞዙን እንደለዋወጠበት፥ ነገር ግን እግዚአብሔር በጎቹን ሁሉ እንደሰጠው ካስታወሳቸው በኋላ፥ በጎቹ በጎመጁ ጊዜ ያየውን ሕልም ነገራቸው።

እርሱም የእግዚአብሔር መልአክ እንደጠራውና፥ ላባ በእርሱ ላይ የሚያደርገውን ሁሉ እንዳየ ከገለፀለት በኋላ፥ በቀጥታ ሀውልት የቀባበትና፥ በዚያም ለእርሱ ስዕለት የተሳለበት የቤቴል አምላክ እንደሆነ ይነግረዋል። ይህ ቃል በቃል የተነገረ ቃል ሲሆን፥ በዘፍ 28 ላይ ለያዕቆብ የተገለጠለት አምላክ ማን እንደሆነ በሚገባ ያረጋግጣል። በዘፍ 28 በቤቴል ለያዕቆብ የተገለጠለት አምላክ መልአኩ ነበር! ለዚህ ነው በቀጥታ ሀውልት የቀባህበት በዚያም ለእኔ ስዕለት የተሳልክበት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ ያለው።

በዘፍ 31:10-13 እንደምናነበው መልአኩ የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ ነው ያለው። ቤቴል ማለት በዘፍ 28 ላይ እግዚአብሔር ለያዕቆብ በሕልም የተገለጠለት ቦታ ሲሆን፥ ከእንቅልፉ ሲነቃ ይህስ የእግዚአብሔር ቤት ነው በማለት ለስፍራው የሰጠው ስም ነው (ዘፍ 28:19) ቀጥሎም መልአኩ "..ሀውልት የቀባህበት.." በማለት እርሱ ያ ያዕቆብ ሀውልት የቀባበት ቦታ የተገለጠለት አምላክ መሆኑን ይነግረዋል። ይህም ዘፍ 28ን የሚያስታውስ ቃል ነው። ምክንያቱም ያዕቆብ በቤቴል ሳለ እግዚአብሔርን በሕልም ካየ በኋላ፥ ከእንቅልፉ ሲነቃ ያደረገው ይህንኑ ነው። ተንተርሶት የነበረውን ድንጋይ ሀውልት አደረገው፥ በላዩም ላይ ዘይት አፈሰሰበት (ዘፍ 28:18)

ይህ ሁሉ የሆነው በቤቴል ሲሆን፥ መልአኩ "..ሀውልት ያፈሰስክበት .." ሲል እያስታወሰው የነበረው ይህንን ነበር። ከዚያም በተጨማሪ መልአኩ "..በዚያም ለእኔ ስዕለት የተሳልክበት.." ብሎታል። ይህም ዘፍ 28ን የሚያስታውስ ቃል ነው። ምክንያቱም ያዕቆብ በዘፍ 28 በቤቴል ካደረጋቸው ነገሮች አንዱ ስዕለትን መሳል ነው። እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ቢሆንና፥ በሚሄድበት ቢጠብቀው አምላኩ እንደሚሆን በመግለፅ ስዕለትን ተስሏል (ዘፍ 28:20) ስለዚህ ከዘፍ 31:10-13 የምንመለከተው ቀጥተኛ ቃል፥ መልአኩ ያኔ በዘፍ 28 ላይ በቤቴል ለያዕቆብ የተገለጠለት፥ ያዕቆብ ሀውልት የቀባለት፥ ስዕለትም የተሳለለት አምላክ መሆኑን ነው። ያ እግዚአብሔር እርሱ ነው።

✏️ ከባለፈው ክፍል ጀምሮ በማስረጃ ለማየት እንደሞከርነው ግን፥ በዘፍ 32 ላይ ያዕቆብ ሲጸልይ የነበረው በዘፍ 28 ላይ ተገልጦለት ወደነበረው አምላክ ነው። ወንድሙ ኤሳው በመጣ ጊዜ እንዲያድነው የጸለየው፥ በዘፍ 28 ላይ ተገልጦለት ወደ ነበረው አምላክ ነው። አሁን ግን ከዘፍ 31:10-13 እንደምንረዳው ያ በዘፍ 28 ላይ ለያዕቆብ ተገልጦለት የነበረው የቤቴል አምላክ መልአኩ ነበር። ስለዚህ በዘፍ 32 ላይ ያዕቆብ ሲጸልይ የነበረው ወደ መልአኩ ነበር ማለት ነው! ዘፍ 28 ላይ ተገልጦለት፥ እነዚያን ነገሮች ሊያደርግለት ቃል የገባለት፥ በኋላም በዘፍ 31:10-13 ላይ በድጋሚ ተገልጦለት የቤቴል አምላክ መሆኑን ወደ ነገረው መልአክ ነበር ያዕቆብ በዘፍ 32 ላይ ሲጸልይ የነበረው! ያ በዘፍ 28 የተገለጠለት አምላክ መልአኩ ነውና

