Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

🦋የህይወት ሳይኮሎጂ🦋

Description
ትክክለኛ አስተሳሰብ ሲኖርህ ትክክለኛ ሰው ትሆናለህ promotion or any questions can you content 👉👉@wintagh

@Haadhakofqaalii
Advertising
We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month, 2 weeks ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 4 days, 23 hours ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 5 months, 1 week ago

1 week, 4 days ago

ሕይወታችሁን ለማስተካከል ወይም ለማበላሸት አንድ ነገር በቂ ነው!

አዎን! አንድ ነገር በቂ ነው! ካልተጠነቀቅን አንድ የተሳሳተ ነገር እድሜ ልካችንን የሚከተል መዘዝ ይዞ ይመጣል፡፡

1.  አንድ “የተሳሳተ” ሰው

• በብዙ ብልጽግና መኖር ስትችሉ በድህነት፣ በጤንነት መኖር ስትችሉ በበሽታ፣ በደስታ መኖር ስትችሉ በኃዘንና በቁዘማ እንድትኖሩ ሊደርጋችሁ ይችላል፡፡ የምትመርጡትን ሰው በጥንቃቄ ምረጡ፡፡

2.  አንድ የተሳሳተ አመለካከት

• የምታስተናግዱትን ሃሳብ፣ አመለካከትና ፍልፍና በጥንቃቄ ምረጡ፡፡

3.  አንድ የተሳሳተ ውሳኔ

• ሰው የሚኖረው ምርጫና ውሳኔውን ስለሆነና በተሳሳተ ምርጫችሁ ምክንያት የልተጻፈላችሁን ታሪክ ልትኖሩ ስለምትችሉ የምትመርጡትንና የምትወስኑትን ነገር በጥንቃቄ ምረጡ፡፡

4.  አንድ የተሳሳተ ልምምድ

• በጓደኛ ተጽእኖ፣ በ“ልሞክረው” እና በመሳሰሉት መንገዶች የምትገቡባቸውና የምትለማመዷቸው ነገሮች እድሜ ልክ የማይለቅ ልምምድ ውስጥ ይከታሉ፡፡

Join us @adviceeeeee

You can contact me
@wintagh

2 weeks, 3 days ago

የአሶሳ ዩኒቨርሲ ተማሪ የሆነችው ደራርቱ ለሜሳ የተባለች ግለሰብ በስለት ተወግታ ህይወቷ ማለፉ ተሰምቷል ::
EsatMereja🔥****
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነችው ደራርቱ ለሜሳ
የ4 ኛ አመት የጂኦግራፊ ዲፓርትመንት ተማሪ ስትሆን ከምትማርበት ዩኒቨርሲቲ እየወጣች በትርፍ ሰዓቷ ኮንስትራክሽን ውስጥ የምትሰራ ሲሆን ዛሬ ማለዳ ግንቦት 6 2016 ዓ.ም በስለት ተወግታ ህይወቷ አልፏል ::

ገዳዩም ወግቷት ሊያመልጥ ሲል በአከባቢው በነበሩት ህብረተሰብ በቁጥጥር ስር መዋል ችሏል::

የግድያው ምክኒያት እየተጣራ ሲሆን
የቅርብ ጓደኞቿ እንደተናገሩት ገዳዩ እንደሚወዳት ቢነግራትም የሷ ፍላጎት አለመሆኑን እንዳስረዳችውና የሱ ካልሆነች እንደሚገላት በተደጋጋሚ ይዝትባት እንደ ነበር ገልፀዋል ።

ለቤተሰቦቿ እና ለቅርብ ጓደኞቿ እና ወዳጆቿ መፅናናትን እንመኛለን::

EsatMereja🔥****
https://t.me/LAWOFETHIO

3 weeks ago

ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
EsatMereja🔥****

ሃሰተኛ መረጃ እና ከማህበረሰቡ መልካም ባህልና ወግ የተቃረኑ አፀያፊ የፈጠራ ታሪኮችን  በማህበራዊ ሚዲያ እያሰራጩ በህዝብ ላይ ውዥንብር እና መደናገርን የሚፈጥሩ ግለሰቦች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ ከመጠቀም ይልቅ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ብቻ ከእውነት የራቁ መሰረተ ቢስ የፈጠራ አፀያፊ  ወሬዎችን እየፈበረኩ በማሰራጨት የህዝብን ደህንነት ስጋት ላይ የሚጥሉ ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን  የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው የተለያዩ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት  የማህበረሰቡን ሥነ ልቦና የሚጎዱ የፈጠራ ታሪክ በማሰራጨት የተጠረጠሩ ስድስት ግለሰቦች በህዝብ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተይዘው በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል መቅደስ መብራት መኮንን የተባለችው ግለሰብ ሮሄ፣ ልዩነት፣ ጣዕም፣ አዲስ አለም፣  ዘይቤ፣ ህይወት፣ እይታ፣  እና ዩኒት ህይወት የተባሉ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት በስራ አስኪያጅነት ስትመራ የነበረች ናት ተብሏል፡፡

