ስንክሳር

Description
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Advertising
We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month, 2 weeks ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 4 days, 23 hours ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 5 months, 1 week ago

1 month, 1 week ago
1 year, 1 month ago

ፊርማ ለወዳጅ

ለመላው አብሮ አደጎች ፣ አብሮ አገልጋዮች ፣ ክላስ ሜቶች ፣ ወዳጆችና የመንፈስ ልጆች በሙሉ።

አንዳንዶቻችሁ በቅርብ ለገበያ የቀረበውን መጽሐፌን " አዘጋጁ ካልፈረመበት አንገዛም ሙተን እንገኛለን" ማለታችሁን ሰምቻለሁ። ሌሎቻችሁ ደግሞ "ለበዓል መጥተን ሰኞ ፣ ማክሰኞ ሂያጅ ነን። መጽሐፉን አስቀምጥልን" እያላችሁ በውስጥ መስመር እየወተወታችሁኝ ነው። እኔ የሺህ ወዳጅ ወንድማችሁ ወገቤ እስቲንቀጠቀጥ ጥፌ ማዘጋጀቴ አንሶ እናንተን እግር በእግር እየተከተልኩ መጣፍ ማቀብልበት ጊዜውም ጉልበቱም የለኝምና የግቢ ጉባኤ ፣ የዓለም ት/ቤት ፣ የፕሪፕ ፣ የሚካኤልና የሌላም ሌላም የሰፈር ወዳጅ ፣ ጓደኛ ፣ ደቀ መዝሙርና ደቂቀ መዝሙር ሁሉ በትንሣኤ ዋዜማ በቀዳም ሥዑር ዕለት በደብረ መድኃኒት ሰ/ት/ቤት አዳራሽ ከ4 ሰዓት ጀምሮ ከትተህ ላግኝህ። ማኅተምና ፊርማዬን ከስምህ ጋር ከትቤ እንዳስፈላጊነቱም በሥዕል አስውቤ ዘላለማዊ የወዳጅነት ማስታወሻ ይሆን ዘንድ መጽሐፈ መሠረትን አበረክትልሃለሁ። መርኃ ግብር አይደለም ደግሞ መጥቶ መሄድ ነው። አንድ የጋራ መገናኛ ለመፍጠር ያመች ዘንድ ነው። ማን ያውቃል በስንት እግዚኦታ ፣ ሠርግና ምርቃት መገናኘት ያልሆነለትን ጀማ ማገናኛ ሰበብ ይሆናል። ዘር ፣ ቀለም ፣ ጾታ ፣ እድሜ ፣ ባች ፣ ጸባይ ፣ የአመራርነትና የሥራ እርከን አይለይም። "ከሣችን አውቀዋለሁ" የሚል ሁሉ ጎራ ይበል።
https://www.instagram.com/p/Cq8b-10oXh8/?igshid=MDJmNzVkMjY=