ለዚህ ነው ልክ በዘፍ 32 ላይ የተባሉት ነገሮች በዘፍ 28 ላይ ከተባሉት ነገሮች ጋር እንደሚመሳሰሉት፥ በዘፍ 32 ላይ የተባለው ነገር በዘፍ 31 ላይ ከተባለው ነገር ጋር የሚመሳሰለው፦

"ያዕቆብም አለ። የአባቴ የአብርሃም አምላክ ሆይ፥ የአባቴም የይስሐቅ አምላክ ሆይ። ወደ #ምድርህ ወደ ተወለድህበትም #ስፍራ #ተመለስ፥ በጎነትንም አደርግልሃለሁ #ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ፤"
(ኦሪት ዘፍጥረት 32:9)

ያዕቆብ በዘፍ 32 ላይ ሲጸልይ "..ወደ ምድርህ ወደ ተወለድህበት ስፍራ ተመለስ #ያልከኝ.." ይላል። ይህ ማለት ወደ እርሱ የሚጸልየው አምላክ ወደ ምድሩ፥ ወደ ተወለደበት ምድር ተመለስ ብሎታል ማለት ነው። ይህ በዘፍ 31 ላይ መልአኩ ለእርሱ የተናገረው ነገር ነው፦

"ሐውልት የቀባህበት በዚያም ለእኔ ስእለት የተሳልህበት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ፤ አሁንም ተነሥተህ ከዚህ አገር ውጣ፥ ወደ #ተወለድህበትም #ምድር #ተመለስ።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 31:13)

መልአኩ በሕልም ከተገለጠለት በኋላ ወደ ተወለደበት ምድር እንዲመለስ ሲነግረው እንመለከታለን። ያዕቆብ በዘፍ 32 ላይ "..ወደ ምድርህ፥ ወደ ተወለድክበት ስፍራ ተመለስ ያልከኝ.." ያለው ለዚህ ነው። ወደ እርሱ እየጸለየ የነበረው አምላክ ዘፍ 31 ላይ የተገለጠለት መልአክ ነበርና። በፊት እንዳየነው፥ ዘፍ 32:9 ላይ ያለው ቃል ዘፍ 28:15 ላይ የተነገረው ቃል ነው። ስለዚህ ከዚህ የምንማረው እውነት፥ በዘፍ 28:15፥ በዘፍ 31:13 እና በዘፍ 32:9 ላይ ያዕቆብን ወደ ምድሩ እንዲመለስ የተናገረው አካል አንድ መሆኑን ነው። እርሱም መልአኩ ነው። ያዕቆብን ወደ ምድሩ እንደሚመልሰው ቃል የገባለት፥ በኋላም ወደ ምድሩ እንዲመለስ ያዘዘው አምላክ እርሱ ነው። ስለዚህ ያዕቆብ በዘፍ 32 ላይ ወደ ምድርህ ተመለስ ያልኸኝ በማለት ወደ እርሱ ሲጸልይ የነበረው አምላክ መልአኩ ነበር ማለት ነው።

➣ ከዚህም ባሻገር በዘፍ 32 ላይ ያዕቆብ ወደ እርሱ የጸለየው እግዚአብሔር መልአኩ እንደነበር የምናውቅበት መንገድ አለ። እርሱም ጸሎቱን የመለሰው አካል ማንነት ነው። በዘፍ 32:11 ላይ ያዕቆብ ወደ እርሱ ሲጸልይ የነበረውን አምላክ እንዲያድነው ጠይቆታል። ስለዚህ ጸሎቱ የቀረበለት አካል የያዕቆብን ጸሎት መለሰ የሚባለው የጠየቀውን ነገር ሰምቶ ሲፈጽምለት ነው። ያን የጠየቀውን ነገር ሲፈጽምለት ጸሎቱን መለሰለት ይባላል። ያዕቆብ ደግሞ የጠየቀው እንዲያድነው ነው።

