Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

🫂ሰው ሁን ከሰውም ሰው🫂

Description
Schedule

ሰኞ፡ mental Health
ማክሰኞ፡ sucess
ረብዕ፡ psychology
ሐሙስ፡ relationship
አርብ፡ bed time stories
ቅዳሜ፡ general
እሁድ፡ general

ያለ አእምሮ ጤና ምንም ጤና የለም
For Any Comment Inbox Me @umbeya
Advertising
We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 2 days, 20 hours ago

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 2 months ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 5 months, 4 weeks ago

2 weeks, 3 days ago

🌗 ቅብጥብጡ ውሻ

የት እንዳነበብኳት ባላስታውስም ከረጅም ጊዜ በፊት ያነበብኳት አንዲት አጭር ታሪክ ትዝ አለችኝ፡፡ አስተምራኝ አልፋለች፣ ዛሬም ባሰብኳት ቁጥር ታስተምረኛለች፡፡ የአንድ ሰውና የውሻው አጭር ታሪክ ነው፡፡

💡በገጠራማው አካባቢ የሚኖር አንድ ሰው ከቤቱ ወጥቶ ወደ 30 ደቂቃ የሚፈጅ የእግር ጉዞ ካደረገ በኋላ መድረስ ወደሚገባው የወዳጁ ቤት ደረሰ፡፡ ከእሱ ጋር እሱ በሄደበት ሁሉ የሚከተለው በጣም የሚወደው ውሻው እንደተለመደው ተከትሎት መጥቷል፡፡ ሰውየው ወዳጁ ቤት ሲደርስ ከወዳጁ ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ወዳጁ፣ “ያ ሁልጊዜ በሄድክበት ሁሉ የሚከተልህ ውሻህስ የት አለ?” ብሎ ገና ከመጠየቁ ውሻው እያለከለከና በውኃ ጥም ለሃጩን እያዝረከረከ ከባለቤቱ ጀርባ ከተፍ አለ፡፡

የዚህ ሰው ወዳጅ የሰውየውን አለመድከም ከውሻው ማለክለክ ጋር አነጻጸረና፣ “ውሻህን ምን አድርገኸው ነው እንደዚህ የደከመው፡፡ አንተ ምንም የድካ ስሜት አይታይብህም፣ እሱ ግን በጣም ደክሟል” አለው፣ ልክ በውሻው ላይ እንደጨከነበትና ችላ እንዳለው አይነት ስሜት በሚሰጥ ሁኔታ፡፡

💡የውሻውም ባለቤት ይህ የለመደውና በሄደበት ሁሉ ሰዎች የሚጠይቁት ጥያቄ በመሆኑ ብዙም ሳይገረም በውስጡ አቀባብሎ ያለውን መልስ መለሰለት፣ “የሚገርምህ ነገር ሁለታችን ከቤት ተነስተን እኩል መንገድ ነው የመጣነው፡፡ በእኔና በእሱ መካከል ያለው ልዩነት እኔ ቀጥ ብዬና ተረጋግቼ ነው የመጣሁት፣ እሱ ግን እንዴ ወደ ግራ፣ አንዴ ደግሞ ወደ ቀኝ ሲባዝን፤ አንዴ አንድን ነገር ሲያባርር፣ እንዴ ደግሞ ቆም ብሎ መሬቱን እያሸተተ አንድን ነገር አገኛለሁ ብሎ ሲቆፍ፣ እኔ ስርቅበት ደግሞ ለመድረስ ሲሮጥ . . . ሁል ጊዜ እሱን የሚያደክመው ይህ ቅብጥብጥ ባህሪው ነው”፡፡

💡ለካ ያለመጠን የሚያደክመን መንገዳችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ የሚያዝለን ስራችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ በቀኑ መጨረሻ ላይ ዝልፍልፍ የሚያደርገን የቀኑ ዋና ዓላማችን አይደለም፣ ለካ በኑሮ ድክም ያልነው በተለመደው የኑሮ ሂደት አይደለም፡፡ እኛን የሚያደክመንና ዝለት ውስጥ የሚከተን በመንገዳችን ላይ በማያገባን ነገር እየገባን ወዲህና ወዲያ የምንለው ነገር ነው፡፡

ይህ እውነት የገባኝ ቀን . . .

