Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

EOTC TV

Description
Advertising
We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ሃሳብ አስታየት Or ማስታወቂያ - @AbusheCBot

● Welcome to Ethio music Channel

➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !

Last updated 1 month ago

4 days, 19 hours ago
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ …

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜ ጉባኤ ያደርጋል፤ የመጀመሪያው ጉባኤ ጥቅምት ፲፪ ቀን (የቅዱስ ማቴዎስ በዓል) ሲኾን፣ ሁለተኛው ደግሞ ርክበ ካህናት የሚባለው በዓለ ትንሣኤ በዋለ በ፳፭ኛው ቀን፣ በበዓለ ኃምሳ እኩሌታ በዕለተ ረቡዕ የሚከበረው ነው፡፡

5 days, 8 hours ago

https://youtu.be/0IgWnM69NHE?si=xbtJM4PDg94oqbEj

YouTube

EOTC TV | EEGUMSA AMANTAA Dubartoonni Maaliif Hin Lallabne

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++ https://youtu.be/Wqgq1KebrOo ***🇪🇹*** "የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ" ***🇪🇹*** ***📡*** የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት ***🎥*** ***📱*** የዲጂታል ሚዲያ ገጾች***💻*** ለመረጃ ***📞*** +251985585858 ➽ የዩቲዮብ ገጻችን http://www.youtube.com/c/eotctv…

5 days, 8 hours ago

https://youtu.be/0IgWnM69NHE?si=xbtJM4PDg94oqbEj

YouTube

EOTC TV | EEGUMSA AMANTAA Dubartoonni Maaliif Hin Lallabne

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++ https://youtu.be/Wqgq1KebrOo ***🇪🇹*** "የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ" ***🇪🇹*** ***📡*** የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት ***🎥*** ***📱*** የዲጂታል ሚዲያ ገጾች***💻*** ለመረጃ ***📞*** +251985585858 ➽ የዩቲዮብ ገጻችን http://www.youtube.com/c/eotctv…

1 week, 3 days ago

https://youtu.be/IffVhfQC-8Q?si=3rq9yx96T5vHR0Kr

YouTube

EOTC TV |ዜና ቤተ ክርስቲያን | ግንቦት 14 2016 ዓ/ም

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++ https://youtu.be/Wqgq1KebrOo ***🇪🇹*** "የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ" ***🇪🇹*** ***📡*** የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት ***🎥*** ***📱*** የዲጂታል ሚዲያ ገጾች***💻*** ለመረጃ ***📞*** +251985585858 ➽ የዩቲዮብ ገጻችን http://www.youtube.com/c/eotctv…

1 week, 3 days ago
EOTC TV
1 week, 3 days ago

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በደቡብ አፍሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት በማጠናቀቅ ወደ መንበረ ክብራቸው በሰላም ተመለሱ፡፡
(#EOTCTV ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም)
ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እና ወደ ደቡብ አፍሪካ አብረዋቸው ለተጓዙ የልዑካን ቡድን አባላት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅና ባህር ዳርና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

2 months, 1 week ago

https://vm.tiktok.com/ZMMSfFuLF/

TikTok

TikTok · EOTCTV

Check out EOTCTV’s video.