ብሩክ ወርቅነህ ጌታሰው የተባለ ግለሰብ ደግሞ ገፆቹን በምክትል ስራ አስኪያጅነት እና በአስተባባሪነት ሲመራ የነበረ ሲሆን ናትናኤል አበራ በቀለ፣ እየሩሳሌም አስማረ ምህረት እና ምህረት ያሲን ቲጋ የተባሉት ግለሰቦች ደግሞ በፕሮግራም አቅራቢነት እንዲሁም ናትናኤል ዮሃንስ አሸነፍ በካሜራ ባለሙያነት ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡  ከላይ ከተጠቀሱት ስምንት የዩቲዩብ ገፆች በተጨማሪ ክህሎት እና ሲንግል የተባሉ ሌሎች ሁለት የዩቲዩብ ገፆችም በዚያው ህንፃ ላይ የፈጠራ ወሬ ሲፈበርኩ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

ፖሊስ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ እና ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ ተከራይተው በሚሰሩበት ህንፃ 8ኛ እና 13ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮአቸው ላይ በህግ አግባብ ባደረገው ብርበራ የፈጠራ ወሬ ለመቅረፅ እና ለማሰራጨት የሚጠቀሙባቸው የኤሌክትሮኒክ እቃዎች  ተይዘዋል፡፡

ግለሰቦቹ መረጃውን ለማሰራጨት የሚያስችል ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የህጋዊነት ማረጋገጫም ሆነ ፈቃድ እንደሌላቸው በምርመራው ሂደት መረጋገጡንም ከየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
እነዚህ ተጠርጣሪዎች ሃሰተኛ እና የፈጠራ ወሬዎቹን የሚሰራጩት ታሪኩን ለሚተውኑላቸው ግለሰቦች ገንዘብ በመክፈል ሲሆን በወቅቱ ጉዳዩን በጥልቀት ሳይረዱ እና መረጃው ሳይኖራቸው የማያውቁትን የፈጠራ ታሪክ ሊሰሩ ለቀረፃ ስራ የተጠሩ ሌሎች ሶስት ሰዎችን  ፖሊስ አግኝቷል፡፡   

መሰል የውሽት ታሪኮችን ቀልብ በሚስብ መልኩ እያቀናበሩ በማሰራጨት በህብረተሰቡ ላይ መደናገርን የሚፈጥሩ ሌሎች ግለሰቦችም ተለይተው የታወቁ  እና በቁጥጥር ስር ለማዋል የክትትል ስራው ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

ህብረተሰቡ እንዲህ አይነት ከባህልም ከስነ ምግባርም ያፈነገጡ የፈጠራ ወሬዎችን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ በሚመለከትበት ወቅት ገፆቹን ከመከተል እንዲቆጠብ እና የሌሎች መረጃዎችንም ትክክለኛነት በማረጋገጥ ራሱን ከአላስፈላጊ መደናገር እንዲጠብቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

EsatMereja🔥****
https://t.me/LAWOFETHIO

2 months ago

#ቴሌግራም
# አራት_ቀን_ቀረው

የቴሌግራም አዲሱን ኖትኮይን መቼም ያልሰማ የለም። ሁሉም tab tab እያደረገ መሆኑ ያያቹ ወይንም የሰማቹህ ይመስለኛል። የቢትኮይን ዋጋ እየጨመረ እየጨመረ መሄድ ያሳሰባቸው የምስራቁ ሰዎች የቴሌግራሙ መስራች ወንድማማቾች ፓቬል ዱሮቭ ከትልቁ የዲጂታል ሳንቲም አቀናባሪ TON COIN ጋር ከዚ በፊት የገባውን ስምምነት ከወራት በፊት NOTCOIN በማለት እየተንቀሳቀሰበት ይገኛል።

በጥቂት ወራት ውስጥ ቢሊዮን የዲጂታል ሳንቲሞች የተሰበሰቡ ሲሆን ከ10 ሚሊዮን በላይ ሳንቲሞች ያለው ሰው ወደ ዶላር ከዛም ወደ ኢትዮጲያ ብር መየቀር ይችላል። ይህ ገንዘብ ባንዴ የሚመጣበት ሳይሆን ገንዘብ መስራት የሚያስችለውን የዲጂታል መገበባያ ሳንቲም tab tab እያደረጉ በመነካካት ብቻ የሚሰራ ነው።