💎ስለማያገባኝ ሰው ማውራት አቆምኩኝ፣ በማያገባኝ ስፍራ መገኘት ተውኩኝ፣ ምንም ለውጥ በማያመጣ ነገር ላይ መከራከርን ጣልኩት፣ ምንም ተጽእኖ ከማላመጣለት ሰው ጋር መነታረክን ተወት አደረኩኝ፣ ድምዳሜ ላይ ስደርስ ምንም ፋይዳ የማያመጣልኝን ጉዳይ ማሰላሰል እርግፍ አደረኩኝ . . . በአጭሩ የማደርገው ነገር ሁሉ ከዋናው የህይወቴ ዓላማና እሴት ጋር የመጣጣሙን ጉዳይ ማሰብ መኖር ጀመርኩኝ፡፡

ይህንን ያደረኩኝ ጊዜ ብዙ ሸክም ከላዬ ላይ የተነሳ ያህል እርምጃዬ ቀለለኝ፣ ምክንያት-የለሹ የድካም ስሜት ተወኝ፣ የጀመርኩትን ግቤን ጥጉ የማድረስ ጉልበት አገኘሁኝ! ለካ እኔንም ልክ እንደ ቅብጥብጡ ውሻ ያደከመኝ ቀጥታው ሳይሆን ግራ-ቀኙ እና መለስ-ቀለሱ ነው!

   ዶ/ር እዮብ ማሞ

tazi

2 weeks, 4 days ago

እየጎዳችሁ እንደሆነና እንደማይጠቅማችሁ እያወቃችሁ ሙጭጭ ያላችሁበት ልምድ፣ መተው ያቃታችሁ የፍቅር ግንኙት ውስጥ ከሆነ ያላችሁት ለምን??
የትኛውን ርሃባችሁን አስታግሶላችሁ ነው??
አልያም ከምን እየተሸሸጋችሁ ነው??

ታዚ

2 weeks, 5 days ago

**እንደ እናትም እንደ አባትም!

ለእናቶች . . .**
ከአባት እርዳታ ውጪ ልጆቻቸውን ለሚያሳድጉ ብርቱና ገራሚ እናቶች!

ትናትና ባስተላለፍኩት አባት-የለሽ በሚለው መልእክቴ ላይ የአባትን አለመኖር ተጽእኖ ተመልክተና፡፡ በርካታ ሰዎች ከአባት ውጪ ልጆችን ለሚያሳድጉ ሃሳብ ቢሰጥ የሚልን መልእክት inbox በማድረጋችሁ ምክንያት ይህችን ሃሳብ አስተላልፋለሁ፡፡

አባት በስራ ብዛት፣ በግድ የለሽነት፣ በሱሰኝነት፣ በፍቺ፣ በሞትና በመሳሰሉት ምክንያቶች በልጆች ሕይወት በማይገኝት ጊዜ በእናት ላይ ያለው ጫና ቀላል አይደለም፡፡ አቅርቦትን ለማምጣት መስራት፣ የልጆችን ባህሪይ በምሳሌነትና በእርማት መግራት፣ ለልጆች ጥበቃ ማድረግ፣ የልጆችን የስሜት ውጣውረድ መሸከም . . . ሃላፊነቱ ብዙና ከባድ ነው፡፡ የማይቻል ግን አይደለም፡፡

ልጆች ይህ ነው የማይባል ሁኔታዎችን የመላመድና እንደሁኔታው ራስን የማዘጋጀት ብቃት አላቸው፡፡ ይህ ብቃታቸው ከአባት ውጪ በመኖርም አንጻር አይለወጥም፡፡ ሆኖም፣ ከአባት ድጋፍ ውጪ ልጆችን የምታሳድግ እናት ማድረግ ያለባትንና የሌለባትን በሚገባ የማወቋ ጉዳይ ወሳኝ ነው፡፡

በልጆች ሕይወት ላይ ችግር የሚያስከትለው የአባት አለመኖር ሳይሆን ሁኔታው በምን መልኩ እንደተያዘ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ፣ እናት ብቻዋን ሆና የልጆችን ሸክም ስትሸከም አያያዟ ወሳኝ ነው፡፡

•  የቤት ውስጥ ስራንና ሸክምን ለመወጣት የሰዎችን እገዛን ማግኘት፡፡
•  የአባትን ሚና ሊጫወት የሚችል የቅርብ ሰው (አጎትና የመሳሰሉት) ማዘጋጀት፡፡
•  የአባትን ክፍተት ለመሙላት በሚል ምክንያት በልጆች ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ሌላ ወንድ ከማስገባት መጠንቀቅ፡፡
•  በአባታቸው አለመኖር ምክንያት የጎደለውን ለመሙላት ሲባል ልጆችን ልቅ ከማድረግ መጠበቅ፡፡
•  በልጆች ፊት ኑሮን፣ ፈጣሪን፣ የሌለውን አባት እና የመሳሰሉትን እየጠቀሱ ከማማረር መጠበቅ፡፡
•  ራስን አለመጣል፡፡ ልጆች ጤናማ የሚሆኑት እናት ጤናማ ስትሆን፣ የሚኖሩት እናት ስትኖር እንደሆነ በማሰብ ራስን መጠበቅ አስፈላጊ ነው፡፡

