Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

ከ ደጋጎቹ ዓለም

Description
Comment @Kedegagochu0bot
Advertising
We recommend to visit

Your own Memes centre.

Memes | Memes | Memes

Last updated 2 years, 10 months ago

« Le complotisme en s’amusant »
____________
Je ne vous demanderai jamais rien.
Donc si un connard vient vous parler en se faisant passer pour moi et en vous demandant des trucs bloquez-le immédiatement

Last updated 1 week ago

Uniquement des vidéos... 😁❤️

Last updated 3 days, 17 hours ago

2 weeks, 6 days ago

ከሚገርመው ነገር ውስጥ

አሏህን አውቀሃው አትወደውም፤ ወደርሱ የሚጣሩትን እየሰማህ መልስ ከመስጠት ግን ወደኋላ ትላለህ። ከርሱ ጋር በመሆን የምታገኘውን ትርፍ እያወቅክ ከርሱ ውጪ ላለ ነገር ስትለፋ ትኖራለህ። የቁጣውን ሃይል ከማወቅህ ጋር ጀርባ ሰጥተህ ትሄዳለህ።እርሱን በመታዘዝ የሚገኘውን ጣእም ትተህ ወንጀል በመስራት የሚደርስብህን የብቸኝነትን ህመም ትመርጣለህ። ልብህን በአልባሌ ንግግሮች ለማስደሰት እየጣርክ በርሱ ንግግር፣ እርሱን በማስታወስ ልብህን ስለማስፋት ግን ቅንጣት አታስብም። ከርሱ ውጪ ባለ ነገር ላይ ልብህን በማንጠልጠልህ የደረሰብህን ወይም የሚደርስብህን የልብ ስብራት፣ ወደርሱ ከመመለስ ውጪ የማይወገደውን ባዶነት እያወቅክ ወደርሱ ግን አትሸሽም።
ከዚህ የበለጠ የሚያስደንቀው ግን እርሱ ሊኖርህ እንደሚገባ እና እርሱን በጣም እንደምትፈልግ እያወቅክ፤ ከሱ እየራቅክ ከእርሱ የሚያርቅህን ነገር መፈለግህ ነው።

ኢብኑል ቀይ-ዩም رحمه الله

2 weeks, 6 days ago

የሰዎችን ነገር በመከታተል፣በርሱ ላይ በደረሰበት ነገር በመቆጣት፣ ወይ መጥፎ ነገርን በመጠበቅ፣ አሏህ በርሱ ላይ የዋለለትን ፀጋ በመዘንጋት በራሱ ላይ ጭንቀትን እና ሃዘንን የሚያመጣ ብዙ ነው።

እንዲህ አይነት ባህሪ ህይወትህን ከማበላሸት ውጪ ምንም የሚያመጣው ነገር የለም።

አሏህ በሰጠህ ፀጋ ደስተኛ ለመሆን ሞክር፣ በ አሏህ ላይ መልካም ጥርጣሬ ይኑርህ።

3 weeks, 2 days ago

በጣም ታጋሽ ሰው ብሎ ማለት የሆነ ጊዜ አለመግባባት ሊፈጠር ቢችልስ ከሚል መነሻ ሀሳብ
"እሱ ማለት እኔው ነኝ ብሎ ለሚገልጸው የልብ ወዳጁ እንኳ ሚስጥሩን የማይናገር ሰው ነው።"

ረውዶቱል ዑቀላእ

በርግጥ በዚህ ዘመን ሚስጥርን አይደለም ለወዳጅና ለቅርብ የስጋ ቤተሰብ መንገር ራሱ ዋጋ ያስከፍላል።

3 weeks, 4 days ago

ዱንያ ላይ ኖሮ የማይፈተን የለም። ለፈተናው ከሚሰጡት ምላሽ አንፃር ሰዎች በ አራት ይከፈላሉ ይለናል ኢብኑል ቀይ-ዩም رحمه الله

1- ራሳቸውን በዳዮች ናቸው። በደረሰባቸው ፈተና ሁሉ ያማርራሉ። ምንዳም አያገኙ ፈተናም እየበረታባቸው ይሄዳል።

2- ታጋሾች ናቸው። እነዚህ የሚመነዱት ያለገደብ ነው።  ሽልማቱን በዚህ አላቆመም። በህመም ከተፈተኑ ከህመም በፊት ይሰሩት የነበረው መልካም ስራ በህመም ላይ እያሉም እንዲመዘገብላቸው አድርጓል። ከ ጌታቸው ዘንድ ውዳሴ፣ እዝነት በነርሱ ላይ ይወርዳል፣ ነፃ ከሚወጡት፣ ወደ ቀጥተኛው ጎዳና ከተመሩቱም ይሆናሉ።

