Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

Description
🔨እጅግ ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ትምህርቶች
💵የ ኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭ እና ገዢ ሚገናኙበት
📐ውብ ውብ የ ቤት ዲዛይናኖች
💻ሶፍትዌሮችና ሴታፖችን
📙መፅሃፍቶች
🎬ቪድዮዎቾ ምታገኙበት ምርጥ ቻናል

📨ሃሳብ እና ኣስተያየት @ETCONpBOT ፃፉልን

📌ጨረታ ና ስራ @ETCONpWORK
📃 ለ መወያያ @COTMp

📍ዲጂታል ቤተ መፅሃፍ:- @ETCONpDigitalLibrary_Bot
Advertising
We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 1 week ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 1 week, 6 days ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 5 days, 16 hours ago

4 days, 16 hours ago

ETCONP TRIVIA #6 As we all know the strength of concrete has many factors one of thr factor that affects the strength of concrete is W/C( water cement ratio) ... NOW my question is what happens is W/C is lesser ? What happens if W/C is higher ? #share for…

WhatsApp.com

ETCONP | WhatsApp Channel

ETCONP WhatsApp Channel. Ethiopian construction work professionals. 0 followers

4 days, 16 hours ago

ETCONP TRIVIA #6

As we all know the strength of concrete has many factors one of thr factor that affects the strength of concrete is W/C( water cement ratio) ... NOW my question is what happens is W/C is lesser ? What happens if W/C is higher ?

#share for content like this

Follow us on 👇🏿👇🏻👇🏼👇🏽👇🏾👇

WhatsApp channel :- https://whatsapp.com/channel/0029VafkZEJ7dmefGtvKWL2C

Telegram:- https://t.me/ETCONp

YouTube:- https://www.youtube.com/@ETHIOCONp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

X formerly (Twitter):- https://x.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg

WhatsApp.com

ETCONP | WhatsApp Channel

ETCONP WhatsApp Channel. Ethiopian construction work professionals. 0 followers

4 days, 17 hours ago

👉በግንባታ ላይ ያሉ የመስኖ ፕሮጀክቶች
ለማጠናቀቅ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ይጠይቃሉ

🚧ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ ግማሽ ሚሊዮን ሄክታር ማልማት ያስችላሉ ተብሏል

🔰በግንባታ ላይ የሚገኙ የመስኖ ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቁ ግማሽ ሚሊዮን ሄክታር የሚጠጋ መሬት ማልማት እንደሚያስችሉ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

🔰የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብዙነህ ቶልቻ እንደገለጹት፤ የ28 መካከለኛና የሰፋፊ የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ እየተከነወነ ሲሆን በተጨማሪ የ25 መስኖ ልማት ፕሮጀክት የጥናትና ዲዛይን ሥራዎች ሂደት ላይ ናቸው።

ፕሮጀክቶቹን ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅም አሁን ባለው የገበያ ዋጋ 100 ቢሊዮን ብር ወጪ ይጠይቃሉ ሲሉ አቶ ብዙነህ አመላክተዋል።

❇️ባለፉት ዘጠኝ ወራት ጥናትና ዲዛይን ላይ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች ውስጥ የሦስት ፕሮጀክቶች ጥናት ዲዛይን ተጠናቋል ያሉት አቶ ብዙነህ፤ በተጨማሪ የሁለት ፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይን ሥራቸው በተያዘው ዓመት መጨረሻ ላይ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ጠቁመዋል።

📌በፀጥታ ችግር ምክንያት ግንባታቸው የተስተጓጎሉ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ በተለያዩ ችግሮች የበለስ መስኖ ልማት ፐሮጀክት ጥናትና ዲዛይን ሥራ አፈጻጸም 30 በመቶ እንዲሁም የጎርጎራ መስኖ ልማት ፕሮጀክት የጥናትና ዲዛይን ሥራም 57 በመቶ ላይ ቆሟል ብለዋል፡፡

በአጠቃላይ በፀጥታና በሌሎችም ጉዳዮች ምክንያት የዘጠኝ ፕሮጀክቶች ጥናት ዲዛይን ሥራ ተስተጓጉሏል ሲሉ ገልጸዋል።

በግንባታ ሂደት ላይ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች መካካል ከጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ አንገር፣ የላይኛው ጉደር፣ ካዛና የላይኛው ርብ ግድብን ጨምሮ ስምንት ፕሮጀክች ላይ መስተጓጎል ማጋጠሙን አስረድተዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሚገኙ ሁለት ፕሮጀክቶች በተቋራጩ ድክመት የተነሳ በመዘግየታቸው ለሌላ ተቋራጭ ተሰጥተው ሥራው ለማከናወን በሂደት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

አቶ ብዙነህ እንዳስታወቁት፤ ስምንት የመስኖ ልማት ግንባታ ፕሮጀክቶች በጥሩ አፈጻጸም ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በጥሩ አፈጻጸም ላይ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች አንዱ የታችኛው ርብ መስኖ ግድብ ይጠቀሳል፤ አፈጻጸሙ ከ92 በመቶ በላይ ደርሷል፡፡