ልጆቻችሁን ለብቻችሁ የምታሳድጉ እናቶች *በርቱ! አይዟችሁ!

dr eyob mamo
ታዚ*

3 weeks, 3 days ago

**ፈጣሪ ሆይ፣ ወደ እኔነቴ መልሰኝ

ራስን የመሆን ቁልፍ!**(25 የስኬት ቁልፎች ከተሰኘው የዶርር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ ውስጥ የተወሰደ)

የጥንት አፈ-ታሪክ እንዲህ ይነገረናል፡፡ አንድ ጊዜ አንዲት አይጥ በሰላም ስትኖር ሳላች በድንገት ድመት አይታ እጅግ ደነገጠች፡፡ ከዚህ ድንጋጤ ለመዳን ምርጫዋ ብዙ ነው - ለምሳሌ ምናልባት ድመቷ ፈሪ ልትሆን ስለምትችል መጋፈጥና ሁኔታውን ማየት፣ አላዛልቅ ካለ ወደቀዳዳዋ ገብታ ቀን እስኪያልፍ መሸሸግ፡፡ አይጧ ግን የመረጠችው ያልተጠበቀ መንገድ ነው፡፡

“ፈጣሪ ሆይ፣ ሁለተኛ ድመትን እንዳልፈራ፣ ድመት አድርገኝ” በማለት ጸሎት አደረሰች፡፡ የተመኘችው ሆነላትና ወዲያው ወደ ድመትነት ተቀየረች፡፡ ብዙም ሳትቆይ ግን ውሻ በፊቷ ተደንቅሮ አገኘችው፡፡ የለመደችውን ጸሎት ማነብነብ ቀጠለች፣ “ፈጣሪ ሆይ፣ ሁለተኛ ውሻን እንዳልፈራ፣ ውሻ አድርገኝ”፡፡ አሁንም የተመኘችው ሆነላትና ወዲያው ወደ ውሻነት ተቀየረች፡፡

ሆኖም ይህኛውም ማንነት ብዙም አላዛለቃትም፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ መንገድ ስታቋርጥ አንበሳን አየችና የተለመደውን ጸለቷን አደረገች፡፡ “ፈጣሪ ሆይ፣ ሁለተኛ አንበሳን እንዳልፈራ፣ አንበሳ አድርገኝ”፡፡ እንደገና የተመኘችው ሆነላትና ወዲያው ወደ አንበሳነት ተቀየረች፡፡ አንበሳነቱም አላዛለቃትም፡፡  ከጥቂት  እርምጃ  በኋላ  አንድ  ለአደን  የወጣ  ሰው  መሳሪያ  ታጥቆ  አየችና እጅግ ደከማት፡፡

“ፈጣሪ ሆይ፣ አንዴ ብቻ ታገሰኝ፡፡ ሁለተኛ ሰውን እንዳልፈራ፣ እባክህን ሰው አድርገኝ” ብላ የተለመደ ጸሎቷን ጸለየች፡፡ አሁንም ምኞትዋ ደረሰና ወደ ሰው ተቀየረች፡፡ በመለዋወጥ የደከመ ማንነቷን ለማሳረፍ እቤቷ ገብታ ቁጭ ባለ ቴሌቭዥን ስታይ አንድን የኮሽታ ድምጽ ሰማች፡፡ ዘወር ስትል፣ አይጥ ወዲህ ወዲያ ስትል አየችና እጅግ ፈራች፡፡ የመጨረሻው ምኞትዋ በጸሎት መልክ በድንገት ከአንደበቷ ወጣ፣ “ፈጣሪ ሆይ፣ ሁለተኛ አይጥን እንዳልፈራ፣ ወደ እኔነቴ መልሰኝ”፡፡ ወዲያውኑ ይህ የመጨረሻ ምኞቷ ሆነላትና ችግሯን ለማሸነፍ ራስን የመቀየር ጉዞዋን ወደ ጀመረችበት ወደ አይጥነቷ ተመለሰች - ብዙ ቀናትን ካባከነች በኋላ፡፡

ራስን ከመሆን፣ ማንነታችንን ከማሳደግ እና ባደገው ማንነታችን ፍርሃታችንን ከመጋፈጥ ውጪ ድል የማግኛው መንገድ ምንድን ነው? በፊታችን እንደተደነቀረው ገጠመኝና እንደ እለቱ ሁኔታ ራስን እንደመለወጥ ምን አድካሚ ሕይወት አለ?