3- የ አሏህን ውሳኔ ወዳጆች ናቸው። ታጋሽ መሆናቸውን በራሱ ይወዳሉ።የ አሏህን ውሳኔ የወደደ አሏህም ይወደዋል።

4- አመስጋኞች ናቸው። በተፈተኑበት ፈተና ስለሚመነዱ፣ መታገስን፣ የ አሏህን ውሳኔ ለመውደድ መታደልን ስለተሰጡ ያመሰግናሉ። እንዚህኞቹ ከፍተኛ የተባለውን ደረጃ የተቆናጠጡ ናቸው። ጥሪያቸው ወዲያው ተመላሽ የሚሆንላቸው ድንቅ ሰዎች፣በቁጥር ያነሱ በደረጃ ግን ከፍ ያሉ!

አሏህ ሆይ ለፈተናዎች ሁሉ ታጋሽ፣ ውሳኔህን ወዳጆች፣ እንዲሁም አመስጋኞች አድርገን።

3 weeks, 4 days ago

ሶስት አይነት ቦታዎች ላይ ዝምታን ምረጥ ይላሉ

1-በተቆጣህበት ሰዓት
2-ሰዎች ለንግግርህ ምንም አይነት ቦታ በማይሰጡበት ሰዓት
3-ማዳመጥ በፈለግክበት ሰዓት

3 weeks, 6 days ago

ወጭ የሌለበት መልካም ስራ ቢኖር #ፈገግታ ነው።

ሱዐይር ቢን ኺምስ ን
ፈገግታህን ምን አበዛው!!! ብለው ሲያደንቁት #ወጪ የለበትምና ነው ብሎ እንደመለሰላቸው ተዘግቧልል።

አንዳንዴ ዉስጣችን እርር ትክን ብሎ ወዳጃችን እንዳይረበሽ ጠላታችን ደግሞ እንዳይደሰት ብለን ፈገግታ በፈገግታ እንሆናለን።

ማንን ደስ እንድለው ነው የምንከፋው!!!

2 months, 3 weeks ago

ያህያ ቢን ሰዒድ رحمه الله እንዲህ ብሏል:- አንድ ጊዜ ዱንያዊ ነገር ቀረበልኝና ቀንና ማታ አሏህ ያንን ነገር እንዲሰጠኝ መጠየቅን ተያያዝኩት። እና ይህን በማድረጌ ራሴን ወቀስኩ በራሴም አዘንኩ። ይህንንም ጉዳይ ለ ኻሊድ ቢን አቢ ዒምራን ነገርኩት። እርሱም እንዲህ አለኝ

"ይህን በማድረግህ ምንም አያሳስብህ፤ አሏህ አንድን ሰው በጉዳዩ ላይ ሊባርክለት ሲፈልግ፣ ስለዚያ ነገር ዱዓእ እንዲያደርግ ይፈቅድለታል መባሉን ሰምቻለሁ" አለ።

رياض النفوس، لأبي بكر المالكي

እናም ምንንም ነገር ከመጠየቅ አትፈሩ።መርፌም ቢሆን!

2 months, 3 weeks ago

የሰራንበት ቢሆን ምነኛ ይጠቅመን ነበር!

አንድ ሙስሊም በዚህ ረመዻን ውስጥ በተለየ መልኩ ምንም ሳይሳነፍባቸው ሊያደርጋቸው የሚገቡ ዱዓዎች ሊኖሩት ይገባል።ሙጭጭ የሚልባት በሌሊቱ አንድ ሶስተኛ ላይ፣ በ ሁለት አዛኖች መኃል፣ ከ ኢፍጣር በፊት፣ ቀኑን ሙሉ ሊያደርጋቸው ይገባል።

እንደው ዱዓህ ምናለ ጀነተል ፊርደውስን መጠየቅ ቢሆን፣ የረሱል صلي الله عليه وسلم ጎረቤት መሆን፣ ወይም ባለህበት ሁሉ የተባረክ እንዲያደርግህ መጠየቅ ቢሆን፣ ወይም ልብህን መበላሸት የሌለበት አይነት መስተካከል እንዲያስተካክልህ፣ወይ እስክትገኛኘው ድረስ የወደደህ እንዲያደርግህ፣ ጠቃሚ እውቀትን ከመልካም ስራ ጋር እንዲያድልህ ቢሆን፣ ወይም ቁርዓንን መሃፈዝን በዚህም እንዲያከብርህ፣ ወይ ደግሞ ዝርያህን በሙሉ ደጋግ እንዲያደርግልህ ብታደርገው ምን ችግር አለው?!