ዲጂታል ነገሮች በጣም ቀላል እና ግልፅ ከመሆናቸው የተነሳ ብዙ ሰዎች ይህ ውሸት ቢመስላቸውም በዛው ልክ ቢሊዮን ሳንቲሞችን ያመረተው የቴሌግራሙ NOTCOIN ከመስራቹ ፓቬል ዱሮቭ እየመጣን ነው ፍንጭ በተጨማሪ ቴሌግራም የ Official Verification የሰማያዊ ምልክት አርማን ሰጥቶታል።

ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም ከገባቹ በውሃላ start በማለት አባል ስትሆኑ PLAY ስትሉት ደግሞ ሳንቲም መስራት ትችላላችሁ አስር ጊዜ በመነካካት ፣ እኛ በሌለን ጊዜ እየነካ የሚሰራ ሮቦት AutoBot በመግዛት ፣ ጓደኞቻችንን በመጋበዝ ብዙ የዲጂታል ሳንቲሞችን መሰብሰብ እንችላለን። በቀሪ አራት ቀን ውስጥ ሙሉበሙሉ ሳንቲሙ ለገበያ የሚለቀቅ ሲሆን አሁን በመቶ ዶላሮች እየተሸጠ ይገኛል። ቀላል ነው መነካካት ብዙዙዙዙዙ የሰበሰበ የሚሰጠውን ያገኛል። ሊንኩን በመጫን ወደ NOTCOIN የዲጂታል ሳንቲም መሰብሰቢያ መግባት ትችላላቹ PLAY!!!!

👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/notcoin_bot?start=r_578988_34826434
🎁 +2.5k Notcoin as a first-time gift
🎁🎁🎁 +50k Notcoin if you have Telegram Premium @PremiumBot

#EsatMereja*🔥***https://t.me/LAWOFETHIO

Telegram

Notcoin

Probably nothing @notcoin

[#ቴሌግራም](?q=%23%E1%89%B4%E1%88%8C%E1%8C%8D%E1%88%AB%E1%88%9D)
2 months, 2 weeks ago
**ለራሳችሁ ዋጋ ስጡ!**

ለራሳችሁ ዋጋ ስጡ!

አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች እኛን በምን መልኩ እንደሚያስተናግዱን (Treat እንደሚያደርጉን) የምናስተምራቸውና የምንፈቅድላቸው እኛው ራሳችን ነን፡፡

ራሳችንን ከናቅን ሰዎች እኛን ይንቁናል፣ ራሳችንን ስናከብር ደግሞ ያከብሩናል፡፡ ራሳችንን ርካሽ አድርገን ካሰብንና ልክ የትም መሄጃ እንደሌለው አይነት ሰው ሆነን ራሳችንን ካቀረብን ሰዎች እንደ ተራና የትም መሄጃ እንደሌለው ሰው ያስተናግዱናል፣ ለራሳችን ዋጋ ከሰጠን ደግሞ ዋጋ ይሰጡናል፡፡

ሰዎች በምን መልኩ እየቀረቧችሁና እያስተናገዷችሁ እንዳሉ ተመልከቱትና ምናልባት በዚያ መልክ እንዲቀርቧችሁና እንዲያስተናግዷችሁ የፈቀዳችሁት እናንተው የመሆናችሁን ጉዳይም በዚያው ለመቃኘት ሞክሩ፡፡

እናንተ ሳትፈቅዱላቸው ሰዎች ሊንቋችሁና በወረደ መልኩ ሊያስተናግዷችሁ አይችሉም፡፡ ከእናንተ ፈቃድ ውጪ በዚያ መልክ እንዳይቀርቧችሁ ማድረግ ባትችሉም ሁኔታው ልክ በማስያዝ ድርጊታቸው የመጀመሪያና የመጨረሻ እንዲሆን የማድረግ መብቱም ሆነ አቅሙ አላችሁ፡፡

ፈጣሪ ከሰጣችሁ “ሰውነት” በታች አትኑሩ!

Have Great Day
Join us @adviceeeeee

You can contact me
@wintagh

2 months, 2 weeks ago

በጫጫታ የተደበቀ ማንነት!

የአንድ ሰው ከልብ የመነጨ ጥያቄ . . .
ጠዋት እንደነቃሁ ከአልጋዬ ሳልወጣ የመጀመሪያ ስራዬ ሶሻል ሚዲያ በመክፈት ምን እንደተለጠፈና ምን እንደተባለ ማየትና ማድመጥ ነው፡፡ ከአልጋዬ ወጥቼ ለመውጣት ስዘጋጅ የጆሮ ማድመጫ (Earphone) በጆሮዎቼ ላይ ሰክቼ ከሰዎች ጋር እያወራሁ መዘገጃጀት አዘውትራለሁ፡፡

ከቤቴ ስወጣም አሁንም የጆሮ ማድመጫ (Earphone) በጆሮዎቼ ላይ ሰክቼ ጠዋት የጀመርኩትን የሚዲያ ጉብኝት መቀጠል ወይም የሞቀ ሙዚቃ እያደመጡ መሄድ የየእለት ልምምዴ ነው፡፡