ማንነቴን አውቄና ተቀብዬ፣ ድካሜን በማሸነፍና ብርታቴ ላይ በመገንባት ራሴን ሆኜ መኖር የድሎች ሁሉ ድል ነው! ራስንና ማንነትን ለቅቆ የሚጀመር ጉዞ የማያልቅ፣ አድካሚና፣ ወደተነሳንበት ስፍራና ሁኔታ እንደገና “በዜሮ” የሚያስጀምር ሁኔታ ነው፡፡

ሌሎች የራሳቸው ማንነት በማሳደግና በመበርታት ያሸነፉትን ችግር አንተ እነሱን ለመሆን በመሞከር አታሸንፈውም፡፡ አንተነትህ አንተነትህን ይፈልገዋልና ራስህን ሆነህና ከራስህ ጋር ተስማምተህ ኑር፡፡

ይህንን ወሳኝ መጽሐፍ ለቅዳሜና እሁድ የእረፍት ቀን እንድታነቡ ላነሳሳችሁ!

ታዚ

3 weeks, 3 days ago

በህይወት ስንኖር አንድ ልብስ ብቻ መልበስ ቢኖርብን የምናደርገውን ጥንቃቄ አስቡት እስኪ?
ያ ልብስ እንዳይቆሽሽ ስንጠነቀቅ፣ ከቆሸሸብን ደግሞ ስናጥበው እንዳይሳሳ ስንጠነቀቅ፣ እንዳይቀደድ ስንሳቀቅ ብቻ በተቻለን አቅም እኛ ሳናልቅ እሱ ቀድሞ እንዳያልቅ ዋጋ እንከፍላለን።

የተሰጠን ህይወት እንደዚህ ልብስ ነው፤ ሌላ ተቀያሪ የለንም። ታዲያ ለምንድነው ግድየለሽ የምንሆነው? ሰዎች ምን ይሉኛል ብለን የማንፈልገውን የምናደርገው? አንድ አይን ያለው ሰውኮ በአይን አይቀልድም! ወንድሜ የተሰጠህን የመኖር ዕድል በነፃነት የፈለከውን ሆነህ የፈለከውን አሳክተህ መኖር አለብህ!

ጥሩ ጥሩ ነገሮች በሙሉ ለ እናንተ መልካም ቀን🌞

ታዚ

3 weeks, 3 days ago

👁    አንድ ዓይን
በአንድ መንደር የሚኖር አንድ ምቀኛ ሰው ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን እግዚአብሔር ተገለጠለትና ንገረኝ ምን ላድርግልህ ካለው በኋላ ወንድማዊ ፍቅርን ሊያስተምረው ስለፈለገ የፈለከውን ጠይቀኝ እሰጥሃለሁ።

፡ ግን ለአንተ አንድ ነገር ሳደርግልህ ለጎረቤትህ ሁለት እጥፍ እንደማደርግለት ልታውቅ ይገባሃል አለው።

: ምቀኝነቱ ከደሙ ጋር የተዋሃደ ያህል የሚያመው ይኽ ምቀኛ ሰው የሚፈልገው ብዙ ነገር ቢኖርም ለጓደኛው /ጎረቤቱ እጥፍ ሊሰጠው በመሆኑ ተበሳጨ እናም ምን ብሎ ቢለምን ጥሩ ነው???
.
.
.
.
.
.
.
: እግዚአብሔር ሆይ አንድ አይኔን አጥፋው...........(የጎረቤቱ ሁለቱም እንዲጠፋ )
✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️

ምቀኛ ነጋዴ "በራሱ መዘረፍ ሳይሆን በጓደኛው መታለፍ ይበሳጫል" እንዲሉ ....

እኔ መልካም ስለሆንኩ ዓይንህ ምቀኛ ናትን? ማቴ 20:1 - 17

ታዚ

2 months, 3 weeks ago

ፍቅረኛ አሎት?😍🤷‍♂

2 months, 3 weeks ago

Sex🔞 or love🥰

2 months, 3 weeks ago

ጅንጀና style part 1
😘😘😘😘😘😘😘
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

3 months ago

ፍቅረኛ አሎት?😍🤷‍♂

We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 2 days, 20 hours ago

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 2 months ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 5 months, 4 weeks ago