6 months, 2 weeks ago

"እነሆም፥ እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር፥ እንዲህም አለ። የአባትህ #የአብርሃም #አምላክ #የይስሐቅም #አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ፤"
(ኦሪት ዘፍጥረት 28:13)

በዘፍጥረት 28 ላይ እንደምናነበው፥ በቤቴል ለያዕቆብ የተገለጠለት እግዚአብሔር የአባቶቹ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ ነው። ስለዚህ ያዕቆብ በዘፍጥረት 32 ላይ "የአባቴ የአብርሃም ፥ የአባቴም የይስሐቅ አምላክ ሆይ" ብሎ ሲጸልይ፥ በዘፍጥረት 28 ላይ ወደ ተገለጠለት አምላክ እየጸለየ እንደነበር ከዚህ እንረዳለን።

2) ወደ ምድሩ መልሶታል

በዘፍጥረት 32 ላይ ካለው የያዕቆብ ጸሎት የሚስተዋለው ሌላው ነገር፥ ወደ እርሱ የሚጸልየው አምላክ ወደ ተወለደበት ምድር እንዲመለስ ያዘዘው መሆኑን ነው፦

"ያዕቆብም አለ። የአባቴ የአብርሃም አምላክ ሆይ፥ የአባቴም የይስሐቅ አምላክ ሆይ። ወደ #ምድርህ ወደ #ተወለድህበትም #ስፍራ #ተመለስ፥ በጎነትንም አደርግልሃለሁ ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ፤"
(ኦሪት ዘፍጥረት 32:9)

ያዕቆብ ከወንድሙ ለመትረፍ ወደ እርሱ ሲጸልይ፥ ይህ በያቦቅ ወንዝ ማዶ ሆኖ የሚጸልይለት አምላክ ወደ ተወለደበት ምድር ተመለስ ያለው አምላክ መሆኑን ይገልጻል። ይህ እውነት በዘፍጥረት 32 ላይ ያዕቆብ ወደ እርሱ የጸለየው አምላክ፥ በዘፍ 28 ላይ ለእርሱ የተገለጠለት አምላክ መሆኑን ያሳያል። ምክንያቱም በዘፍጥረት 28 ለእርሱ የተገለጠው አምላክ ወደ ተወለደበት ምድር እንደሚመልሰው ቃል ገብቶለት ነበርና፦

"እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ #ወደዚችም #ምድር #እመልስሃለሁ፤ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 28:15)

በዚህ ቦታ ላይ በዘፍጥረት 28 ለያዕቆብ የተገለጠለት አምላክ ወደዚህችም ምድር እመልስሃለሁ በማለት ቃል ሲገባለት እናያለን። ከላይ ለማየት እንደሞከርነው፥ ያዕቆብ ከከነዓን ምድር ወጥቶ ወደ እናቱ አባት ቤት እየሄደ ነበር። ስለዚህ ከተወለደበት ምድር እየወጣ ነበር ማለት ነው። ይህ በቤቴል የተገለጠለት እግዚአብሔር ግን ወደዚህች ምድር (ወደተወለደባት ምድር) እንደሚመልሰው ቃል ሲገባለት እንመለከታለን። በሄደበት ምድር እንደማይቀር፥ ነገር ግን ሕልሙን ሲያይባት ወደነበረችው ምድር (የትውልድ ምድሩ) እንደሚመልሰው ይነግረዋል። ስለዚህ በዘፍጥረት 32 ላይ "ወደ ተወለድህበት ስፍራ ተመለስ ያልከኝ" በማለት ወደ እርሱ የጸለየው አምላክ፥ በዘፍጥረት 28 ላይ ከወንድሙ በሸሸ ጊዜ በቤቴል የተገለጠለት እግዚአብሔር ነው። ያዕቆብ በዘፍጥረት 28 ላይ የሚጸልየው በዘፍጥረት 32 ላይ ወደ ተገለጠለት አምላክ ነው።