ስራዬ ቦታ ግር-ግር ነው፡፡ በሻይ ጊዜ ካፌው ጫጫታ ነው፡፡ ምሳ የምንሄደው በቡድን ሲሆን እዚያም ካለው ጫጫታ ጋር እኛም እንደመርና እየተንጫጫን እንመገባለን፡፡

ከስራ በኋላ ወደቤቴ ከመሄዴ በፊት ከጓደኞቼ ጋር ስንንጫጫ አምሽተን እቤት እገባለሁ፡፡ ማታም እቤት ስገባ ቴሌቭዥኑ ካልጮኸ ቅር ይለኛል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ቲቪው እንደበራና እንዳወራ ሲያድር ደስ ይለኛል፡፡

ለማሰብ፣ ለማሰላሰል፣ ለማቀድ፣ ራስን ለማየት . . . ጊዜ እስከማጣ ደረስ  በጫጫታ ተደብቄ ይሆን?   

ማናልባት ትኩረት የማጣው፣ አንድን ነገር የማልጀምረው፣ የጀመርኩትን ነገር የማልቀጥለውና የማልጨርሰው፣ ሕይወቴ ከእለት እለት እድገት የማይታይበት ለዚያ ይሆን?

ከአንዱ ጫጫታ ወደሌላው፣ ከአንዱ ማሕበራዊ ግንኙነት ወደሌላው፣ ከአንዱ የማሕበራዊ ሚዲያ ወደሌላው .  . . የሚል ሰው ለራሱ የማሰቢያ ጊዜ ስማያገኝ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምን ያህል ኋላ እንደቀረ ይደርስበታል፡፡ ይህንን ለማረም ከተፈለገ . . .

1.  በቀን ውስጥ ቢያንስ 30 ደቂቃ፣ ከተቻለ የአንድ ሰዓት ጊዜ በመውሰድ ማሰብ፣ ራስን ማየት፣ ስራን መገምገም፣ እቅድ ማውጣ፡፡

2.  የነገን እቅድ ማታ አውጥቶ ማደርና ጠዋት ወደ ስራ ወይም ወደ ማሕበራዊ ሕይወት ከመሰማራት በፊት የማታውን እቅድ አየት በማድረግ ማስታወስ፡፡

3.  ትኩረታችንን፣ ስሜታችንንና ጊዜያችንን የምንሰጥበት ሁኔታ በጥንቃቄ መምረጥ፡፡

4.  ለብቻ ስንሆን የሚያስጨንቀንን ሃሳብ ከመሸሽ ይልቅ መጋፈጥና መፍትሄ መፈለግ፡፡ 

Have Great Day
Join us @adviceeeeee

You can contact me
@wintagh

4 months ago
**" ሁሉም ሰው ምቾት ይዞት ነው …

" ሁሉም ሰው ምቾት ይዞት ነው እንጂ ፊሪ አይደለም "

ምንም አማራጭ የሌለው ልጅ እና ሁሉ ነገር የተሟላለት ልጅ እኩል ፈተና ውስጥ ቢገቡ የመመለስ እድላቸው እኩል አይሆንም !

የሆነን አዲስ ነገር ለመጀመር ወደኋላ የምንለው ወደኋላ የምንልበት መደገፊያ ስላለን ነው መደገፍያ ባይኖረን ያለንን አማራጭ በሙሉ እንጠቀም ነበር

ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏

Have Great Day
Join us @adviceeeeee

You can contact me
@wintagh

4 months, 1 week ago
**ብቻ ወስን !**

ብቻ ወስን !

ፈጣሪ ሁሌም ቢሆን ያንተን ውሳኔ ነው የሚጠብቀው ፤ አየህ ወስነህ ከጀመርክ እርሱም ወስኖ ያግዝኋል የእውነት ከለፋህ የእውነት ውጤት ይሰጥኋል ከልብህ ካሻህ የልብህን የመሻትህን ታገኛለህ ብቻ የምትፈልገውን የምታደርገውን ወስን !

ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏

Have Great Day
Join us @adviceeeeee

You can contact me
@wintagh

6 months, 1 week ago
ሰዎች ምን እንደሚሉ ወይም ሰዎች ስለሚያስቡት …

ሰዎች ምን እንደሚሉ ወይም ሰዎች ስለሚያስቡት አይጨነቁ። እራስህን ሁን.
ብሬት ሃል°°
joun us  @adviceeeeee
◉◉◉◉◎◎           ●●◉◉◉◉
ሀሳብ እና አስተያየቶን በዚህ @wintagh ያጋሩን።

መልካም ምሽት🥰

We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month, 2 weeks ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 4 days, 23 hours ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 5 months, 1 week ago