የሆነን ነገር መጠየቅ ላይ ሙጭጭ እንድትል ካደረገህ፣ በዚያ ላይም ካመላከተህ፣ ልብህን ለዚህ ከከፈተልህ አብሽር የሚያስደስትህን ነገር ተስፋ አድርግ፣ በዚህ ሙጭጭ ብለህ እንድትጠይቅ ያደርገህ ሊያከብርህ እንደሆነ እወቅ።

ይህን ጠለቅ ያለ የ ኢብኑ ተይሚያን ንግግር ልብ በል።
"ለ አንድ ባርያ አሏህ መልካምን ሲያስብለት፣ ዱዓእ ላይ እንዲበረታ፣ በርሱ እንዲታገዝ ያደርገዋል። ይህን ዱዓእ እና በርሱ መታገዝን ደግሞ ለርሱ ላሰበለት መልካም ነገር ምክንያት እንዲሆን ያደርግለታል።

(اقتضاء الصراط المستقيم)

2 months, 3 weeks ago

ልብ ካላልናቸው ጉዳዮች ውስጥ ዱዓችን ተቀባይነት ያላገኘበትን ምክንያት ልብ አለማለት አንዱ ነው።

"አንድ ሙእሚን ዱዓእ አድርጎ ሲዘገይበት፣ ከብዙ ጊዜ ልመና ቡሃላ ተስፋ ሲቆርጥ፣ ዱዓው ተቀባይነት ያገኘበትን ምልክት ሲያጣ፣ ወደ ነፍሱ መለስ ብሎ ነፍሱን ይወቅሳል
ይህ ሁሉ የሆነው ባንቺ ነው ይላታል፣በ ውስጥሽ መልካም ነገር ቢኖር ኖሮ በተመለሰልኝ ነበር ብሎ ይወቅሳል። ይህ ነፍሱን መውቀሱ በ አሏህ ዘንድ ከብዙ አምልኮዎች በላይ ተወዳጅ ነው። ይህ የባሪያው ድርጊት ለ አሏህ ልቦናው የተሰበረ፣ ፈተና የተገባቸው፣ ጥሪያቸው ደግሞ ከሚዘገይባቸው ሰዎች እንደሆነ አምኖ እንዲቀበል ያደርገዋል። ታድያ ያን ጊዜ ነው ጥሪው ፈጥኖ ምላሽ የሚያገኘው፣ ከ ገባበት አጣብቂኝ ነፃ የሚወጣው። የ ላቀው አሏህ ልቦናቸው ለሱ ሲሉ ከተሰባረባቸው ጋር ነውና።ምላሹም ለነርሱ የፍጠነ ነው።"

ኢብኑ ረጀብ رحمه الله

3 months ago

ይበልጡን አሏህ ያውቃል

ሙታኖች ረመዻን ሲመጣ ልክ እንደኛው ደስ ይላቸዋል ተብሎ ይታሰባል፣ በየመሳጂዶቹ በየሌሊቱ ዱዓእ ይደረግላቸዋል። የታዘነለት ኡማ፣ ኃለኞቹ ቀድመው ለሞቱት ዱዓእ ያደርጋሉ።

ነገ ተራችን ሲደርስ ማን ያውቃል የታዘነለት ኡማ ለኛም ያደርግ ይሆናል!

اللهم اغفر لنا ولآبائنا وأمهاتنا والمسلمين

We recommend to visit

Your own Memes centre.

Memes | Memes | Memes

Last updated 2 years, 10 months ago

« Le complotisme en s’amusant »
____________
Je ne vous demanderai jamais rien.
Donc si un connard vient vous parler en se faisant passer pour moi et en vous demandant des trucs bloquez-le immédiatement

Last updated 1 week ago

Uniquement des vidéos... 😁❤️

Last updated 3 days, 17 hours ago