የመስኖ ግድቡ ግንባታ ሥራ በዚህ በጀት ዓመት መጨረሻ አልያም በቀጣዩ በጀት ዓመት መጀመሪያ ላይ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ ጠቁመዋል።

በሁለት ሎት ተከፍሎ እየተገነባ የሚገኘው የወልመል የመስኖ ልማትም ፕሮጀክትም ሌላኛው ጥሩ አፈጻጸም የታየበት ፕሮጀክት መሆኑን አንስተው፤ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በግድቡ አማካኝነት ሰባት ሺህ ሄክታር መሬት ይለማል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ 13 የመስኖ ፕሮጀክቶችን በከፊል ሥራ ለማስጀመር ታቅዶ ሲሠራ መቆየቱን አስታውሰው፤ በዚህም 29 ሺህ 970 ሄክታር መሬት ማልማት የሚያስችል አቅም ለመፍጠር ሲሠራ እንደነበር ተናግረዋል።

በበጀት ዓመቱ ዘጠነኛው ወር ድረስ 35 ሺህ 700 ሄክታር መሬት ማልማት የሚያስችል አቅም መፈጠሩንም ገልጸዋል።

@etconp

1 week, 3 days ago
***👉***Iconic Tower ይባላል ፤ በአፍሪካ ረጅሙ …

👉Iconic Tower ይባላል ፤ በአፍሪካ ረጅሙ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ነው ፤ ቁመት 400 ሜትር ሲሆን፣ 77 ወለሎች አሉት።

🚧ጠቅላላ የወለሎቹ ስፋት ደግሞ 250 ሺህ ስኩዌር ሜትር ነው።

✳️ይህ ሕንፃ በግብጽ ከዋና ከተማዋ ካይሮ ወጣ ብሎ ከተገነባው አዲሱ የአስተዳደር ዋና ከተማ ውስጥ ከተገነቡ 20 ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን፣ በአመዛኙ የቢሮ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል።

@etconp

1 week, 3 days ago
***👉***የቻይና ዘመናዊ የባህር የውስጥ ለውስጥ አቋራጭ …

👉የቻይና ዘመናዊ የባህር የውስጥ ለውስጥ አቋራጭ መንገድ

🚧በደቡብ ቻይና ጓንግዶንግ ግዛት የተገነባው የቻይና አዲስ የባህር ውስጥ አቋራጭ ከ 6 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ዋሻ ሼንዘንን እና ዞንግሻንን የሚያገናኘው 24 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው አውራ ጎዳና አካል መሆኑ ተነግሯል።

✳️የሼንዘን-ዞንግሻን አገናኝ መንገድ በጓንግዶንግ- ሆንግ ኮንግ- ማካኦ ታላቁ የባህር ወሽመጥ ዋና የትራንስፖርት ፕሮጀክት መሆኑ ተመላክቷል።

❇️አንድ የውሃ ውስጥ ዋሻ፣ ሁለት ድልድይ እና ሁለት ሰው ሰራሽ ደሴቶችን ያቀፈ ሲሆን ይህም በዓለም ላይ ካሉ እጅግ ፈታኝ የባህር አቋራጭ ፕሮጀክቶች አንዱ ያደርገዋል ተብሏል።

✳️ማቋረጫው በፈረንጆቹ 2024 ለትራፊክ ክፍት የተደረገ ሲሆን÷ ከሼንዘን ወደ ዞንግሻን ይወስድ የነበረውን ሁለት ሰአት ወደ 20 ደቂቃ እንደቀነሰም ተገልጿል።

🔰የሼንዘን-ዞንግሻን አገናኝ መንገድ እንደ ሆንግ ኮንግ-ዙሃይ-ማካኦ ድልድይ ካሉ ነባር መስመሮች ጋር በመጣመር በታላቁ የባህር ወሽመጥ አካባቢ የባህር አቋራጭ እና የወንዞች መተላለፊያ አውታር እንደሚፈጥርም ነው የተመላከተው፡፡

✳️ይህም የከተማዋን ትስስር ያሳድጋል ሲሉ የጓንግዶንግ ግዛት ኮሙኒኬሽን ቡድን ኃላፊ ዴንግ ዢዋ መናገራቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።

@etconp

1 week, 3 days ago
New Robin plate compactor

New Robin plate compactor

- 90KG

- 00 condition

Price 80,000 birr

Call :- 0920652543

በ ብዛት አለ

4 months, 1 week ago

👉በመዲናዋ የሚገኙ ከ30 ሺህ በላይ ግንባታዎች ላይ የጥራትና ቁጥጥር ሥራ እየተሠራ ነ

🌟በመዲናዋ በሂደት ላይ የሚገኙ ከ30ሺህ በላይ ግንባታዎች ላይ የጥራት ደረጃና የደህንነት ቁጥጥር እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።