3) አምላኩ መሆኑን መስክሯል

በዘፍጥረት 32 ላይ ከምንመለከተው የያዕቆብ ጸሎት የምንረዳው ሌላው ነገር ቢኖር፥ ወደ እርሱ የሚጸልየው አምላክ አምላኩ መሆኑን መመስከሩ ነው፦

" #ለባሪያህ ከሠራኸው ከምሕረትህና ከእውነትህም ሁሉ ትንሽ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፤ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና፥ አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 32:10)

በዚህ ስፍራ ላይ ያዕቆብ ወደ እርሱ የሚጸልየው እግዚአብሔር ባሪያ መሆኑን ይመሰክራል። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ፥ አንድ ሰው የእግዚአብሔር ባሪያ ከሆነ እግዚአብሔር የዚያ ሰው አምላክ ነው። ሰለሞን የእግዚአብሔር ባሪያ በመሆኑ (1ነገ 8:29) እግዚአብሔር የሰለሞን አምላክ ነው (1 ነገ 5:4) ኢያሱ የእግዚአብሔር ባሪያ በመሆኑ (መሳ 2:8) እግዚአብሔር የኢያሱ አምላክ ነው (ኢያ 9:23) ኢሳያስ የእግዚአብሔር ባሪያ በመሆኑ (ኢሳ 20:13) እግዚአብሔር የኢሳያስ አምላክ ተብሏል (ኢሳ 7:13) በዚሁ መንገድ፥ ያዕቆብ ወደ እርሱ የሚጸልየው አምላክ ባሪያ መሆኑን መመስከሩ፥ ያ አምላክ የእርሱ አምላክ መሆኑን እንደመሰከረ ያረጋግጣል።

ይህ በዘፍጥረት 32 ላይ ያዕቆብ ወደ እርሱ የጸለየው አምላክ በዘፍጥረት 28 በቤቴል የተገለጠለት አምላክ ለመሆኑ ተጨማሪ ማሳያ ነው። ምክንያቱም በዘፍጥረት 28 ላይ ያዕቆብ ያኔ የተገለጠለት አምላክ፥ አምላኩ መሆኑን መስክሯልና፦

"ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ፥ እግዚአብሔር #አምላኬ ይሆንልኛል፤"
(ኦሪት ዘፍጥረት 28:21)

በዚህ ቦታ ላይ ያዕቆብ በቤቴል በዘፍ 28:13-15 ላይ የተገለጠለት እግዚአብሔር አምላኩ መሆኑን ሲመሰክር እንመለከታለን። ከቁ.13-15 እንደምናነበው በዚህ ቦታ ላይ ለእርሱ የተገለጠው አምላክ ከእርሱ ጋር እንደሚሆን፥ እንደሚጠብቀውም ቃል ሲገባለት እንመለከታለን (ዘፍ 28:15) ከዚያም በማለዳ ተነስቶ፥ ተንተርሶት የነበረውን ድንጋይ ሐውልት አድርጎ አቆመው፥ በላዩም ዘይትን አፈሰሰበት። ከዚያም እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድበት መንገድ በዚህ መንገድ ቢጠብቀኝ አምላኬ ይሆናል በማለት ስዕለትን ይሳላል። ማለትም፥ በዘፍ 28:13-15 ላይ የተገለጠልኝ አምላክ የገባውን ኪዳን ቢፈጽምልኝ አምላኬ ይሆናል ማለት ነው። ስለዚህ ያዕቆብ በዘፍጥረት 28:21 ላይ ተገልጦለት የነበረው እግዚአብሔር አምላኩ መሆኑን መስክሯል።

ስለዚህ በዘፍጥረት 32:10 ላይ ባሪያው እንደሆነ የመሰከረለት እግዚአብሔር፥ በዘፍጥረት 28:21 ላይ አምላኩ መሆኑን የመሰከረለት እግዚአብሔር ነው። ይህ በዘፍጥረት 32 ላይ ያዕቆብ እየጸለየ የነበረው በዘፍጥረት 28 ላይ ወደ ተገለጠለት እግዚአብሔር መሆኑን በግልጽ ያሳያል።

♦️ ይህ ሁሉ ጸሎት ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ እንደሚጸለይ የሚያሳየው እንዴት ነው?

▶️ ይቀጥላል

We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month, 2 weeks ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 4 days, 23 hours ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 5 months, 1 week ago