EOTC TV
2 months, 2 weeks ago
EOTC TV
2 months, 2 weeks ago

“ቅድስት” የዐቢይ ጾም ኹለተኛ ሳምንት
መ/ር ጌታቸው በቀለ
የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መዝሙር ንባቡን ከዜማው አስማምቶና አጠናቅሮ የተናገረው ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው በዓቢይ ጾም ውስጥ ለሚገኙት እሑዶች ሁሉ የተለየ መዝሙር ሰርቶላቸዋል፡፡ በመዝሙራቱ ውስጣዊ ምስጢር መሠረትም እያንዳንዱ እሑድ ስያሜ ተሰጥቶቸል፡፡ በዚሁም መሠረት ያሳለፍነውን ሳምንት ከቅበላው ዋዜማ ጀምሮ “ዘወረደ” ብለን በቤተ ክርስቲያናችን አክብረናል፡፡ ዛሬ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የኹለተኛውን ሳምንት “ቅድስት”ን ስያሜና ምሥጢሩን እንማራለን፡፡ ቅድስት ቅድሰት የዐቢይ ጾም ኹለተኛ ሰንበት (ሳምንት) ስያሜ ነው፡፡የሰንበትን ቅድስና የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ስያሜውም ከኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ከቅዱስ ያሬድ የተገኘ ነው፡፡ከዚህ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይዘመራል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ሰንበቱን ስለ ቅድስና ልጆቿን ታስተምርበታለች፡፡ በቅዳሴ ጊዜ የሚሰበከው ምስባክ፤ የሚነበቡ መልዕክታት፤ የሐዋርያት ሥራና ወንጌል ስለ ቅድስት የሚያስተምሩ ናቸው፡፡ “ቅድስት” ማለት የዘይቤ ፍችው “የተቀደሰች፣ የተለየች፣ የተባረከች፣ ንጽሕት” ማለት ነው፡፡ ምስጢራዊ መልእክቱ ግን የምስጢረ አድኅኖት ታላላቅ ሥራውን ለመጀመር መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ ከቆመ ሳያርፍ፣ ከዘረጋ ሳያጥፍ የጾማት የአርብዓው ቀንና ሌሊት ልዩ የሆነችና ክብርት ጾም የምትጀመርበትን ሁለተኛ ሳምንት ናት፡፡ /ማቴ. ፬፥፪/፡፡ «ጾምን ቀድሱ ጉባኤውን ዐውጁ ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤተ ሰብስቡ፡፡» (ት.ኢዩ. ፪፥፲፬) ብሎ በነቢዩ ኢዮኤል አፍ የተናገረ ቅዱስ እግዚአብሔር የጾማት ጾም ስለሆነች ቅድስት ትባላለች። ቅድስት ዕለተ ሰንበት “እግዚአብሔር ሰባተኛይቱን ቀን ባረካት ቀደሳት” (ዘፍ 2÷3፣ ዘጸ 20፥8) ሰዎች ፍጥረት ያልተፈጠረባት ዕለት ብለው እንዳይንቋት እንዳያቃልሏት እረፍተ ሥጋ እረፈተ ነፍስ የተገኘባት ዕለት ስለሆነች ቀደሳት አለ፡፡ ቅዱስ ያሬድም “ሰንበትየ ቅድስትየ ዕንተ አዕረፍኩ እምኩሉ ግብርየ ይቤ እግዚኣብሔር” ብሉአል:: በዚህ እሑድ (ሳምንት ) ቀደሳት፣ አከበራት፣ ከፍ ከፍ አደረጋት የተባለች ሰንበትን የምትታሰብበት የሰንበትንም ቅድስና የሚመለከቱ መዝሙሮች የሚቀርብበት ሳምንት በመሆኑ ቅድስት ተብሏል። ቅድስት የዐቢይ ጾም ኹለተኛ ሳምንት ሲሆን፤ ለጌታ ጾም (ጾመ ዐርባ) የመጀመሪያ ሳምንት ነው፡፡ ያለትናንት ቀዳማዊ፤ ያለዛሬ ማዕከላዊ፤ ያለነገ ደሃራዊ፤ ለዘመኑ ጥንትና ፍጻሜ ለግዛቱ ዳርና ድንበር የሌለበት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ አብነት ይሆነን ዘንድ ጾሙን የጀመረበት የመጀመሪያው ሳምንት ቅድስት ተብሎ የመጠራቱ ምክነያት ከዚሁ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ የአምላካችንን ቅድስና እና ሰንበት ቀድሶ በፈቃዱ እንደሰጠን እያነሣሣ ስለሚዘምር ነው፡፡ ጾመ ድጓውም እንዲህ ይለዋል፡- “ዛቲ ዕለት ቅድስት ይዕቲ ሰንበትየ ቅድስትየ እንተ አዕረፍኩ ቅዱሳነ ኩኑ እስመ አነሂ ቅዱስ አነ አብ ቀደሳ ለሰንበት - ይህች ቀን የተቀደሰች ናት ያረፍኩባት ቅድስት ሰንበት ናት፡፡ እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ፡፡ አብ ሰንበትን አከበራት ቀደሳት”፡፡ ስያሜው ሰንበት የዕረፍት ቀን እንድትሆን በኦሪትም በሐዲስም እግዚአብሔር የባረካት የቀደሳት ዕለት መሆኑዋን የሚናገርና እግዚአብሔር ቅዱስ እንደሆነ የፈጠረውም ሰውም ቅድስናን መያዝ የሚገባው መሆኑን የሚያሳስብ ነው፡፡ /ዘፍ ፪፥፫፤ዘፀ ፳፥፰-፲፩፤ዘሌ ፲፱፥፪-፫፤፩ኛ ጴጥ ፩፥፲፭-፲፮/፡፡ ከላይ እንደተገለጸው እቀደስ አይል ቅዱስ፤ እከብር አይል ክቡር፤ እነግስ አይል ንግሥና የባህሪዩ የሆነ አምላክ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾሞ፤ የጾምን ጥቅምና ሥርዓቱንም ሊያስተምረን መጾም የጀመረበት ሳምንት ይህ ነው፡፡ ይህ ሳምንት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የባሕሪይ ቅድስና የሚነገርበት ሳምንት ነው፡፡ ስለዚህች ቀን ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት አስቀድሞ “እስመ አማልክተ አሕዛብ አጋንንት፤ እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ፤ አሚን ወሠናይት ቅድሜሁ፤ ቅድሳት በዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ - የአሕዛብ አማልክት ሁሉ አጋንንት ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ፡፡ ምስጋናና ውበቱ በፊቱ፤ ቅድስናና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው፡፡” /መዝ ፺፭፥፭/ በማለት ቅድስናና ክብር የባሕሪዩ መሆኑን ተናግሯል፡፡ እኛ ከርኵሰታችን የምንቀደስበትንና የምንከብርበትን ሥርዐት ሊሠራልን አንድም አዳም በመብል ምክንያት ከክብሩ ተዋርዶ ነበርና በአዳም ምትክ ተተክቶ ካሣ ሊከፍልለት በገዳመ ቆሮንቶስ ጌታችን መጾም መጀመሩን በዲያብሎስ መፈተኑንና ዲያቢሎስንም ድል መንሣቱን ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ሳምንት ታስተምረናለች፡፡ በዚህች ቅድሰት በተባለች ሳምንት እሑድ የሚነበቡት የቅዳሴ ምንባባት የሚከተሉት ናቸው፡፡ ምንባባተ ቅድስት መልዕክታት፡ ፩ኛ ተሰሎቄ ፬፥፮-፲፫ ፩ኛ ጴጥሮስ ፩፥፲፫ - ፳፭ ግብረ ሐዋርያት፡ የሐዋ.ሥራ ፲፥፲፯ - ፴ ምስባክ መዝ ፺፭፥፭ “እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ አሚን ወሰናይት ቅድሜሁ ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ” ትርጓሜውም፡- “እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ፡፡ ምስጋናና ውበቱ በፊቱ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው፡፡” ወንጌል ማቴ ፮፥፲፮ - ፳፭ ይህ ጾም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም በመሆኑ፤ በዚህች በዕለተ ሰንበት(“ቅድስት”) በቤተክርስቲያን በመሰብሰብ ቃለ እግዚአብሔር በመስማት (በመማር)፣ ንስሐ ገብቶ ቅዱስ ቁርባን በመቀበል፣ የተጣላ በማስታረቅ፣ ያዘነ የተከዘ በማጽናናት፣ የታሰረ በመጠየቅ በአጠቃላይ በማቴ. ፳፭፥፴፭—፴፯ ላይ የተጠቀሱትን ምግባራትን በመፈጸም ለቱን (በዓሉን) ማክበር ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን ያሰጣል፡፡ ሰንበትን በሚገባ እንድናከብር የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

2 months, 3 weeks ago
EOTC TV
We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ሃሳብ አስታየት Or ማስታወቂያ - @AbusheCBot

● Welcome to Ethio music Channel

➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !

Last updated 1 month ago