🚧በየመንገዱ የተሰቀሉ ከ45ሺህ በላይ ሕገወጥ ማስታወቂያዎች ተነስተው ወደዲጂታል ሥርዓት እንዲገቡ አቅጣጫ ተቀምጧል።

▶️የባለስልጣኑ የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር ከማል ጀማል (ኢ/ር) ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በአዲስ አበባ በአጠቃላይ ከወረዳ ጀምሮ እስከ ማዕከል በተለያዩ ግለሰቦችና ተቋማት አማካኝነት ከ30ሺህ በላይ ግንባታዎች እየተከናወኑ ይገኛል።

▶️ግንባታዎቹ ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በተቋም ደረጃ ልዩ እቅድ ተዘጋጅቶ ክትትል እየተደረገ ነው ያሉት ኢንጂነር ከማል፤ የግንባታ ጥራትና ደህንነት ጥንቃቄዎችን ከግምት ውስጥ ባስገባ መንገድ የፍቃድ አሰጣጥና የክትትል ሥርዓቱ በወረዳ፣ በክፍለ ከተማና በማዕከል ደረጃ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። የህንጻ ግንባታዎች በተዘጋጀላቸው ዲዛይንና ቦታ ላይ መከናወናቸውን የሚከታተል ክፍል መኖሩንና፤ ማንኛውም አልሚ የግንባታ ደህንነት መሟላቱን አረጋግጦ ህንጻውን ማጠናቀቅ እንዳለበት አመላክተዋል።

ከተማዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ እየተሠራ ባለው ሥራ የማስታወቂያ፣ የመሰረተ ልማትና የሌሎችንም ግንባታዎች ለመቆጣጠር በልዩ ሁኔታ ከጥቅምት ወር ጀምሮ እቅድ ወጥቶ ከማዕከል እስከ ወረዳ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል። በዋና ዋና መስመሮች የከተማ ገጽታን የሚያበላሹ የአጥር ግንባታዎች እንዲስተካከሉ፣ የህንጻ ሽፋኖች ደረጃቸውን እንዲጠብቁና በግንባታ ወቅት የሰራተኞች ደህንነት እንዲጠበቅ ክትትል እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።

🖱ኢንጂነር ከማል እንዳመለከቱት፤ የህንጻ ሽፋን፣ የአጥር ደረጃ፣ የግንባታ ግብዓትና ተረፈ ምርት በመንገድ ላይ የሚያስቀምጡና በህንጻ ደህንነት ላይ ችግር የተገኘባቸው አልሚዎች፣ የግንባታ አማካሪዎችና ኮንትራክተሮች ላይ የማስተካከያ ርምጃ እየተወሰደ ይገኛል።

የግንባታ ግብዓቶች በእግረኛ መንገዶች ላይ በሚያስቀምጡ በመሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ያደረሱ ሦስት ሺህ የሚጠጉ አካላት ላይ ርምጃ በመውሰድ ግብዓቶቹን የማንሳት ሥራ ተከናውኗል ሲሉ አስረድተዋል።

በተጨማሪ የከተማዋን ውበት በማበላሸት በየመንገዱ የተሰቀሉ ከ45ሺህ በላይ ማስታወቂያዎች እንዲነሱና በዋና ዋና መንገዶች ላይ በዲጂታል ማስታወቂያዎች እንዲተኩ መደረጉን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

🚧በመንገድ ዳር በተለያዩ ተለጣፊና ተንጠልጣይ መንገዶች የሚሰቀሉ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ማስታወቂያዎች ህጋዊነታቸው ያልተረጋገጡና የመንገድ ደህንነት ህግን ያላከበሩ በመሆናቸው በቀጣይም የማስተካከሉ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በከተማዋ ዋና ዋና አካባቢዎች የተሰቀሉ ዲጂታል የማስታወቂያ ቦርዶች ዘመናዊነትን የተላበሱና በውበትም የተመረጡ በመሆናቸው ማንኛውም ማስታወቂያ ያለው አካል ከሚመለከተው ክፍል ጋር በመነጋገር ወደዘመናዊ ሥርዓቱ መግባት እንደሚችል አስረድተዋል።

Via ኢ ፕ ድ

@etconp

4 months, 1 week ago

👉WHAT IS QUANTITY SURVEYING

➡️Quantity surveying means generally materials take off preparation and measuring of quantities Such as length,Area,Volumes and Pcs for Construction projects

🏷Quantity Surveying can be cover different tasks like

*⃣preparation of specification.

*⃣Taking measurements of Construction works.

*⃣preparation of approximate cost estimate at the very early stage of the project.

*⃣preparation of detail cost estimate at different stages.

*⃣Valuation of property.

🏷PURPOSE OF QUANTITY SURVEYING

Assist the client to have an accurate estimate of volume of work as well as the required budget.

to assist in the accurate preparation of tenders,by providing uniform Measuring of quantity.

To give an accurate checklist of work accomplished.

To assist in the certification of payments.

To give insight into the required variation work amounts.

#QuantitySurveying

@etconp

4 months, 1 week ago
4 months, 2 weeks ago
We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 1 week ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 1 week, 6 days ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 5 days, 16 hours ago