Instagram

41 Likes, 1 Comments - ከሣቴ ብርሃን (@dn.\_dr.\_kesatebirhan) on Instagram: "ፊርማ ለወዳጅ ለመላው አብሮ አደጎች ፣ አብሮ አገልጋዮች ፣ ...

ፊርማ ለወዳጅ
1 year, 2 months ago

እኔና የቆሎ ጓደኞቼ የአብነት መምህራችን መጋቤ ምሥጢር አለቃ መሠረት ተሰማን ቢያንስ በወር አንደዜ “ለምን መጽሐፍ አይጽፉም?” የሚል የልጅነት ቅንዓት ፣ ጉጉትና ምኞት የወለደው ሃሳብ በጉባኤ መሃል ወርወር ባደረግላቸው ቁጥር እንዲህ ብለው ይመልሱ ነበር።
“መጽሐፍ ልጻፍ ብል ቤት መቀመጥ ፣ መጻሕፍት ማገላበጥ ግድ ይሆናል። ይህ ደግሞ የእናንተን የትምህርት ጊዜ ይሻማል። ስለዚህ እኔ እናንተው ላይ መጻፉን መርጫለሁ። እናንተ ደግሞ መጽሐፉን ትጽፉታላችሁ።”
ይህ አነጋገራቸው “ሰዎች ሁሉ በሚያውቁትና በሚያነቡት በልባችን የተጻፈ መልእክታችን እናንተ ናችሁ። እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደሆናችሁ የተገለጠ ነው።” የሚለው የቅዱስ ጳውሎስን ኃይለ ቃል ይመስላል።
እንዳሉትም እስከ መጨረሻይቱ ሕቅታ ድረስ አንድነትን ሦስትነትን ማመንን የሚያጸና ትምህርት እየጻፉ አረፉ። “መጽሐፉን እናንተ ትጽፉታላችሁ” የሚለው ትንቢትም ከዐሥር ዓመታት በፊት በበኩር የመንፈስ ልጃቸው በዲ/ን ዶ/ር አቤል ኃይሉ “የማእዘን ራስ” መጽሐፍ ተፈጽሟል። እነሆ አሁን ደግሞ የገዛ ብዕራቸው ውጤት “መጽሐፈ መሠረት” በሚል ርእስ ለኅትመት ብርሃን በቃ።

ይኼን መጽሐፍ የማዘጋጀት እድሌን አደንቃለሁ። ከፈቃደ እግዚአብሔር ጋር ይኼ ኃላፊነት ወደ እኔ እንዲመጣና እኔም በልዩ ትኩረት እንድፈጽመው ያደረጉኝ ክስተቶች ግን አሉ። በሕይወተ ሥጋ ሳይለዩን የአብነት ትምህርት የምስክር ወረቀት ከሰጧቸው የመጨረሻ ልጆቻቸው ማካከል አንዱ መሆኔ ፣ የመጨረሻ የጉባኤ ስብከታቸውን ያደግሁበትና በሰ/ት/ቤት አመራርነት ያገለገልኩበት ደብሬ ባዘጋጀው የኅዳር ሚካኤል ጉባኤ ላይ ጋብዣቸው ያስተማሩ መሆኑ ፣ በመጨረሻ በግል ሄጄ የተቀበልኩት የ”ዕዳ አለብህ” ቃላቸው ፣ የጊዜ ዕረፍታቸው የዓይን እማኝነት ዕጣ ከመንፈስ ልጆቻቸው መካከል እኔ ጋር የወደቀ መሆኑ በአጋጣሚ የሆነ አይመስለኝም።

ይልቁንም ዜና ሕይወታቸውንና ሥራዎቻቸውን ይዞ የወጣው የዳረጎት ልዩ ዕትም ዋና አዘጋጅ መሆኔ እኔ በግሌ ካሰባሰብኳቸው ሰነዶች በብዙ እጥፍ የሚበልጡ የልዩ ልዩ ዘመን አበርክቶአቸው እጄ እንዲገባ ምክንያት ሲሆን አንድ ላይ ሰብስቦ መጽሐፍ የማድረግ ሐሳብ ተፀነሰ። በፈቃደ እግዚአብሔርም እዚህ ደረሰ።

መጽሐፉ ሦስት አበይት ምእራፎች ያሉት ሲሆን በመጀመሪያው ምእራፍ ለኮርስ ስልጠና የተዘጋጁ ወጥ ሥራዎች ቀርበዋል። በሁለተኛው ምእራፍ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ በጽሑፍ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በጽሑፍ የሰጡትን ምላሽ ይዟል። የመጨረሻው ምእራፍ የሕይወት ታሪክ አምድ ሆኖ የግላቸውን የጉባኤ ቤት ቆይታ በወፍ በረር ፣ ለስንክሣርና ግብረ ሕማማት መተርጉም ወዳጃቸው ለሊቀ መዘምራን ላእከ ማርያም ወልደ ኢየሱስ የጻፉትን በቅኔ የተዋዛ ጽሑፍ ፣ እንዲሁም ዜና ሕይወታ ለማርያም ድንግልን አካቷል።
በቅጽ አንድ የተካተቱት ሥራዎቻቸው ለኅትመት በሚበቃ ምሉዕነት ስለተገኙ ብቻ እንጂ በቀጣይ ተሟልተው የሚዘጋጁ ብዛት ያላቸው ርእሰ ጉዳዮች እንደሚኖሩ ይታወቅልኝ።
በተረፈ ስለ ብዕራቸው የሥነ ጽሑፍ ውበት ፣ የምሥጢር ጉልበትና የሐሳብ ፍሰት እየተነተኑ ሊቁን ለእናንተ ማስተዋወቁ አስፈላጊ አልመሰለኝም። “ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ” ይላልና ቃሉ ከፍሬያቸው ዕወቋቸው። የቻልኩትን ያህል ለቅሜ በያዛችሁት ቅርጫት አኑሬላችኋለሁ። የተባረከ ማዕድ ይሁላችሁ።
https://www.instagram.com/p/CqYPYpXIA4T/?igshid=MDJmNzVkMjY=

Instagram

152 likes, 6 comments - dn.\_dr.\_kesatebirhan on March 29, 2023: "እኔና የቆሎ ጓደኞቼ የአብነት መምህራችን መጋቤ ምሥጢር አለ...

እኔና የቆሎ ጓደኞቼ የአብነት መምህራችን መጋቤ ምሥጢር አለቃ መሠረት ተሰማን ቢያንስ በወር አንደዜ “ለምን መጽሐፍ አይጽፉም?” የሚል የልጅነት ቅንዓት ፣ …
1 year, 2 months ago
ስንክሳር
1 year, 3 months ago

Watch "ተዋሕድዋ - የአድዋ ድል እና ተዋሕዷዊ ገድል" on YouTube
https://youtu.be/7_6A_kMAvSs

YouTube

ተዋሕድዋ - የአድዋ ድል እና ተዋሕዷዊ ገድል | Victory Of Adwa and EOTC

ይኽ ጥናት ቀመስ አድዋዊ ጽሑፍ ከሦስት ዓመት በፊት የዳረጎት ዲጂታል መጽሔት ላይ የወጣና ዛሬ ለ127ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በጸሐፊው ተተርኮ የቀረበ ነው።#eotc #adwa #victoryofAdwa

1 year, 3 months ago

#ስለምንታገልለት_ዕውቀት_ይኑረን

ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በKesatebirhan Ze Tewahdo Telegram Channel በLive stream በሰሞናዊ የቤተ ክርስቲያን ትኩሳት መነሻነት መታወቅ ያለባቸውን መሠረታዊ ነጥቦች እንማማራለን።

#የሚነሡ_ጉዳዮች

  1. ዶግማ ፣ ቀኖና ፣ ትውፊት ምንድናቸው? ዶግማ ፈረሰ ፣ ቀኖና ተጣሰ ፣ ትውፊት ተፋለሰ ሲባል ምን ማለት ነው። ቅጣቱስ ምንድን ነው?

  2. ምሥጢር ክህነት ፣ ምን? ለምን? እንዴት? ፣ ክብረ ክህነት።

  3. መፈንቅለ ክህነት በዘመነ ሙሴ ፣ የደብተራ ኦሪት ግርግርና መዘዙ

  4. አቤሴሎማዊነትና ዖዝያናዊነት በቤተ ክህነት

  5. የጵጵስና ታሪክ በኢትዮጵያ

  6. የጳጳሳት ስም ፣ ብፁዕ አቡነ እገሌ መባልና የስም ለውጥ የአስኬማ ፣ የጽሕምና የልብሳቸው ፣ የበትራቸውም ምሥጢርና ውክልና

  7. ኦርቶዶክስ በኦሮሞ ታሪክና ፖለቲካ መነጽር

  8. የአሁኑን ፈተና እንዴት እንመልከተው? እንዴትስ እንመክተው?

#ሰዓት_ከምሽቱ_3_ሰዓት

#ዕለታት_ቅዳሜና_እሑድ

የስሜት ብቻ ሳይሆን የዕውቀትም ጦር ዕቃ ለውጊያው ያስፈልገናል።

#ሊንኩን ተጭነው የChannelu Member በመሆን ይጠብቁ።
👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/KesatebirhanZeTewahdo

Telegram

Kesatebirhan Ze Tewahdo

ይህ የዲ/ን ከሣቴብርሃን ግጥሞች፣ወጎች፣ትረካዎች፣ተውኔቶች ፣ ስብከቶችና ወረቦች የሚተላለፉበት ሕጋዊ ገጽ ነው። እናንተም ከመንፈሳዊ አቅርቦቶቹ እንዲቋደሱና share በማድረግ ሌሎች እንዲያቃምሱ ጋበዝንዎ። "ዘመኑን እየዋጃችሁ፥በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ።"ቆላ.፬፥ የዩቲዩብ ቻናል ***👇*** https://youtube.com/channel/UCH5c3LZnu5c-cVbPT0ZI-rg

[#ስለምንታገልለት\_ዕውቀት\_ይኑረን](?q=%23%E1%88%B5%E1%88%88%E1%88%9D%E1%8A%95%E1%89%B3%E1%8C%88%E1%88%8D%E1%88%88%E1%89%B5_%E1%8B%95%E1%8B%8D%E1%89%80%E1%89%B5_%E1%8B%AD%E1%8A%91%E1%88%A8%E1%8A%95)
1 year, 4 months ago

Watch ""ትጉኃን የአምኑ ልደቶ - ትጉኃን ልደቱን ያምኑታል" - ሊደመጥ የሚገባው የልደት መልእክት" on YouTube
https://youtu.be/z-d4xuntJBE

YouTube

"ትጉኃን የአምኑ ልደቶ - ትጉኃን ልደቱን ያምኑታል" - ሊደመጥ የሚገባው የልደት መልእክት

ድንቅ ሊደመጥ የሚገባው የልደት መልእክት መምህር ዲ/ን ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ (ዶ/ር) New Ethiopian Orthodox Sibket by deacon doctor kesatebirhan Gebreyesus#eotc #newmezmur #sibket

1 year, 4 months ago

Watch ""ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት" ዕብ. 11÷13 | መምህር ዲያቆን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ" on YouTube
https://youtu.be/BRhwmDNljgM

YouTube

"ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት" ዕብ. 11÷13 | መምህር ዲያቆን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ

ይኽ ትምህርት ሊቀ ሊቃውንት መልአከ አማረና ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ በተገኙበት ጉባኤ ላይ ኅዳር 17 ቀን 2015 ዓ.ም የተሰጠ ትምህርት ነው።New Ethiopian Orthodox Sibket by deacon doctor kesatebirhan Ge...

1 year, 6 months ago

Watch "የኤፍራጥስ ወንዝ መድረቅ አንድምታዎች - ዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ" on YouTube
https://youtu.be/JkKkmVtzYQU

YouTube

የኤፍራጥስ ወንዝ መድረቅ አንድምታዎች - ዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ

#eotc #interview #orthodox

1 year, 6 months ago

Watch ""አባቴ ሚካኤል" - ዘማሪት ፍቅርተ የተሻወርቅ | ልብን ደስ የሚያሰኝ ዝማሬ ||New ethiopian orthodox mezmur 2022" on YouTube
https://youtu.be/9l7rLq_X55g

YouTube

"አባቴ ሚካኤል" - ዘማሪት ፍቅርተ የተሻወርቅ | ልብን ደስ የሚያሰኝ ዝማሬ ||New ethiopian orthodox mezmur 2022

ከሣቴብርሃን ዘተዋሕዶ ***©***Kesatebirhan ze tewahdo #eotc #orthodoxmezmur #newmezmur

We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month, 2 weeks ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 4 days, 23 hours ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 5 months, 1 week ago